Latest Blog posts
Editors Pick
Latest documents
Education and Training Policy of Ethiopia - Amharic version - 2023 7249 Downloads - policies and strategies | 7.6 MB | |
The Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration - the Extent of Party Autonomy 197 Downloads - Arbitration Law | 635.59 KB | |
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25 8781 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 10.72 MB | |
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ እይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ FEATURED 397 Downloads - Criminal Law | 317.19 KB | |
Federal Supreme Court Cassation Decisions - Table of content Volume 1-25 10412 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 6.57 MB |
- Details
- Category: Legal News - የሕግ ዜናዎች
በዛምቢያ 26 ኢትዮጵያውያን የአንድ ዓመት እስራት ተፈረደባቸው
አስፈላጊውን የስደተኞች ሥነ ሥርዓት ሳያሟሉ ወደ አገሬ ገብተዋል በማለት ደቡብ አፍሪካዊቷ አገር ዛምቢያ በ26 ኢትዮጵያውያን ላይ የአንድ ዓመት እስራት፣ ከባድ የጉልበት ሥራና 4,500 የዛምቢያ የገንዘብ (ኩዋቻ) ቅጣት አስተላለፈች፡፡
ታይምስ ኦፍ ዛምቢያ በድረ ገጹ የዛምቢያ ስደተኞች ጉዳይ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ናማቲ ሺንካን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በ26 ኢትዮጵያውያን ላይ ውሳኔው የተላለፈው የስደተኞች ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሳይቀርቡና አስፈላጊውን ሥነ ሥርዓት ሳያሟሉ ወደ አገሪቱ በመግባታቸው ነው፡፡
በኢትዮጵያውያኑ ላይ ይህ የቅጣት ውሳኔ የተላለፈው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሲሆን፣ ሕገወጥ የተባሉት ስደተኞች በዛምቢያ የስደተኞች ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ደግሞ ነሐሴ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. ነበር፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ወደ አገሪቱ ሊገቡ የነበረው በሁለት ተሽከርካሪዎች ተጭነው የነበረ ቢሆንም፣ ከየት እንደተነሱና ወዴት እየተጓዙ እንደነበር አልተገለጸም፡፡
በተመሳሳይ ዜና በዛምቢያ ርዕሰ መዲና ሉሳካ የሚገኘው የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ፣ በሕገወጥ መንገድ ወደ አገሪቱ ገብተዋል ያላቸውን ሌሎች 24 ኢትዮጵያውያንን ከአገሪቱ ማባረሩም ተዘግቧል፡፡
እነዚህ ከአገሪቱ የተባረሩት 24 ኢትዮጵያውያን ሉሳካ ከሚገኘው የኬኔት ካውንዳ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል በዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ እንዳደረገላቸውም ተጠቅሷል፡፡ ወደ አገራቸው ይመለሱ ወይም ወደ ሌላ አገር ይጓዙ በዘገባው ተብራርቶ አልቀረበም፡፡