Latest blog posts

-በድጋሚ ፍርድ ቤት ደፍራችኋል በሚል የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶ ለቅጣት ተቀጠሩ

 ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትሕ ጠምቶታልና እግዚአብሔር ፍትሕ ይስጠው››አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል የነበሩ

 ‹‹ተራ ስድብ ተሳድባችኋልና ማዕከላዊ እንድትመረመሩ እናዛለን›› ፍርድ ቤት

በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው በሙግት ላይ የሚገኙት የአንድነት፣ የዓረናና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ አቶ አብርሃ ደስታና አቶ የሺዋስ አሰፋ ጥፋተኛ በተባሉበት ፍርድ ቤትን መድፈር ወንጀል ክስ፣

እያንዳንዳቸው በሰባት ወራት እስራት እንዲቀጡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19 ወንጀል ችሎት መጋቢት 1 ቀን 2007 .. የቅጣት ውሳኔ ሰጠ፡፡

ተከሳሾቹ የሰባት ወራት የእስራት ቅጣት የተወሰነባቸው የዋስትና መብት ተከልክለው በእስር ላይ በሚገኙበት የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች፣ ታኅሳስ 12 13 አጥቢያ 2007 .. የተቋሙ አባላት ባልሆኑ የደኅንነትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ናቸው ባሏቸው ግለሰቦች ተፈትሸው፣ ሰነዶችና ገንዘብ እንደተወሰደባቸው ለፍርድ ቤቱ ላቀረቡት አቤቱታ፣ ‹‹በማስረጃ የተደገፈ አይደለም›› በማለት ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ብይን በመቃወም ባሰሙት ንግግር፣ ‹‹ፍርድ ቤት ደፍራችኋል›› ተብሎ በተላለፈባቸው የጥፋተኝነት ውሳኔ ነው፡፡ 

ፍርድ ቤቱ መጋቢት 1 ቀን 2007 .. እያንዳንዳቸው በሰባት ወራት እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ማሳለፉን በችሎት ሲያሰማ፣ የሦስቱም ፓርቲዎች አመራሮች በማጨብጨባቸው ችሎቱ ለደቂቃዎች ታውኮ ነበር፡፡ ፍርድ ቤት አለመድፈራቸውንና በወቅቱ የተናገሩት መሯቸው እንደሆነ በቡድን ተናግረዋል፡፡

በፍርድ ቤት ሊናገሩ የቻሉት መሯቸውና ፍርድ ቤቱአሻንጉሊት ፍርድ ቤትበመሆኑ ፍትሕ እንደማያገኙ በማመናቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ችሎቱ እውነተኛ ችሎት ባለመሆኑ ችሎት አለመድፈራቸውንም አስረድተዋል፡፡ 

ፍርድ ቤቱ በተደጋጋሚ የአመራሮቹን ንግግር አስቁሞ፣ ‹‹ተራ ስድብ ሰድባችሁናል፡፡ ፖሊስ ወደ ማዕከላዊ ወስዶ እንዲመረምራችሁ እናደርጋለን፤›› ካለ በኋላ፣ ፍርድ ቤቱ አሻንጉሊት ስለሆነ ፍትሕ እንደማያገኙ የተናገሩትን አቶ አብርሃ ደስታ እያስቀረፁ እንዲናገሩ ፍርድ ቤቱ ሲጠይቃቸው፣ ‹‹ሰምታችኋል ለምን በድጋሚ እናገራለሁ? ከዚህ በፊትም ተቀርጬ ነው ጉድ የሆንኩት፤›› በማለት ሳይናገሩ ቀርተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ተመካክሮ ሦስቱም አመራሮች ጥፋተኛ መሆናቸውን ከነገራቸው በኋላ የቅጣት ማቅለያ እንዲያቀርቡ ሲጠየቁ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ ‹‹እኛ በፍርድ ቤቱ ላይ እያፌዝን አይደለም፣ ታፍነናል፤›› ሲሉ ፍርድ ቤቱ አስቁሟቸዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ አመራር አቶ ዳንኤል ሽበሺ ሲጠየቁ፣ ‹‹ፍትሕ የለም …›› ሲሉ እሳቸውንም ፍርድ ቤቱ ሲያስቆማቸው፣ ‹‹ታዲያ እንዴት ልናገር?›› ቢሉም ፍርድ ቤቱ ከልክሎ ሦስቱም አመራሮች ከችሎቱ እንዲወጡ አዝዟል፡፡ አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትሕ ተጠምቷልና እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትሕ ይስጠው፤›› እያሉ ችሎቱን በፖሊስ ኃይል እንዲለቁ ተደርገዋል፡፡

