Latest Blog posts
Editors Pick
Latest documents
Education and Training Policy of Ethiopia - Amharic version - 2023 7263 Downloads - policies and strategies | 7.6 MB | |
The Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration - the Extent of Party Autonomy 218 Downloads - Arbitration Law | 635.59 KB | |
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25 9026 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 10.72 MB | |
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ እይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ FEATURED 408 Downloads - Criminal Law | 317.19 KB | |
Federal Supreme Court Cassation Decisions - Table of content Volume 1-25 10533 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 6.57 MB |
- Details
- Category: Legal News - የሕግ ዜናዎች
በህገ ወጥ መንገድ ቤሩት በመላክ የሰው ህይወት እንዲጠፋ ያደረገው ግለሰብ በ8 ዓመት ፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ
የማማለያ ቃላትን በመጠቀም ልጅሽን ወደ ውጭ እልካታለው በማለት ከ12 ሺህ ብር ተቀብሎ ልጅቷን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ቤሩት በመላክ ህይወቷ እንዲጠፋ ያደረገው ግለሰብ በ8 ዓመት ፅኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ ተወሰነ።
ተከሳሽ ቢኒያም ወርቁ ይሰኛል።
ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ወደ ውጪ አገራተ የመላክ ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው ዜጎችን ወደውጪ አገራት በመላክ ወንጀል ነው አቃቤህግ ክስ የመሰረተበት።
በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃመ ዞን ሸበላ ወረዳ መስከረም 2004 ዓ.ም በህጋዊ መንገድ ወደ ሳዑዲ ረቢያና ወደ ተለያዩ አገራት እልካችኋለሁ በማለት የተለያዩ ሰዎችን የማሳመን ስራ ለመስራት ይንቀሳቀሳል።
ወይዘሮ ስናፍቅሽ እያያው ወደተባሉ እማወራ ቤት በመዝለቅ ም ልጅሽን ለምን ወደውጪ አገር አልክልሽም በማለት ለማሳመን ሞክራል።
በተጨማሪም ልጅቷን በህጋዊ መንገድ እንደሚልካትበመንገር አዲስ አበባ በመሀድ ለምታከናውነው የጤና ምርመራ እና ለተለያዩ ሂደቶች ማስፈፀሚያ በሚል 12 ሺህ ብር ይቀበላል።
ተከሳሽ ልጅቷ ወደ አዲስ አበባ እንድትመጣ የህክምና እና የአሻራ ምርመራ እንድታደርግ እና የፓስፖርት ቀጠሮ በማስያ ወደ መኖሪያዋ እንድትመለስ አድርጓልም ነው የሚለው የአቃቤህግ ክስ።
ተከሳሹ ግንቦት 2004 ዓ.ም ስልክ ወደ ልጅቷ ቤተሰቦች በመደወል ፣ ሂደቱ እንዳለቀ በመግለፅ ወደ አደስ አበባ እንድትመለስ እና የተነጋገሩበትን የገንዘብ መጠን ይዛ እንድትመጣ ይጠይቃል።
ግንቦት 30፣ 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው አውቶብስ ተራ አካባቢ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ቀሪ 12 ሺህ ብሩን ከልጅቷ በመቀበል፥ ሰኔ 20፣ 2004 ዓ.ም ወደ ቤሩት ሀገር እንድትሄድ ያደርጋል።
በሄደች በስድስት ወሯ ህዳር 6 ቀን 2005 ዓ.ም ከ11ኛ ፎቅ ላይ ተወርውራ በመውደቅ በራስ ቅሏ ላይ በደረሰባት ስብራት ህይወቷ ሊያልፍ ችሏል።
አስክሬኗም ታህሳስ 6፣ 2005 ዓ.ም ወደ ትውልድ አገሯ ይገባለ።
አቃቤህግም በፈፀመው ህገወጥ በሆነ መንገድ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ወደውጪ አገር የመላክ ወንጀል ክስ መስርቶበታል።
ተከሳሽ የወንጀል ድርጊቱን አለመፈፀሙን ክዶ ቢከራከርም አቃቤህግ ያቀረበውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ብሎታል።
ተከሳሽ የቀደመ የወንጀል ሪከርድ የሌለበት እና ሊድን የማይችል ህመም ያለበት መሆኑን በቅጣት ማቅለያነት በመያዝ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሶስተኛ ፍርድ ቤት በስምንት ዓመት ፅኑ እስራት እና በሁለት ሺህ ብር መቀጮ ቀጥቶታል።