Latest Blog posts
Editors Pick
Latest documents
Education and Training Policy of Ethiopia - Amharic version - 2023 7249 Downloads - policies and strategies | 7.6 MB | |
The Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration - the Extent of Party Autonomy 197 Downloads - Arbitration Law | 635.59 KB | |
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25 8781 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 10.72 MB | |
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ እይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ FEATURED 399 Downloads - Criminal Law | 317.19 KB | |
Federal Supreme Court Cassation Decisions - Table of content Volume 1-25 10412 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 6.57 MB |
- Details
- Category: Legal News - የሕግ ዜናዎች
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ለባለጉዳዮችና ለመላው ሕብረተሰብ በቀላሉ መረጃ ለመስጠት ያስገነባው 992 የነፃ የጥሪ ማዕከል በይፋ ሥራ ጀመረ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ለባለጉዳዮችና ለመላው ሕብረተሰብ በቀላሉ መረጃ ለመስጠት ያስገነባው 992 የነፃ የጥሪ ማዕከል በይፋ ሥራ ጀመረ፡፡
ከጥር/2006 ዓ.ም. ጀምሮ በሙከራ ላይ ቆይቶ ሰኔ 13/2006 ዓ.ም. በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት ክቡር አቶ ተገኔ ጌታነህ በይፋ ተመርቆ ሥራ የጀመረው የነፃ የጥሪ ማዕከል የፍ/ቤቱን ተገልጋዮች ጨምሮ ለዜጐች ወቅታዊና ፈጣን መረጃ በመስጠት የላቀ አስተዋፅዖ ያበረክታል፡፡ ተገልጋዮች በፍርዱ ሂደት ያለ ጉዳያቸውም ሆነ ስለ ፍ/ቤቱ አሠራር አደረጃጀትና ተዛማጅ ጉዳዮች ወደ ነፃ የጥሪ ማዕከል ደውለው በቀላሉ መረጃ አንዲያገኙ ያግዛል፡፡ በይፋ ሥራውን የጀመረው የጥሪ ማዕከሉ ባለጉዳዮች ብቻ ሳይሆኑ ዜጎችም ጭምር የፍ/ቤቱ አገልግሎተ አሰጣጥን ጨምሮ ፍ/ቤቱን የሚመለከት ማንኛውም መረጃ በነፃ የስልክ መስመሩ ጠይቀው ምላሽ የሚያገኙበት እንደሆነም ተገልጿል፡፡
የጥሪ ማዕከሉ ከዋናው የፍ/ቤቶች የመረጃ ቋት ፣ ከድረ-ገፅና ከእያንዳንዱ የሥራ ክፍል ጋር የሚገናኝ ስለሆነ ዜጎች ከዕለታዊ ሥራቸው ሳይስተጓጎሎ መረጃ በቀላሉ የሚያገኙበት አሰራር ይፈጥራል ተብሏል፡፡
አዲሱ የጥሪ ማዕከል ከነባሩ ሰው አልባ የጥሪ ማዕከል በሚሰጠው የመረጃ አይነትና ስፋት እጅግ የተለየ ሲሆን በአንዴ 18 ሰዎችን የማስተናገድ ዓቅም እንዳለው ተገልጿል፡፡ ለበርካታ ዓመታት ሥራ ላይ የቆየው የፍ/ቤቱ ሰው አልባ የጥሪ ማዕከል ባለጉዳዮች ጉዳያቸው ለመቼ እንደተቀጠረ ለማወቅ ብቻ የሚያገለግልና በአንዴ ከሁለት ሰው በላይ የማስተናገድ ዓቅም እንዳልነበረው ታውቋል፡፡
አዲሱ የጥሪ ማዕከል በተለይ በፍትህ አካላት የሚያልፉ ሕፃናት የሕግ፣ የማህበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ምክርና ድጋፍ ለሚፈልጉ ዜጎች የተሟላ መረጃ ለመስጠት እጅግ ጠቃሚ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል፡፡
የጥሪ ማዕከሉ በይፋ ሥራ መጀመሩን ያበሰሩት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት ክቡር አቶ ተገኔ ጌታነህ እንደተናገሩት የማዕከሉ መገንባት የፌዴራል ፍ/ቤቶችን ይበልጥ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግም ሆነ ሕብረተሰቡ ስለ ፍርድ ገቤቶች የሚፈልገውን መረጃ በቀላሉ የሚያገኝበት አሰራር ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡ የጥሪ ማዕከሉ ፍ/ቤቱ ከሕበረተሰቡ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ያለውን ፋይዳ እንዲህ በማለት ይገልፁታል፡፡ ወደፊት የጥሪ ማዕከሉ በዜጎችና በፍ/ቤቶች መካከል ያለው ግንኙነት ለማጠንከርና ዜጎች በፍ/ቤቶች ላይ ያላቸውን አስተያየት ለመቀበልና ለዕቅዶች እንደ ግብአት ለመጠቀም ዕቅድ እንዳለም መግለፅ እወዳለሁ ብለዋል፡፡
የፌዴራል ፍ/ቤቶች ባለፉት ዓመታት የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ ሥርዓት መዘርጋትተችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ፍ/ቤቱ በመላ ሃገሪቱ ባሉት 23 ማዕከላት አማካኝነት ዳኝነትን በኢንተርኔት በታገዘ የርቀት የቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት አልግሎቱ ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች ተደራሽ የማድረጉ ሥራ በስፋት እየተሰራ እንደሆነ ኘሬዚዳንቱ ገልፀዋል፡፡ በዚህ ምከንያት የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ከጥቂት ዓመታት በፊት በተዘዋዋሪ ችሎት ወደ ክልሎች በመሄድ ይሰጥ የበረውን የችሎት አገልግሎት በማስቀረት የክልል ተከራካሪ ወገኖች ከዕለታዊ ስራቸውና ከአካባቢያቸው ሳይርቁ በአቀራቢያቸው አገልግሎት የሚያገኙበት ሁኔታ መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የመዝገብ አያያዝ፣ የችሎት ቀረፃና የፍ/ቤት ተገልጋዮች ዕለታዊ ቀጠሮአቸውን የሚከታተሉበት የኘላዝማ ስክሪን እና ተች ስክሪን ቴክኖሎጂዎችን በመዘርጋት የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡን ፈጣንና ዘመናዊ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን አማረ በበኩላቸው መረጃ ለመስጠት በተገነባው የጥሪ ማዕከል አንድ አስተባባሪና ስድስት የጥሪ ማዕከል ባለሙያዎችን በመቅጠር ሥራ መጀመሩን ገልፀው ዜጎች 992 በመደወል መረጃ ማግኘት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
ሰኔ 13 / 2006 ዓ.ም. በተከናወነው የጥሪ ማዕከሉ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የፌዴራልና የከልል ፍ/ቤቶች የበላይ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ለጥሪ ማዕከሉ ግንባታ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦት የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