Latest blog posts

-ፍርድ ቤቱ በድጋሚ ቢፈጸም ተገቢ ዕርምጃ እወስዳለሁ አለ

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ክስ ከተመሠረተባቸው ጋዜጠኞችና ጦማሪያን መካከል፣ ሴት ጦማሪያን ማኅሌት ፋንታሁንና ኤዶም ካሣዬ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እየደረሰባቸው ያለውን በደል በሚመለከት ለፍርድ ቤት ያቀረቡትን አቤቱታ፣ ማረሚያ ቤቱ ጥቅምት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. አስተባበለ፡፡

የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት አስተዳደርን ወክለው ፍርድ ቤት የቀረቡትና በማረሚያ ቤቱ የሴት ታራሚዎች መምርያ ኃላፊ ሱፐር ኢንቴንደንት አየለች አሰፋ ለፍርድ ቤቱ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ቀደም ባለው ቀጠሮ ማረሚያ ቤቱ ጦማሪያኑ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ቀርቦ እንዲያስረዳ ታዞ ለምን እንዳልቀረበ ተጠይቀው፣ ‹‹የደረሰን ነገር የለም፣ ሁለተኛው ትዕዛዝ ስለደረሰን መጥቻለሁ፤›› ካሉ በኋላ፣ ጦማሪያኑ እንደ ማንኛውም ታራሚ በአግባቡ እንደተያዙ በማስረዳት የጦማሪያኑን አቤቱታ አስተባብለዋል፡፡

የጦማሪያኑ ጠበቆች ለፍርድ ቤቱ ያለፈው ነገር አልፏል ቢባል እንኳን መብታቸው ወደፊት ሊከበርላቸው ይገባል ብለዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ እንደ ማንኛውም ታራሚ በማረሚያ ቤቱ ደንብ መሠረት ለመስተናገድ ጥያቄ ማቅረባቸውን ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል፡፡ ‹‹አሸባሪዎች›› ተብለው ከማንኛውም እስረኛ ጋር እንደማይገናኙና ብዙ ጠያቂዎቻቸው ‹‹ስማችሁ አልተመዘገበም›› ተብለው ሳይጠይቋቸው መመለሳቸውን አስረድተዋል፡፡ ቤተሰቦቻቸውም ቢሆኑ ከ6፡10 ሰዓት እስከ 6፡20 ሰዓት ብቻ ለአሥር ደቂቃ እንደሚያነጋግሯቸው በማስረዳት፣ በቀጣይ እንዲስተካከልላቸው ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ እንደ ማንኛውም የማረሚያ ቤት ታራሚ እንዲያዙ፣ ከዚህ በኋላ ሌላ አቤቱታ የሚቀርብ ከሆነ ፍርድ ቤቱ በሚቀርብለት አቤቱታ መሠረት ማጣሪያ አድርጐ ተገቢ ዕርምጃ እንደሚወስድ ተወካይዋን አስጠንቅቋል፡፡

በዕለቱ እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ያልተሰጣቸው ወንድ ጦማሪያን (በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ያሉ) የቀረቡ ሲሆን፣ ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ እነሱም የአያያዝ ችግር እንዳለባቸው አመልክተዋል፡፡ 

በአንድ ዓይነትና በአንድ መዝገብ የተጠቃለለ ክስ የተመሠረተባቸው በመሆኑ ተገናኝተው መወያየት ቢኖርባቸውም፣ እንደማይገናኙ ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል እንደ ማንኛውም ታራሚ መጻሕፍት እንዲገባላቸው ቢጠይቁም፣ ከሃይማኖት መጻሕፍት በስተቀር እንደማይፈቀድና ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው እየተጣሰ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በዕለቱ የተያዘው ቀጠሮ የሴት ጦማሪዎቹ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ምላሽ እንዲሰጥ መሆኑን በማስታወስ፣ እነሱም ችግር አለ የሚሉ ከሆነ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችሉ በማስታወቅ፣ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡   


Editors Pick

Succession Law Blog
   መግቢያ የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ ኑዛዜ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሰጠው ትርጉም ባይኖርም አንድ ኑዛዜ ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች ምን ምን እንደሆኑ በዝርዝር የሚያስቀምጡ የሕግ ድንጋጌዎችን ከፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 857 እስከ 908 ተደንግጎ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ ጽሁፍ ኑዛዜ በምን ...
5944 hits
International Law Blog
  World Trade Organization (WTO) was established with the main objective of liberalizing multilateral trade, based on the belief that the liberalization of trade brings multiple of benefits to the wor...
16116 hits
Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
በተለምዶ የሕግ ባለሙያዎች በንግዱ ዘርፍ ለሚንቀሳቀሱት ተወዳዳሪ ኃይሎች የተጋለጡ አልነበሩም፡፡ ይህ በሲቪል ሎው የሕግ ሥርዓት ተከታይ ሃገራት በአድቮኬቶችና ላቲን ኖታሪዎች እንዲሁም በኮመን ሎው የሕግ ሥርዓት ተከታይ ሃገራት በባሪስተሮች፣ ሎሊሳይቶሮች እና ኮንቬሮች መካከል ተመሳሳይ እውነታ ነበር፡፡ በእነዚህ በሁለ...
12891 hits
Human Rights, Public Policy and Law Blog
1.      Introduction This essay examines the normative contemporary constitutional law question ‘how constitutionality of laws is controlled?’ under Ethiopian and Nigerian Federal Systems. In constitu...
16740 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...