Latest blog posts

ተጠርጣሪው በሌላ ወንጀል 12 ዓመታት ተፈርዶባቸው ሲፈለጉ እንደነበር ተገልጿል

በደቡብ ክልል ሐዋሳ ከተማ ውስጥ መስከረም 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት አካባቢ ዳንኤል ዋለልኝ የተባሉ የሕግ ባለሙያን በጥይት ገድለው መሰወራቸው የተገለጸው ባለሀብት፣ ጥቅምት 8 ቀን 2007 ዓ.ም. አዲስ አበባ ከተማ ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታወቀ፡፡

ባለሀብቱ አቶ ታምራት ሙሉ መሆናቸውንና በሐዋሳ ከተማ ከሚገኙ ሆቴሎች መካከል አንዱ የሆነው ብሉ ናይል ሆቴልና ኢቪኒንግ ስታር ሆቴል ባለቤት መሆናቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ተጠርጣሪው ባለሀብት አቶ ታምራት፣ በክልሉ ታዋቂ ጠበቃ መሆናቸው የተገለጸውን አቶ ዳንኤልን ገድለዋል ከተባሉ በኋላ ተሰውረው የከረሙት ለ12 ቀናት ብቻ መሆኑን ምንጮች ሲጠቁሙ፣ ጥቅምት 8 ቀን 2007 ዓ.ም. አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ውለው፣ ጥቅምት 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ወደ ደቡብ ክልል መወሰዳቸውን ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ 

በከተማው ውስጥ ቢቆዩ ለደኅንነታቸው ያሰጋል በሚል፣ ከሐዋሳ ከተማ በ45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ይርጋለም ከተማ አካባቢ በሚገኘው የደቡብ ፖሊስ ማሠልጠኛ አፖስቶ ኮሌጅ ተወስደው መታሰራቸውም ተጠቁሟል፡፡ 

ተጠርጣሪው በጠበቃው ላይ ግድያውን የፈጸሙበትን ምክንያት ምንጮች እንዳስረዱት፣ ‹‹መልጌ መርሳ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ›› በሚባለው ድርጅታቸው ሥር ከሚገኙት ‹‹ብሉ ናይል ሆቴልና ኢቪኒንግ ስታር ሆቴል›› መካከል ‹‹ኢቪኒንግ ስታር ሆቴል›› የተባለውን ሆቴል፣ ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ መሆኑ ለተገለጸው አቶ መሐመድ ሰዒድ ለሚባሉ ግለሰብ ይሸጣሉ፡፡ ሁለቱ ወገኖች የሆቴሉን ሽያጭ በሚመለከት በተዋዋሉት መሠረት መፈጸም ባለመቻላቸው፣ አቶ መሐመድ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ የፍትሐ ብሔር ክስ ያቀርባሉ፡፡ 

አቶ መሐመድ ለአቶ ታምራት መጥሪያ ይዘው በአድራሻቸው ሲሄዱ ሊያገኟቸው ባለመቻላቸው ወደ ፍርድ ቤት ይመለሳሉ፡፡ ‹‹አቶ ታምራትን ላገኛቸው ስላልቻልኩኝ በሌሉበት ይታይልኝ፤›› በማለትም ያመለክታሉ፡፡ የአቶ ታምራት ጠበቃ ነኝ ያሉ የሕግ ባለሙያ ቀርበው መቃወሚያ ማቅረባቸውንም ምንጮች ገልጸዋል፡፡

የአቶ መሐመድ ወኪል የነበሩት ሟች አቶ ዳንኤል፣ አቶ ታምራት በሌላ ወንጀል ተከሰው 12 ዓመታት የተፈረደባቸውና ጠፍተው በመፈለግ ላይ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳታቸውንም ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ተጠርጣሪውን ወክለው እንደቀረቡ የሚናገሩትን ጠበቃ ባለቤቱ በሌለበት ውክልና መስጠት ስለማይቻል፣ ተወካይ ነኝ ብለው ለክርክር መቅረባቸው ሕጋዊ መሠረት እንደሌለው ለፍርድ ቤቱ ያስረዳሉ፡፡ ፍርድ ቤቱ የሟቹን ጠበቃ መከራከሪያ ነጥብ በመቀበል፣ የተጠርጣሪውን ጠበቃ ክርክር ውድቅ ማድረጉንም አክለዋል፡፡ 