በሽብርተኝነት ከተጠረጠሩትና ክስ ከተመሠረተባቸው የአንድነት አመራሮች አንዱ የሆኑት አቶ ሀብታሙ አያሌው ተነስተው አቤቱታ እንዳላቸው ሲናገሩ ተፈቀደላቸው፡፡ ታኅሳስ 12 13 ቀን 2007 .. የማረሚያ ቤት አባላት ባልሆኑ ሰዎች ተፈትሸው ገንዘብና ሰነዶች እንደተወሰዱባቸው ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ማቅረባቸውን አስታወሱ፡፡ በወቅቱ አቤቱታውን ያቀረቡት በጠበቃቸው በአቶ ተማም አባቡልጉ አማካይነት ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ በወቅቱ የሰጠው ምላሽ ለደኅንነታቸው እንደሚያሰጋቸው ገልጿል፡፡ በመሆኑም በወቅቱ ሲያመለክቱ ስላልተመዘገበላቸው አሁን እንዲመዘገብላቸው አመልክተዋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በወቅቱ በጠበቃቸው በኩል ሲያመለክቱ፣ ከአንድ ጠበቃ የማይጠበቅ አቤቱታ መሆኑንና ማረሚያ ቤቱ የበቀል ዕርምጃ ቢወስድባቸውስ የሚል ምላሽ ፍርድ ቤቱ በመስጠቱ፣ ፍርድ ቤቱ ምንም እንደማያደርግላቸው በመገንዘባቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ አስሮዋቸው ዋስትና ሲከለክላቸው፣ ደኅንነታቸውን የሚጠብቅ ቢሆንም አሁን ግን ለደኅንነታቸው ሥጋት እንዳለባቸው አመልክተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ አቤቱታውን ውድቅ በማድረጉ ምክንያት ይግባኝ ማለት አለማለታቸውን ወደፊት የሚያየው መሆኑን ገልጾ እንዲመዘገብላቸው ግን አሳስቧል፡፡

ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ አቶ ሀብታሙ አቤቱታቸውን በጽሑፍ አቅርበው ብይን እንደሚሰጥ፣ በሦስቱ አመራሮች ላይ ችሎት በመድፈር ጥፋተኛ እንደሆኑ ለሁለተኛ ጊዜ የወሰነው ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለመጋቢት 3 ቀን 2007 .. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡


Editors Pick

Labor and Employment Blog
{autotoc}   Abstract A minimum wage is the lowest wage that employers may legally pay to workers. The purpose of minimum wages is to protect workers against unduly low pay and they are essentially lab...
4000 hits
Commercial Law Blog
   {autotoc}     Abstract Ethiopia introduced a new Commercial Code in March 2021, replacing the Commercial Code of the Empire of Ethiopia Proclamation No. 166/1960 (the repealed Commercial Code) that...
6688 hits
Construction Law Blog
  “And they said, Go to, let us build us a city and a tower, whose top may reach unto heaven; let us make as a name, lest we be scattered abroad upon the face of the whole earth…Therefore is the name ...
20946 hits
Family Law Blog
{autotoc}   1. መግቢያ ቤተሰብ የአንድ ማኅበረሰብ በጣም ጠቃሚ እና መሠረት የሆነ አካል ነው፡፡ ቤተሰብ አንድ ግለሰብን ከአጠቃላይ ማኅበረሰብ ጋር የሚያገናኝ ታላቅ ድልድይ ነው፡፡ እንዲሁም ተፈጥሮዊ ኢኮነሚያዊ እና ማኅበረሰባዊ ጥቅም አለው፡፡ በእርግጥ ቤተሰብ በቁጥር ትንሽ ሊሆን ይችላል ነገረግን የአንድ ቤ...
17459 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...