Latest blog posts

-ዓቃቤ ሕግ አቤቱታውን ተቃውሞ ምላሽ ሰጥቷል 

-ፍርድ ቤቱ መርምሮ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሰጠ

በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው ላለፉት ሁለት ዓመታት በክርክር ላይ የሚገኙትና በክስ መዝገብ 141352 ላይ ከተካተቱት ውስጥ፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና ሌሎች ተከሳሾች፣ የቀረበባቸው ክስ ተሰርዞ በነፃ እንዲሰናበቱ ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ፡፡ 

በፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ የተመሠረተባቸውን ክስ እየመረመረው ለሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት አቤቱታ ያቀረቡት አቶ መላኩ ፈንታ፣ አቶ ገብረዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ፣ አቶ በላቸው በየነ፣ አቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር፣ አቶ ስማቸው ከበደ፣ አቶ ገብረ ሥላሴ ኃይለ ማርያም፣ ነፃ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ኮሜት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርና ሌሎችም ናቸው፡፡ 

ተከሳሾቹ ለፍርድ ቤቱ የአቤቱታ ማመልከቻ ያስገቡበትና ክሱ እንዲሰረዝላቸው የጠየቁበት ምክንያት፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንን የሚመለከተው አዲስ አዋጅ ቁጥር 859/2006 እነሱ የተከሰሱበትን ክስ ውድቅ እንዳደረገው በመግለጽ ነው፡፡ 

አቶ መላኩ በክስ መዝገብ 141352 ላይ ሦስት ክሶች የቀረቡባቸው ሲሆን፣ የመጀመርያው ለሆቴል አገልግሎት ከቀረጥ ነፃ የገቡ ዕቃዎች ከታለመላቸው ዓላማ ውጪ መዋላቸውን በሚመለከት መረጃ ቢደርሳቸውም፣ ከባለሀብቱ ጋር በመመሳጠር ምርመራ እንዳይጀመርና ለሕግ እንዳይቀርብ አድርገዋል የሚል ነው፡፡ የቀድሞዎቹ አዋጆች፣ አዋጅ 60/89፣ 368/95 እና 622/01 በወንጀል ተጠያቂ የሚያደርጉ ድንጋጌዎች የነበራቸው ቢሆንም፣ በአዲሱ አዋጅ 859/2006 አንቀጽ 181(1) ሙሉ በሙሉ ተተክተው፣ በአንቀጽ 163(1) መሠረት በአስተዳደር ውሳኔ በገንዘብ መቀጮ ብቻ የሚያልቅ እንዳደረገው በመግለጽ አመልክተዋል፡፡ 

ሌላው ቀርቦባቸው የነበረው ክስ ምንም ዓይነት የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ያልተፈጸመባቸው፣ ገደብና ቁጥጥር የተደረገባቸውን 32 ዓይነት ብዛት ያላቸው የተለያዩ ዓይነት የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲገቡ ይያዛሉ፡፡ ክስ ተመሥርቶባቸውና ለፍርድ ተቀጥረው እያሉ፣ ያለ ሕጋዊ ምክንያት ክሱ እንዲነሳ አድርገዋል የሚል ክስ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ይህም ክስ ገደብና ቁጥጥር ከተደረገበት ዕቃ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በቀደመው አዋጅ ወንጀል የነበሩት ድንጋጌዎች፣ በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 156(1) መሠረት ወንጀልነቱ ቀሪ መሆኑ ቀርቶ በአስተዳደራዊ ውሳኔ በገንዘብ መቀጮ የሚያልቅ መሆኑን ጠቁመው ክሱ እንዲሰረዝ ጠይቀዋል፡፡ 

ሁሉም ተከሳሾች (አቤቱታ ያቀረቡት) እንደ አቶ መላኩ ፈንታ የቀረበባቸው ክስ በአዋጅ ቁጥር 60/89፣ 368/95 እና 622/01 የነበረ መሆኑን በማስታወስ፣ በአዲሱ አዋጅ 859/2006 አንቀጽ 181/(1) መሠረት ሙሉ ለሙሉ የተሻሩ መሆኑን በመጠቆም፣ በተዘረዘሩት ተገቢ አንቀጾች መሠረት የቀረበባቸው ክስ እንዲሰረዝላቸው ጠይቀዋል፡፡ 

