Latest blog posts

Not published yet

የፌዴራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን በእነ አቶ መላኩ ፈንታ ላይ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ፡፡ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር በሚገኙት በእነ አቶ መላኩ ላይ የኮሚሽኑ

ዓቃቤ ሕግ ካቀረባቸው ሦስት የክስ መዝገቦች መካከል በመዝገብ ቁጥር 141356 ላይ ከቀረቡ 28 ክሶች መካከል 23 ክሶችን አሻሽሎ እንዲያቀርብ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15 ወንጀል ችሎት ብይን መስጠቱ ይታወሳል፡፡

የፍርድ ቤቱን ብይን የተቃወመው የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ የክስ መዝገቡን ማሻሻል እንደሌለበት በመጥቀስ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ አቤቱታውንና ብይኑን መርምሮ የዓቃቤ ሕግን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሥር ፍርድ ቤቱን ብይን አፅንቶታል፡፡

የሥር ፍርድ ቤቱ ዓቃቤ ሕግ እንዲያሻሽል ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረው ዓቃቤ ሕግ በቡድን በቡድን ያቀረባቸው 23 ክሶችን ነጥሎ እንዲያቀርብ፣ ጊዜና ቀን ያልተጠቀሰባቸውን ክሶች ጠቅሶ እንዲያቀርብና ለክሶቹ ማስረጃነት ያቀረባቸው ሰነዶች ጥቅል በመሆናቸው የትኛው ማስረጃ ለየትኛው ክስ እንደሚያስረዳ ግልጽ ባለመሆኑ አስተካክሎ እንዲያቀርብ ብይን ሰጥቶ ነበር፡፡

ይህንን የከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትናንትናው ዕለት ያፀናው በመሆኑ፣ ዓቃቤ ሕግ ሰኔ 27 ቀን 2006 ዓ.ም. በችሎት ቀርቦ ክሶቹን አሻሽሎ የሚያቀርብበትን የጊዜ ትዕዛዝ ይቀበላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡    


Editors Pick

Criminal Law Blog
1.      Introduction Globalization is easing border restrictions and increasing travel opportunities. Perpetrators use globalization to avoid prosecution and justice. This problem can be solved by cre...
5665 hits
Taxation Blog
    መግቢያ በሀገራችን የኤክሳይዝ ታክስን በተመለከተ በሥራ ላይ የነበረው አዋጅ ቁጥር 307/2002 (እንደተሻሻለ) ተሽሮ በአዲስ የኤክሳይዝ አዋጅ ቁጥር 1186/2020 የተተካ ስለመሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ይህ ጽሁፍ ሁለቱ አዋጆች የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸው ዕቃዎችን፤ ታክሱን የመክፈል ግዴታን እና ታክሱ ስ...
3874 hits
Property Law Blog
  መሬት ካለው ተፈጥሮዋዊ ባሕርይም ሆነ ግዙፍነት የተነሳ በሃገራችን ፖለቲካል ኢኮኖሚ ማዕከል ሆኖ እስካሁን ዘልቋል፡፡ በተለይም አብዛኛው ሕዝብ በእርሻ  የሚተዳደር ባለበት ሃገር የመሬት ጉዳይ የኢኮኖሚያዊ መሣሪያ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ የሆነ ጠቀሜታ አለው፡፡ የሃገሪቱን የመሬት ስሪት (land tenure) ወደ ኋላ...
26992 hits
Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
በዳኛው ገጠመኝ እንጀምር። የአንዱ የኦሮሚያ ወረዳ ፍ/ቤት ዳኛ ለተዘዋዋሪ ችሎት በሕዝብ ትራንስፖርት እየሄደ ነበር። መኪናው ውስጡ ሞልቶ ረዳቱ ከላይ ለመጫን ይቃጣዋል። መኪናው ላይ የተፃፉ ጥቅሶች እንቅጩን ይናገራሉ። "ታሪፍ እንጂ ትራፊክ የለም፣ ጠጋ ጠጋ በሉ"  "የሰው ልጅ ክቡር ነው፣ ትርፍ ሰው የለም ግቡ" "...
7491 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...