Latest blog posts

በኢትዮጵያ ውስጥ አባላትን በመመልመል መንግሥትንና ተቋማቱን እንዲሰልሉ፣ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትሕዴን) ወይም ዴሞክራሲያዊ ምንቅስቃስ ሕዝቢ ትግራይ (ዴምሕት) ብሎ በሚጠራው ቡድን የተመለመሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሠረተ፡፡

የወንጀል ድርጊት በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም የአይዲዎሎጂ ዓላማን ለማራመድ፣ ሕዝብን ለማስፈራራትና በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ሲንቀሳቀሱ ነበር ተብለው በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ የተመሠረተባቸው፣ ነዋሪነታቸው በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ በሆኑት አቶ አማረ ተወልደና አቶ ታሪኩ በላይ ላይ ነው፡፡ 

ተከሳሾቹ የሽብር ቡድን ነው ከተባለው ድርጅት ጋር በስልክ በመገናኘት፣ አባል በመሆንና መመርያ በመቀበል፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አባላትን በመመልመል፣ የኢትዮጵያ ተቋማትን በመሰለልና መረጃ አሳልፈው በመስጠት በሽብር ወንጀል ውስጥ የተሳተፉ መሆናቸውን፣ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተው ክስ ያስረዳል፡፡ 

አቶ አማረ ተወልደ የተባሉት አንደኛ ተከሳሽ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እያሉ ያውቋቸው የነበሩትንና አሁን ኤርትራ ከሚገኙት የትሕዴን ወይም ዴምሕት አመራር አቶ ጐይቶም በርሔ ጋር በተንቀሳቃሽ ስልክ እየተደዋወሉ (ስልክ ቁጥሩ ተጠቅሷል) የግለሰቦችን ተንቀሳቃሽ ስልክ ይሰጡ እንደነበር፣ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ኢሕአዴግና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ እንዳይጠሩ እንደሚፈልግ፣ ሕዝቡ በስብሰባ እንዳይሳተፍ አፈና እንደሚያደርግና ሌሎች መረጃዎችን ይቀባበሉ እንደነበር ክሱ ያስረዳል፡፡

መንግሥት ያላደረገውን ነገር ግን በጭላ፣ በኢሮብና በማይጨው በሚገኙ የዓረና ትግራይ ለሉዓላዊነት ፓርቲ አባላት ላይ ችግር እያደረሰባቸው መሆኑን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ዓረና ፓርቲ ውቅሮ ከተማ ውስጥ የተሳካ ሕዝባዊ ስብሰባ ማድረጉን፣ አቶ ብርሃነና አቶ አብርሃ በተባሉ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ስብሰባው መመራቱንና ዝርዝር መረጃ ይቀባበሉ እንደነበረ ክሱ ይዘረዝራል፡፡ መንግሥት ያላደረገውን እንዳደረገና በሕዝብ ላይ በደል የደረሰ በማስመሰል ሐሰተኛ መረጃ ሲያስተላልፍ እንደነበርም ይጠቁማል፡፡

በትግራይ ክልል የተለየ በደል በሕዝቡ ላይ እየደረሰ መሆኑንና ሌሎች መረጃዎችን ማስተላለፉንና በወልቃይት የስኳር ፋብሪካ ለመገንባት የአካባቢው ነዋሪዎች ያለምንም ካሳ እየተፈናቀሉ መሆኑን የሐሰት መረጃዎችን በማቀበል አገርን አደጋ ላይ የሚጥል እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደነበር የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ ሁለቱም ተከሳሾች ትሕዴን/ዴምሕት የሚባል ስያሜ ያለው የሽብር ቡድን ውስጥ አባል በመሆንና ከቡድኑ አመራሮች ጋር በስልክ መረጃ በማስተላለፍ፣ በፈጸሙት በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ መሳተፍ ወንጀል እንደተከሰሱ ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሷል፡፡ 

ፓርላማው በሰኔ ወር 2003 .. በሽብርተኝነት የፈረጃቸው አምስት ድርጅቶች ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ አልቃይዳና አልሸባብ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በሽብርተኝነት ወንጀል ለመክሰስ ቢቻልም፣ አንድን ድርጅት ሽብርተኛ ለማለት የሚቻለው ፓርላማ ሲወስን ነው፡፡ ትሕዴን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀ ቡድን አይደለም፡፡


Editors Pick

Legislative Drafting Blog
How many countries have ‘Codes’ as a basic legal source in the world? In how many countries legal systems the term ‘Codification’ exist? Are there common features of codification used as a basis for c...
11206 hits
Constitutional Law Blog
{autotoc}     Introduction In this piece, I will examine the legality of and intent induced the State of Emergency (SoE) declared on Feb. 16, 2018, in Ethiopia. Throughout, I will utilise legal and pu...
11151 hits
Arbitration Blog
{autotoc}   The legislator who, on the plea of checking litigation, or on any other plea, exacts of a working man as a preliminary to his obtaining justice, what that working man is unable to pay, doe...
3308 hits
Criminal Law Blog
“Violations of human rights are both a cause and a consequence of trafficking in persons.”                                       UN human rights office of the High Commissioner, fact sheet 36  Introdu...
10895 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...