Latest blog posts

-አንድ ጋዜጠኛና አንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባልን ጨምሮ በርካቶች መታሰራቸው ተጠቁሟል ‹‹አብዛኛዎቹ ተለቀው ለግጭቱ ምክንያት የሆኑት ብቻ ታስረዋል›› ፖሊሶች

ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ለጁምዓ (እለተ ዓርብ) ፀሎት መርካቶ በሚገኘው ታላቁ የአንዋር መስጊድ ተገኝተው የነበሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች ባሰሙት ጠንከር ያለ ተቃውሞ ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት

በመፈጠሩ፣ የተጎዱ የዕምነቱ ተከታዮች፣ የተለያዩ ግለሰቦችና የፖሊስ አባላት መኖራቸው ተገለጸ፡፡ በግጭቱ ምክንያት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የዕምነቱ ተከታዮችና በአካባቢው በግርግሩ ወቅት የነበሩ ሰዎች በፖሊስ ታስረው አንድ ቀን ካደሩ በኋላ፣ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ሐምሌ 12 ቀን 2006 ዓ.ም. ቀርበው ለተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ታውቋል፡፡ 

ሐምሌ 4 ቀን 2006 ዓ.ም. በተለይ ሴት የዕምነቱ ተከታዮች ከድምፅ ያልዘለለ ተቃውሞ ማሰማታቸው የተገለጸ ቢሆንም፣ የአሁኑ ከበድ ያለ እንደነበር ተገልጿል፡፡ ግጭቱ በተፈጠረበት ወቅት በቦታው የጋዜጠኝነት ሥራዋን ስትሠራ ነበረች የተባለችው የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድና ለግል ጉዳይዋ መርካቶ አካባቢ እንደነበረች በፓርቲው አመራሮች የተገለጸው የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ወ/ት ወይንሸት ሞላን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ወደተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች መወሰዳቸው መገለጹ ይታወሳል፡፡ 

በተለይ መሀል መርካቶ በሚገኘው አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ ኮልፌ ፖሊስ ማሠልጠኛ፣ ማዕከላዊና ኢትዮጵያ ትቅደም ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ በርካታ ሰዎች ታስረው እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ 

ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን ተጠርጣሪዎች በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት፣ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና በተለያዩ ፍርድ ቤቶች በማቅረብ ለተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ታውቋል፡፡ 

በወቅቱ በነበረው ግጭት የተፈነከቱ፣ የእጃቸው ጣቶች የተሰበሩ፣ የሚያነክሱና ራሳቸውን ስተው የወደቁ እንደነበሩ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ገልጸው፣ የፖሊስ ተሽከርካሪዎችና የቀይ መስቀል አምቡላንሶች ወደ ሆስፒታል ሲያመላልሱ መታየታቸውን ጠቁመዋል፡፡ 

ታሳሪዎቹ ‹‹ፍትሕ ናፈቀን፣ ፍትሕ ይከበር፣ የዕምነት ነፃነታችን ይከበር፣ የታሰሩ ይፈቱ፣ መንግሥት በዕምነታችን ጣልቃ አይግባብን፣ የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ይፈቱ…›› እና ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት በአንዋር መስጊድ ግቢ ውስጥ በማሰማት ላይ እያሉ፣ ከማን እንደተወረወረ ባልታወቀ ድንጋይ ፖሊሶች መጎዳታቸውን በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ 

ለሥራ ወጥተው ምንም ሳያደርጉ ልጆቻቸው የት እንደደረሱ ማወቅ ያልቻሉ እናቶች፣ ቤተሰቦችና የሚመለከታቸው ወገኖች በየፖሊስ ጣቢያው ሄደው ሲጠይቁ በቂ ምላሽ አለማግኘታቸውን የገለጹ ቢሆንም፣ አንዳንዶቹ ወላጆች ደግሞ የልጆቻቸውን ስም እየተናገሩ የታሰሩበትን ፖሊስ ጣቢያ ለማወቅ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ሐምሌ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. በድጋሚ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡና ምናልባትም በተለይ ሳያስቡትና በወጡበት ችግሩ የገጠማቸው በዋስትና ይለቀቃሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል፡፡ 

