Latest Blog posts
Editors Pick
Latest documents
Education and Training Policy of Ethiopia - Amharic version - 2023 7263 Downloads - policies and strategies | 7.6 MB | |
The Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration - the Extent of Party Autonomy 218 Downloads - Arbitration Law | 635.59 KB | |
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25 9026 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 10.72 MB | |
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ እይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ FEATURED 408 Downloads - Criminal Law | 317.19 KB | |
Federal Supreme Court Cassation Decisions - Table of content Volume 1-25 10533 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 6.57 MB |
- Details
- Category: Legal News - የሕግ ዜናዎች
በሽብርተኝነት ወንጀል የተጠረጠሩት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ዋስትና ተከለከሉ
የአንድነት፣ የአረናና የሰማያዊ ፓርቲዎች አመራሮች ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ስለሺ፣ የሺዋስ አሰፋና አብርሃ ደስታን ጨምሮ በሽብርተኝነት የተከሰሱ አሥር ተጠርጣሪዎች የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡
የፌዴራል ከፍተኛ ዓቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የመሠረተውን የሽብርተኝነት ክስ እየመረመረው የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት፣ ኅዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት ጥያቄ ላይ ብይን ሰጥቷል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 19 (6) ማለትም ‹‹የተያዙ ሰዎች በዋስ የመፈታት መብት አላቸው›› በማለት በተደነገገው መሠረት የጠየቁት መብት፣ ትክክለኛ ጥያቄ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አረጋግጦ፣ ነገር ግን በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 20 (5) ‹‹በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ የቀረበ እንደሆነ፣ ፍርድ ቤቱ ክሱን ሰምቶ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ተከሳሹ በማረፊያ ቤት ይቆያል፤›› በሚል መደንገጉን በመጥቀስ፣ እነሱም የጠየቁት የዋስትና መብት ተቀባይነት እንደሌለው በብይኑ ገልጿል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ክሱን እንደሚቃወሙ ለፍርድ ቤቱ በማሳወቃቸውና ሰባተኛው ተከሳሽ ደግሞ ዓቃቤ ሕግ ከመሠረተበት ክስ ጋር ሊደርሰው የሚገባ የሰነድ ማስረጃ (የክስ መግለጫ) እንዳልደረሰው በማመልከቱ፣ ታኅሳስ 17 ቀን 2007 ዓ.ም. ዓቃቤ ሕግ ያልተሟላውን የክስ መግለጫ አሟልቶ እንዲያቀርብና ተጠርጣሪዎቹም መቃወሚያ የሚያቀርቡበትን ቀን ለመወሰን ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