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ በሰጠው የአቤቱታ መቃወሚያ መልስ እንዳብራራው፣ እነ አቶ መላኩ ፈንታ የተከሰሱት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1)ሀ እና 411 የተመለከተውን በመተላለፍ እንጂ፣ የጉምሩክ አዋጅ አለመሆኑን ገልጿል፡፡ ድንገተኛ ቆጠራ ተደርጐ ባለበት ሁኔታ ድጋሚ ቆጠራ በማስደረግ ቀረጥና ታክስ እንዲቀንስ ያስደረጉ በመሆናቸው፣ ባልተሰረዘ አንቀጽ ክስ እንዲነሳላቸው መጠየቃቸው አግባብ አለመሆኑን ገልጾ፣ አቤቱታው ውድቅ እንዲደረግ ጠይቋል፡፡ 

 

ሌላው ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ የተባሉት ተከሳሽ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ያልተፈጸመባቸውንና ገደብና ቁጥጥር የሚደረግባቸውን 32 ዓይነት የተለያዩ ብዛት ያላቸው የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችን በአራት ሻንጣዎች በአየር መንገድ ሲያስገቡ መያዛቸውን፣ ክስ ተመሥርቶባቸውና ለፍርድ ተቀጥረው ባለበት ሁኔታ ክሱ እንዲቀር ተደርጎላቸዋል ስለተባለው ዓቃቤ ሕግ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ዶ/ር ፍቅሩ ዕቃውን በመጀመርያ ሲያስገቡ መስመሩን የተከተለ በመሆኑ ፈቃድ እንዲያቀርቡ መጠየቃቸውን ገልጿል፡፡ ማቅረብ ባለመቻላቸው በሕጋዊ መንገድ ከአገር ዕቃውን እንዲያስወጡ ቢደረጉም፣ በድብቅ መልሰው ሲያስገቡ መያዛቸውን አክሏል፡፡ በዚህ መሠረት በአዋጅ 622/01 አንቀጽ 91(1)ም ሆነ 859/06 አንቀጽ 168(1)ም የኮንትሮባንድ ወንጀል በመሆኑ ሕጉ አለመሻሩን ጠቁሟል፡፡ ዶ/ር ፍቅሩ የተከሰሱት በኮንትሮባንድ ወንጀል በመሆኑ ስለመንገደኞች የዕቃ ዲክለራሲዮን ኦዲትና አቀራረብ የተደነገገውን አንቀጽ 30/2/ለን በመጥቀስ ክሱ እንዲነሳ ማመልከታቸው ከጉዳዩ ጋር አግባብነት የሌለው በመሆኑ አቤቱታው ውድቅ እንዲደረግለት ዓቃቤ ሕግ ጠይቋል፡፡ ዓቃቤ ሕግ ሌሎች ተከሳሾችም ያቀረቡትን ‹‹ክስ ይሰረዝልን›› አቤቱታ በመቃወም ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ 


Editors Pick

Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
  ዶ/ር ትዝታ በፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጉዳዩዋን ለመከታተል በችሎት ታድማለች፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በቤቷ ላይ ያለአግባብ ፍርድ ተሰጥቷል ብላ ስላመነች የተማረ ጠበቃ የይግባኝ አቤቱታ ጽፎላት ጉዳይዋን በራሷ ትከታተላለች፡፡ እንደ እርሷ አስተሳሰብ ጉዳይዋን ከእርሷ ይልቅ የሚረዳው የለም በሚል ...
12323 hits
Constitutional Law Blog
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ መንግሥት የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን የሚያቋቁም አዋጅ ማፅደቁ ይታወቃል፡፡ አዋጁ በተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ የጦፈ ክርክርን አስነስቶ በ33 ተቃውሞ እና በ4 ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ቢፀድቅም በፓርላማ ውስጥ ለአዋጁ ድምፅ ከነፈጉ የሕዝብ ተወካዮች ጀምሮ እስከ ክል...
9925 hits
Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
  ይህን ለመጻፍ ያስገደዱኝን እና የገጠመኙን ሁኔታዎች በቅድሚያ ላብራራ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው አንድ ሰራተኛ አሰሪው በነበረው ድርጅት ላይ ህገ-ወጥ የስራ ውል መቋረጥ ተፈጽሞብኛል በማለት ላቀረበው ክስ አሰሪው ድርጅት በተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠኝ ሰራተኛው የስራ ውሉን ስላቋረጠ ካሳ እንዲከፍለኝ የሚ...
13451 hits
Others
የኢትዮጵያ የህግ ስርዓት በተለያዩ የመንግስት የአስተዳደር ስርዓት ውስጥ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ልዩነቶች ሲታዩበት የነበረ ቢሆንም አደረጃጀቱም የዚያኑ ያክል ተለዋዋጭነት የነበረው መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በተለይም ከያዝነው ርዕስ ጋር በተያያዘ የፍርድ ቤቶች አደረጃጀትና በጉዳዮች ላይ የመጨረሻ ውሰኔ የመስጠት ሂደት በተ...
13162 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...