Latest blog posts

ሁሉም የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ሠራተኞች ናቸው

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ስድስት ሠራተኞች በሐሰተኛ መታወቂያ አካውንት በመክፈት፣ ከአንድ ግለሰብ ሒሳብ ላይ በድምሩ ከ482,000 ብር በላይ ወስደዋል በሚል ተጠርጥረው በከባድ አታላይነት የሙስና ወንጀል ተከሰሱ፡፡

የፌደራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው፣ ተጠርጣሪዎቹ አቶ ኃይለ ሚካኤል ኃይሉ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን፣ አቶ  ሱሌማን ሳኒ የውስጥ ተቆጣጣሪ፣ አቶ ተመስገን ለሚ የቅርንጫፉ ባልደረባ፣ አቶ ግርማ ወርቄ የገንዘብ ቤት ዋና ኃላፊ፣ አቶ በላይ ታዬ የደንበኞች አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ፣ እንዲሁም አቶ ሞላ አምሳሉ የደንበኞች አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ሥውር በሆነ የጥቅም ግንኙነት ተመሳጥረው የማይገባ ብልፅግና ለራሳቸው ለማግኘትና ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ፣ ከአንድ ግለሰብ ሒሳብ ላይ ድርጊቱን መፈጸማቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡

አቶ ኃይለ ሚካኤል የተባሉት ተጠርጣሪ ራሳቸው ብቻ የሚያውቁት፣ በባንኩ መመርያና ግዴታ መሠረት ሌላ ሰው ሊያውቀው የማይገባውን ወደ የኮምፒዩተር መግቢያ ፈቃድ በመጠቀም፣ አቶ ገመቹ አዳም ከተባሉ ግለሰብ ሒሳብ ላይ በተደጋጋሚ በሐሰተኛ መታወቂያ በተከፈተው አካውንት ውስጥ በድምሩ 482,495.45 ገቢ ማድረጋቸው ተጠቁሟል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ውለው ሰኔ 30  ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ እንዲነበብላቸው ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡


Editors Pick

Criminal Law Blog
1.      Introduction Globalization is easing border restrictions and increasing travel opportunities. Perpetrators use globalization to avoid prosecution and justice. This problem can be solved by cre...
5665 hits
Litigation
  የአዲስ አበባ ፍርድ ቤት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ሥልጣናቸውን የተመለከቱ የተለያዩ ክርክሮች ተነስተዋል፡፡ ዋናው ክርክር በተቋቋመበት ወቅት የተነሳው የሕገ መንግሥታዊነት ጭብጥ ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 78 እስከ 80 የዳኝነት አካሉን ሲያዋቅር በተለያዩ ደረጃዎች ያሉት የፌዴራልና የክልል ፍርድ ቤቶች እንደሚ...
10633 hits
Investment Law Blog
  One part of the economic reform programs taking place in Ethiopia is improving the country's ranking in the World Bank's Ease of Doing Business. As part of the Ease of Doing Business Project, the Et...
12561 hits
Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
የዛሬ ሳምንት "የሁለት ኢትዮጵያውያን ወግ፡ የቀድሞውና አዲሱ ኢትዮጵያዊነት በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ሊታረቅ ይችላል ወይ?" በሚል ርእስ ላይ ንግግር (public lecture) አድርጌ ነበረ። ንግግሩ እንደወረደ ነበረ፣ በኋላ አዘጋጁ የሬይ ዊተን ፎረም አጠር ያለ መግለጫ ስጠን ብለውኝ እንደምንም (የማስታውሰውን) ፃፍ...
7135 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...