Latest Blog posts
Editors Pick
Latest documents
Education and Training Policy of Ethiopia - Amharic version - 2023 7120 Downloads - policies and strategies | 7.6 MB | |
The Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration - the Extent of Party Autonomy 163 Downloads - Arbitration Law | 635.59 KB | |
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25 8047 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 10.72 MB | |
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ እይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ FEATURED 350 Downloads - Criminal Law | 317.19 KB | |
Federal Supreme Court Cassation Decisions - Table of content Volume 1-25 9940 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 6.57 MB |
- Details
- Category: Legal News - የሕግ ዜናዎች
የአርበኞች ግንባርን ተቀላቅለዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በሽብርተኝነት ተከሰሱ
በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደርና ኅብረተሰቡን ለማስፈራራት፣ እንዲሁም ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በትጥቅ ትግልና በኃይል ለማፈራረስ የሽብር ቡድን ከሆነው የአርበኞች ግንባር ጋር በመቀላቀል ሲያሴሩ በቁጥጥር ሥር ውለዋል በተባሉ ስድስት ተጠርጣሪ ወጣቶች ላይ፣ የሽብርተኝነት ክስ መጋቢት 29 ቀን 2007 ዓ.ም. ተመሠረተ፡፡
በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ የተመረሠረተባቸው ተጠርጣሪዎች፣ ሁሉም በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ይኖሩ የነበሩ ናቸው፡፡ እነሱም አምላኩ መስታዬት (ቅጽል ስም ባሪያው ጎይቶም)፣ ኢሳያስ ማሩ (ለዛው)፣ ጀጃው ዓለማየሁ፣ ወርቁ ዳኘው፣ አሳመረው አሰፋና አብነት ደሳለኝ ይባላሉ፡፡ ሁሉም ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 28 ክልል ውስጥ ያለ ነው፡፡
ተከሳሾቹ የአገሪቱን ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ለማፈራረስ ከሚንቀሳቀሰው የአርበኞች ግንባር ከሚባለው የሽብር ቡድን ጋር መቀላቀላቸውንና መመልመላቸውን የቀረበባቸው ክስ ያስረዳል፡፡ ወጣቶቹ በግንባሩ ከተመለመሉ በኋላ ወደ ኤርትራ ሄደው ወታደራዊ ሥልጠና መውሰዳቸውን፣ ቀደም ብለው የሽብር ቡድኑን በተቀላቀሉ ዘመዶቻቸው መመልመላቸውንና ሥልጠና ወስደው ሲጨርሱ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ሌሎችን ወጣቶች ሲመለምሉ እንደነበር ክሱ ያብራራል፡፡ በሱዳን በኩል በማቋረጥ ኤርትራ ደርሰው ለመሠልጠን ከግንባሩ የገንዘብ ድጋፍ ይደረግላቸው እንደነበረም ክሱ ይገልጻል፡፡
ሁሉም ተከሳሾች በ2007 ዓ.ም. መጀመሪያ ወር ጀምሮ እስከ ታኅሳስ ወር መጨረሻ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ጎንደር ከተማ ውስጥ የተያዙ መሆናቸውን የሚጠቁመው ክሱ፣ በአጠቃላይ በፈጸሙት በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ የመሳተፍ ወንጀል መከሰሳቸውን ይገልጻል፡፡ የአርበኞች ግንባር በፓርላማ በሽብርተኝነት ከተፈረጁ የሽብር ቡድኖች ዝርዝር ውስጥ አልተካተተም፡፡
ፍርድ ቤቱ የጠበቆች ጽሕፈት ቤት ለተጠርጣሪዎቹ ተከላካይ ጠበቃ እንዲያቆምላቸው፣ ክሱን የሚቃወሙ ከሆነ ከተከሳሾቹ ጋር በመነጋገር የክስ መቃወሚያ እንዲያቀርብ ለግንቦት 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቶ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ አዟል፡፡