በግጭቱ ወቅት በቁጥጥር ሥር ስለዋሉት ሰዎች ብዛትና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ፣ እንዲሁም የግጭቱ ዋነኛ መነሻ ምን እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና የፌዴራል ፖሊስ ምላሽ እንዲሰጡ የተጠየቁ ቢሆንም፣ ማብራሪያውን ለማግኘት አልተሳካም፡፡ ነገር ግን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፖሊስ አባላት እንደገለጹት፣ በግጭቱ ወቅት ቁጥራቸው በዛ ያሉ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር፡፡ ሐምሌ 14 ቀን 2006 ዓ.ም. ከበላይ ኃላፊዎች በመጣ ትዕዛዝ ሁሉም ማለት በሚባል ደረጃ ተለቀዋል፡፡ አሁን በቁጥጥር ሥር ሆነው በምርመራ ላይ የሚገኙት ለረብሻው ምክንያት የሆኑና በተደጋጋሚ ችግር ሲፈጥሩ የተገኙ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ በደንብ በመደራጀት ሕዝብ ሰላም እንዳያገኝ በተደጋጋሚ ግጭት ሲያስነሱ የተገኙ ከ14 በላይ ግለሰቦች በተፋጠነ ችሎት እየቀረቡ መሆኑንም አክለዋል፡፡ 

በግጭቱ ወቅት ፖሊሶች ሞተዋልና ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል ስለመባሉም ሐሰት መሆኑን ተናግረው፣ ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉ ግን አልካዱም፡፡ ፖሊስ ምርመራውን ጨርሶ ለዓቃቤ ሕግ ካስረከበና የሚከሰሱ ከሆነም የፍርድ ቤት ጉዳያቸው ሲጠናቀቅ፣ የግለሰቦቹን የወንጀል ድርጊትና እንቅስቃሴ ከነማስረጃው ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡ 


Editors Pick

Constitutional Law Blog
አሁን አሁን በተለያዩ የሃገራችን ክልሎች በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ ዙርያ በሚገኙ የኦሮሚያ ልዩ ከተሞች ላይ ከዕለት ወደዕለት በዜጎች የመዘዋወር መብት፤ንብረት የማፍራት፤ የእኩልነት እና ፍትህ የማግኘት ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በሕግ ማስከበር ሰበብ ሲጣሱ ማዬት የዕለት ተዕለት ተግባራዊ ኩነት እየሆነ መጥቷ...
10124 hits
Arbitration Blog
I say 1958 was a year the international arbitration world took a remarkable move. The UN and other parties interested in international arbitration embarked an international convention to recognize and...
12989 hits
Taxation Blog
የሂሳብ መዝገብ ስለመያዝ የሂሳብ መዝገብ መያዝ ለመልካም የንግድ አሠራር ሥርዓት በጣም ጠቃሚና ከማንኛውም ግብር ከፋይ የሚጠበቅ፤ የንግድ አሠራር ሥርዓቱም የሚጠይቀው በመሆኑ በንግድ ሥራ ውስጥ ያለ አብይ ተግባር ሲሆን ለግብር አሰባሰብና አስተዳደር አመቺ እንዲሆን ከደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋዮች ማለትም የቁርጥ ግብር ከ...
22975 hits
About the Law Blog
    የግብርና እድገትና የመንግስት ሚና ግብርና የሃገራችን ወሳኝ የኤኮኖሚ ዘርፍ ነው። ምጣኔ ሃብት ምሁሮች እንደሚሉት፥ በቅጥርና አገራዊ ምርት የግብርናው ድርሻ እንዲቀንስ (በሌሎች ዘርፎች እንዲተካ)፥ ግብርናው በፍጥነት ማደግ አለበት። ለማነስ፤ በፍጥነት ማደግ። የግብርና እድገት ምን ይጠይቃል? የመስኖ መሰረተልማ...
9675 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...