ተጠርጣሪው ባለሀብት አቶ ታምራት ሙሉ ቀደም ባሉት ወራትም በደረቅ ቼክ ምክንያት ክስ ተመሥርቶባቸው፣ ሟች ጠበቃ ተከራክረው እንዳሸነፏቸውና መጨረሻ ላይ ከከሳሽ ጋር በሽምግልና ለመጨረስ ለመስከረም 30 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጠሮ የያዙ ቢሆንም፣ መስከረም 27 ቀን 2007 ዓ.ም. አቶ ዳንኤል ዋለልኝን በመግደል መሰወራቸውን ምንጮቹ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የሟች ረዳት ጠበቃ ናቸው የተባሉት አቶ ዳግማዊ አሰፋ በወቅቱ አንገታቸው አካባቢ በጥይት ተመትተው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በኮሪያ ሆስፒታል ቀዶ ሕክምና እንደተደረገላቸውና የአቶ ዳንኤል የቀብር ሥርዓት በሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መፈጸሙን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ተጠርጣሪው አቶ ታምራት 12 ዓመታት ተፈርዶባቸው ነበር የተባለው ከታክስና ከግብር ጋር በተገናኘ መሆኑንም ምንጮች አስታውሰዋል፡፡ 


Editors Pick

Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
በተለምዶ የሕግ ባለሙያዎች በንግዱ ዘርፍ ለሚንቀሳቀሱት ተወዳዳሪ ኃይሎች የተጋለጡ አልነበሩም፡፡ ይህ በሲቪል ሎው የሕግ ሥርዓት ተከታይ ሃገራት በአድቮኬቶችና ላቲን ኖታሪዎች እንዲሁም በኮመን ሎው የሕግ ሥርዓት ተከታይ ሃገራት በባሪስተሮች፣ ሎሊሳይቶሮች እና ኮንቬሮች መካከል ተመሳሳይ እውነታ ነበር፡፡ በእነዚህ በሁለ...
12891 hits
Criminal Law Blog
  1.  የመያዝና የመቀጣት እድል፤ ማጅራት መቺዎችን እና ቤት ሰርሳሪዎችን ከተማን በማጽዳት እንዋጋቸው፤ ወይኖን ግረፈው ኳሊ እንዲሰማህ እና ሌሎችም አሳቦች 1.1 አጠቃላይ ማስታወሻ ለአንባቢ፤ ይህ በወንጀል ኤኮኖሚክስ ዙሪያ የጻፍኩት ሁለተኛው ጽሑፌ ነው፡፡ የመጀመሪያውን ክፍል እዚህ ማግኘት ይቻላሉ:: አሳቦቼን ለ...
12188 hits
About the Law Blog
  በተደራጀ እና በብሔራዊ ሕግ ዕውቅና አይሰጣቸው እንጂ በኢትዮጵያ የሸሪኣ ሕግን መሠረት በማድረግ ውሳኔ መስጠት የቅርብ ታሪክ አይደለም፡፡ በታወቀ ሁኔታ እና በመንግሥት ድጋፍ የሸሪኣ ፍርድ ቤቶች የተቋቋሙት ግን በ1934 ዓ.ም. ነው፡፡ ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሕጉ ከሁለት ዓመት በኋላ ተሻሻለ፡፡ ቀጥሎም አገሪቱ በፌደ...
11774 hits
Arbitration Blog
  ማሪዮን ጆንስ፣ ማሪያ ሻራፖቫ፣ ክላውዲያ ፔከንስታይ እና ላንስ አርምስትሮንግን የሚያመሳስላቸው አንዱ በስፖርቱ ዓለም ገናና ስም የነበራቸው መሆኑ ነው፡፡ ማሪዮን ጆንስ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ናት፡፡ አርምስትሮንግ ደግሞ በብስክሌት ግልቢያ የሚያህለው አልነበረም፡፡ ማሪዮን ጆንስ አጭሩን ርቀት በሚያስገር...
11337 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...