Latest blog posts

የኢትዮጵያና የሱዳን መንግሥታት እ.ኤ.አ. በ2013 ወንጀልን በጋራ ለመመርመር የፈረሙትን ስምምነት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትላንትናው ዕለት አፀደቀው፡፡ 

ስምምነቱን የመረመረው የምክር ቤቱ የሕግ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለፓርላማው ባቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ስምምነቱ ላይ ያካሄደው ማስተካከያ አንድ ብቻ ሲሆን፣ ይህም ስምምነቱ የተፈረመበት ቀን ተሳስቶ የተጻፈ በመሆኑ ይስተካከል የሚል ነው፡፡ 

ባቀረበውም የውሳኔ ሐሳብ ስምምነቱ የሁለቱ አገሮችን ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ከማስቻሉም በተጨማሪ ሁለቱ አገሮች በድንበር ዘለል የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር በጋራና በቅንጅት የሚሠሩበትን ማዕቀፍ የሚያመቻች ነው ብሎታል፡፡ 

ስምምነቱ 26 አንቀጾች ያሉት ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል አንዱ ወንጀል የፈጸመ የአንድ አገር ዜጋ ወይም ሕጋዊ ሰውነት ያለው አካል በሌላኛው አገር እንደሚኖር ከተጠረጠረ በጠያቂው አገር ጥያቄ አቅራቢነት የምርመራ ሥራውን ማገዝ ይገኝበታል፡፡ 

በዚህም መሠረት የፍርድ ሰነዶችን ለመለዋወጥ፣ ብርበራ ለማድረግና ለመያዝ፣ መረጃዎችንና ለማስረጃነት የሚያገለግሉ ዕቃዎችን ለመለዋወጥ፣ ዋናና የተረጋገጡ ቅጂ የባንክ፣ የገንዘብ፣ የድርጅትና የንግድ ሰነዶችን መለዋወጥ የስምምነቱ አካል ነው፡፡ 

የተጠርጣሪ ግለሰቦችን ግንኙነት መጥለፍ፣ በወንጀል ሒደት ውስጥ ሠርጎ በመግባት መረጃዎችን የማሰባሰብ ኃላፊነትም በስምምነቱ ተካቷል፡፡ 


Editors Pick

Legislative Drafting Blog
Codification was predominantly regarded as a radical reform in form and substance and ‘reform’ is one of the core features of continental European codification that Weiss has identified. The element o...
8631 hits
Taxation Blog
INTRODUCTION Taxation is as old as history of early state formation. As tax remains essential source of public finance, states used to collect taxes for public funding. Apart from its extant condemnat...
22576 hits
Taxation Blog
The Ethiopian law of tax enforcement experienced a drastic change following the tax reforms of the 2002. Introduction of self-executing tax enforcement mechanisms was among the grand shifts in the cou...
14278 hits
Arbitration Blog
  ግልግል በፍትሐብሔር ሕጋችን እውቅና ከተሰጣቸው የሙግት መፍቻ ዘዴዎች አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ተከራካሪዎችም ጉዳያቸውን ወደ ግልግል የሚወስዱት በመካከላቸው በሕግ ፊት የሚጸና የግልግል ስምምነት እስካለ ድረስ ብቻ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ በግልግል ሂደት መብታቸው የሚነካ ሦስተኛ ወገኖች ምን ዓይነት መፍትሔ ሊያገኙ...
16265 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...