Latest blog posts

በቅርቡ በቡድን ተደፍራ ህይወቷ ያለፈው የሃና ላላንጎ የምርመራ መዝገብ ባለመጠናቀቁ ፖሊስ ምርመራውን በ14 ቀን ውስጥ እንዲያጠናቅቅ የቂርቆስ የመጀምሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራተኛ ምድብ የወንጀል ችሎት ትእዛዝ አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ ትእዛዙን ያስተላለፈው ዛሬ በዋለው ችሎት ፖሊስ ምርመራውን ለማካሄድ ተጨማሪ ጊዜ በመጠየቁ ነው።

የዛሬው ቀጠሮም በዝግ ችሎት ነው የታየው።

የቂርቆስ ምድብ ችሎት የመጀምሪያ ፍርድ ቤት ለፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት እንደተናገረው፥ ቸሎቱን በዝግ ማካሄድ ያስፈለገው በአሁኑ ጊዜ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ጉዳዩን አስመልክቶ የሚያወጡት መረጃ የምርመራ ስራው ላይ እንቅፋት እየሆነ በመምጣቱ ነው።

በተለይም አንዳንድ የውጭ መገናኛ በዙሃን ጉዳዩን አስመልክቶ የሚያቀርቡት ዘገባ በፍርድ ቤቱ ስራ የመግባት ያህል እየሆነ በመምጣቱ ነው የሚለውም ተጠቅሷል።

ከዚህ በተጨማሪም ለተጠርጣሪዎቹ ደህንነት ሲባልና የተፈጸመው ወንጀል ሰቅጣጭና አስከፊ በመሆኑ ችሎቱ በዝግ እንዲታይ ካደረጉ ምክንያቶች ውስጥ ተጠቃሾች ናቸው።

ፍርድ ቤቱ ህዳር 10 ቀን በዋለው ችሎት ፖሊስ መረጃውን አጠናቆ ለዛሬ እንዲቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።

ምርመራውን እያከናወነ ያለው ፖሊስ እስካሁን ባለው ሂደት የህክምና ውጤቱ የተጠናቀቀ ሲሆን የሰው ማስረጃዎችና የአስክሬን ምርመራ ውጤት አልተጠናቀቀም ብሏል።

በዚህም መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቂርቆስ ምድብ አራተኛ የወንጀል ችሎት የፖሊስን ጥያቄ በመቀበል ምርመራውን በተጨማሪ 14 ቀን ውስጥ አጠናቆ እንዲቀርብ ትእዛዝ አስተላልፏል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ፍርድ ቤቱ ማንኛውም የመገናኛ ብዙሃን ለምርመራ ሂደቱ እንቅፋት በሚሆን ደረጃ ዘገባዎችን ከመዘገብ እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርቧል።


Editors Pick

Taxation Blog
  (‘ደረሰኝ የማይሰጥ ከሆነ አይክፈሉ') ደረሰኝ  ምን ማለት ነው? የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 19፣120 እና 131(1)(ለ) እንዲሁም የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀጽ 82 ላይ የተደነገጉ ድንጋጌዎችን ጣምራዊ ንባብ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸው ሕጎች  መሠረት በ...
15508 hits
Constitutional Law Blog
  መግቢያ ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ 6ተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ የፌደራል መንግሥቱ ማራዘሙን ተከትሎ የትግራይ ክልላዊ ብሔራዊ መንግሥት ምርጫውን በክልሉ ለማካሔድ በመወሰን የምርጫ ቦርድ በማቋቋም ምርጫውን ለማድረግ አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን ዝግጅት በማድረጉ ሲሆን የትግራይ ክልል መንግሥት ምርጫውን ማድረግ ይችላል ...
3996 hits
Criminal Law Blog
1.  Introduction Distinct from conventional crimes, “organized crime” involves the commission of series crimes by criminal groups. The offences range from the traditional piracy and slave trade to the...
8545 hits
About the Law Blog
    በአንጌሳ ኢቲቻ የተጻፈውን ‹‹ችሎት መድፈር፡- ሕጉና የአሠራር ግድፈቶች›› የሚለውን ሳነብ እ.አ.አ በታኅሣስ 2013 በተመሳሳይ ርዕስ የጻፍኩትን ለአንባብያን ለማካፈል ወደድኩ፡፡ በዚህ ጽሑፌ ፍርድ ቤት መድፈር ምን ማለት ነው? የኢትዮጵያ ሕግ ስለ ፍርድ ቤት መድፈር ምን ይላል? የሕጉ ዓለማስ ምንድነው፣ የወ...
8266 hits

Top Blog Posts

Taxation Blog
  በዚህ ጽሑፍ ስለ ግብር ስወራ ምንነት፣ በተለያዩ የግብር ዓይነቶች ሥር የግብር ስወራ ስለሚያቋቋሙ ድርጊቶች፣ ለግብር ስወራ መነሻ ሊሆኑ ስለሚችሉ ምክንያቶች እንዲሁም የመከላከያ መንገዶቹ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡ ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ መነሻ የሆነኝ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጉምሩክና ታክስ ወንጀል ችሎት...
About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...