Latest Blog posts
Editors Pick
Latest documents
Education and Training Policy of Ethiopia - Amharic version - 2023 7262 Downloads - policies and strategies | 7.6 MB | |
The Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration - the Extent of Party Autonomy 218 Downloads - Arbitration Law | 635.59 KB | |
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25 8982 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 10.72 MB | |
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ እይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ FEATURED 408 Downloads - Criminal Law | 317.19 KB | |
Federal Supreme Court Cassation Decisions - Table of content Volume 1-25 10517 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 6.57 MB |
- Details
- Category: Legal News - የሕግ ዜናዎች
የቀድሞ የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ በሶስት አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ
ፍትህ ጋዜጣን እያሳተመ ሲያሰራጭ የነበረው ማስተዋል የህትመትና ማስታወቂያ ስራ ድርጅት በ10 ሺህ ብር ተቀጥቷል። የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 9ኛ የወንጀል ችሎት ተመስገን ጥፋተኛ ነህ የተባለባቸውን ሶስት ክሶች በአንድ ሀሳብ ቅጣቱ ተፈፃሚ ይሁን ብሎ መፍረዱን ተከትሎ ነው በሶስት አመት ፅኑ እስራት የተቀጣው።
አቃቤ ህግ ከዚህ ቀደም የወንጀል ህግ 257 ጠቅሶ በመገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት ተግባር ሁለት ክሶች እንዲሁም የመንግስትን ስም ማጥፋት በሚሉ በጥቅሉ በሶስት ክሶች ጥፋተኛ መባሉ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ ሶስቱም በአንድ ሀሳብ የተገለፀ በመሆኑ በወንጀል ህግ 257 ብቻ ይቀጣ ብሎ በመፍረዱ ነው ቅጣቱ ሶስት አመት ሊሆን የቻለው።
የዚህ የወንጀል ህጉ 257 መነሻ ቅጣቱ ቀላል እስራት የሚል ሲሆን፥ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በፍትህ ጋዜጣ ለንባብ ያበቃቸው የተለያዩ እትሞች መላውን ህብረተሰብና ይልቁንም ወጣቱን ለአመፅ የሚያነሳሱ በመሆኑ አመፅ ቢሆን ሊደርስ የሚችለውን ኪሳራ ከግምት በማስገባት ቀላል እስራት የሚለው ፅኑ እስራት ወደሚለው ተቀይሯል።
ከሳሽ አቃቤ ህግም ሆነ ተከሳሹ ተመስገን ደሳለኝ ምንም አይነት የቅጣት ማቅለያም ሆነ ማክበጃ አላቀረቡም።
ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ በአቃቤ ህግ የቀረበበት የወንጀል ሪከርድ ባለመኖሩ የቀደመ ፀባዩ መልካም እንደሆነ በመገመት አንድ የቅጣት ማቅለያ ይዞለት በሶስት አመት ፅኑ እስራት ቀጥቶታል።
አሳታሚው ማስተዋል የተሰኘው ድርጅቱ የተመሰረተበት ክስ በድፍኑ ሲታይ የ50 ሺህ ብር ቅጣት እና ለዚህ ህትመት ስራ ያዋለው አጠቃላይ ንብረት ይወረስ የሚል ነው በህጉ የሰፈረው።
ነገር ግን አቃቤ ህግ ድርጅቱ ያገኘውን ገንዘብ ጠቅሶ ለፍርድ ቤቱ ባለማቅረቡ ፍርድ ቤቱ ድርጅቱ ያቀረበውን የቅጣት ማቅለያ ከግምት ውስጥ በማስገባት በ10 ሺህ ብር ቀጥቶታል።