Latest blog posts

-የተጠራው ጠቅላላ ጉባዔ ተሰረዘ

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አሥረኛውን ጠቅላላ ጉባዔ ታግዶ እንዲቆይ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ለማሳገድ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ሆነ፡፡

ታኅሳስ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. ለማካሄድ የታቀደው ጠቅላላ ጉባዔ መሰረዙን ንግድ ምክር ቤቱ አስታወቀ፡፡ ንግድ ምክር ቤቱ ከኅብረት ኢንሹራንስ ኩባንያ ጋር በነበረበት ክርክር በፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አሥረኛው ጠቅላላ ጉባዔ ታግዶ እንዲቆይ ትዕዛዝ የሰጠው፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል በነበረው ክርክር የዘጠነኛው ጠቅላላ ጉባዔ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች መሻራቸው በመወሰኑ ነው፡፡ ይህንንም ውሳኔ ለማስፈጸም አሥረኛው ጠቅላላ ጉባዔ ሳይካሄድ እንዲቆይና በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ታኅሳስ 20 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ 

ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመውሰድ ከዚህ ቀደም የቀረበው የሰበር አቤቱታ ታይቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ፣ የፌዴራል ይግባኝ ሰሚ ችሎት ኅዳር 16 ቀን 2007 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ አፈጻጸሙ ታግዶ እንዲቆይ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ጠይቋል፡፡ 

በዚሁ ጥያቄ መሠረት ከቀጠሮው በፊት ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የንግድ ምክር ቤቱን አቤቱታ ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ ታኅሳስ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ባዋለው ችሎት የንግድ ምክር ቤቱን ጥያቄ ውድቅ ያደረገበትን ምክንያት በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ በሰጠበት መዝገብ አንድ ጉዳይ ለሰበር ችሎት ሊቀርብ የሚችለው ቅሬታ የቀረበበት ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተገኘበት እንደሆነ ብቻ መሆኑን አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ አንድ እንደሆነ አመልክቷል፡፡ 

አያይዞም እንዲታገድ ትዕዛዝ የሚሰጠውም ተከራካሪ ወገኖች ባሉበት ነገሩ እስኪሰማ ድረስ በወንጀልና በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጎች የተደነገገ በመሆኑም ጠቅሷል፡፡ በዚህ መሠረት የቀረበውን የንግድ ምክር ቤቱ የዕግድ ጥያቄና የሰበር አቤቱታውን መነሻ በማድረግ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞባቸዋል የተባሉትን ውሳኔዎች፣ አግባብነት ካለው ሕግና በየፍርድ ቤቱ ከተደረጉት ክርክሮች ጋር አገናዝቦ በመመርመር የዕግድ ትዕዛዝ የተጠየቀባቸው ተጠቃሾቹ መዝገቦች ከዚህ ጉዳይ ጋር የሚያያዙ አይደሉም ብሏል፡፡ 

‹‹በዚሁ መሠረት በሰጠው ትዕዛዝ በሥር ፍርድ ቤቶች መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተሠርቷል ለማለት ባለመቻሉ የቀረበውን የዕግድ ጥያቄ አልተቀበልነውም፤›› በማለት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት አያስቀርብም በማለት ትዕዛዝ ሰጥቶ መዝገቡን ዘግቷል፡፡ 

ንግድ ምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባዔውን እንዳያካሂድ የተወሰነበት፣ ከአንድ ዓመት በፊት በዘጠነኛ ጠቅላላ ጉባዔው ላይ በንግድ ምክር ቤቱ በአባልነትና በተሳታፊነት ከሚታወቁ አባላት መካከል አንዱ የሆነው ኅብረት ኢንሹራንስ ኩባንያ የወከላቸውን ግለሰብ በጉባዔው ላይ እንዳይሳተፉ በማገዱ በተመሠረተ ክስ ነው፡፡ 

ንግድ ምክር ቤቱ ኅብረት ኢንሹራንስ ኩባንያ ወክሎ የላካቸውን አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ በጠቅላላ ጉባዔው እንዳይሳተፉ ያደረገው የቀድሞው ቦርድ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ነው ይላል፡፡ 

ለዕገዳው የሰጠው ምክንያትም አቶ ኢየሱስ ወርቅ የንግድ ምክር ቤቱን ደንብና ሥርዓት በመፃረር የተቋሙን ስም እያጠፋ ነው የሚል እንደነበር ይታወሳል፡፡ አቶ ኢየሱስ ወርቅ ደግሞ ንግድ ምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባዔ ለማካሄድ እየተጠቀመበት ያለው የምልዓተ ጉባዔ ቀመር ሕገወጥ በመሆኑ፣ ይህንንም አውቆ ወደ ሕጋዊ መንገዱ መምጣት አለበት ብለው በመከራከራቸውና ንግድ ምክር ቤቱም ይህንን ባለመቀበሉ የተፈጠረ ችግር መሆኑን በተደጋጋሚ ሲገልጹ ነበር፡፡ 

ከንግድ ምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት በተገኘው መረጃ መሠረት፣ ታኅሳስ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ሊካሄድ የነበረው አሥረኛው ጠቅላላ ጉባዔ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሠረት አይካሄድም፡፡


Editors Pick

Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
  ኢትዮጵያውን የሚሳተፉባቸውን የማኅበራዊ ሚዲያዎች ለሚጠቀምና ሌሎች ተጠቃሚዎች የሚጽፏቸውን ወይንም የሚጭኗቸውን ጽሑፎች፣ ምሥሎችና ድምፆች ለሚከታተል ሰው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንድ ግልጽ የሆነ አዝማሚያ እያደገ መምጣቱን ያስተውላል፡፡ ይኼውም ጥላቻን ያዘሉ ንግግሮች መበራከታቸውን ነው፡፡ የጥላቻ ንግግር እጅግ ብዙ ...
12756 hits
Legislative Drafting Blog
Codification was predominantly regarded as a radical reform in form and substance and ‘reform’ is one of the core features of continental European codification that Weiss has identified. The element o...
8641 hits
Contract Laws Blog
Does the law of sales applicable to contract for supply of software? Assume a government authority has bought a software from a software company. A defect in the software led to massive loss of money....
13654 hits
Labor and Employment Blog
  የዚህ አጭር ጽሑፍ ዓላማ የሲቪል አቪዬሽን ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማና የፌዴራል ፖሊስ የእስር ዕርምጃ ተከትሎ በተለያዩ ሚዲያዎች በመንግሥት በኩል በተወሰዱት ዕርምጃዎች ዙሪያ እየቀረቡ ያሉ ሕግ ነክ አስተያየቶች ውይይቶች፣ ሰሞነኛ ክርክሮችንና ተያያዥ ነጥቦች መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ ውስጥ የመንግሥት ሠራተኞች...
10876 hits

Top Blog Posts

Taxation Blog
  በዚህ ጽሑፍ ስለ ግብር ስወራ ምንነት፣ በተለያዩ የግብር ዓይነቶች ሥር የግብር ስወራ ስለሚያቋቋሙ ድርጊቶች፣ ለግብር ስወራ መነሻ ሊሆኑ ስለሚችሉ ምክንያቶች እንዲሁም የመከላከያ መንገዶቹ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡ ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ መነሻ የሆነኝ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጉምሩክና ታክስ ወንጀል ችሎት...
About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...