Abyssinia Law Abyssinia Law
  • Home
  • Laws
    • Federal Laws Database
    • Regional Laws
    • Constitutions
    • Audio Legal Resources
  • Decisions
    • Cassation Decisions by Volume
    • Cassation Decisions Database
    • FFI Court Commercial Bench Decisions
  • Blog
  • Resources
    • Researches Papers
    • Policies and Strategies
    • Codes, Commentaries and Explanatory notes
    • Legal Forms
    • Bench Books
    • Human Right Documents
    • Modules and Materials
    • About Our Laws
  • Study On-line
  • know your rights
  • Lawyers
  • Discussions
  • About Us
    • Who Are We
    • Our Partners
    • Advertise with Us
    • Privacy Policy
    • Professional Advice?
    • Contact us
    • How to submit a blog post
  • login
Michael Teshome

የግልግል ስምምነት /Arbitration Agreement/ እና የፍርድ ቤቶች ሥልጣን

በውሳኔው ሐተታ ላይ ‹‹…ይህ መርህ የግልግል ዳኛው የግልግል ዳኝነት ስምምነቱ ዋጋ ያለው መሆን አለመሆኑን በተመለከተ የሚነሳ ክርክር ጭምር ሰምቶ መወሰን እንዲችል ሥልጣን የሚሰጠው ቢሆንም ይህ መርህ… በአገራችን በከፊል ተቀባይነት ባለማግኘቱ በዚህ ድንጋጌ መሠረት በአገራችን የግልግል ዳኛ የግልግል ዳኝነት ስምምነቱ

Michael Teshome
Arbitration Blog
22 February 2023
Continue reading
Fesseha Negash Fantaye

ARTICLE REVIEW - Seyoum Yohannes, the Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration: the Extent of Party Autonomy

Including the abstract, introduction, and concluding remarks, the author’s work is structured into eight sections. The author used abstract and introduction to introduce readers to his work's content,

Fesseha Negash Fantaye
Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
22 April 2023
Continue reading
Nigussie Redae

የዋስትና መብት መከበር ላይ በፖሊስ የሚቀርብ የይግባኝ ጥያቄ ህጋዊ አንድምታው ሲገመገም

እንዳለመታደል ሆኖ የሀገራችን ተቋማት በእጅጉ በግልሰቦች እና በተለያዩ ፖለቲካዊ ተፅዕኖዎች ውስጥ የወደቁ በመሆናቸው የሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች አፈፃፀም ላይ ብዙ ጥሰቶች ሲፈፀሙ መቆየታቸው ማስረጃ የማይጠየቅበት እውነት ነው። ከእነዚህ የሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ውስጥ በኢፌዲሪ ህገመንግስት አንቀፅ 1

Nigussie Redae
Criminal Law Blog
03 May 2023
Continue reading
Fasika Abera

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን - የሴቶች ጥቃት ችግር - ሴቶች

በእርግጥ ሁሉም ችግሮች እንደየደረጃቸው እና ጥልቀታቸው በጥናት የሚለዩ መሆኑን አምናለሁ። ይሁን እና ጥናትም ለማድረግ ችግሩ ባለቤት ሊኖረው የሚገባ ስለመሆኑ ደግሞ የምንግባባበት ነው ብየ አስባለሁ። ይህ እንዳለ ሆኖ ጥናትም ለማድረግ ቢሆን መጀመርያ ላይ መነሻ ሊኖረን የሚገባ ነው። ለዚህም ነው ከዚህ ጉዳይ ጋር በተ

Fasika Abera
Human Rights, Public Policy and Law Blog
17 March 2023
Continue reading
Sesay Goa

ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ ዕይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ

ዳግም ኢጣሊያ ወረራ ፈፅሞ ለአምስት አመት ግዛቱን ባስተዳደረበት ጊዜና ኢጣሊያን በእንግሊዝ አጋዥነትና በሀገር ውስጥ በነበሩ አርበኞች ያላቋረጠ ትግል ከሀገር ሲባረር ስልጣን በቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ቁጥጥር ስር ቢገኝም የእንግሊዝ መንግስት አስተዳደር በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ፣ ፓሊቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ጣልቃ ገ

Sesay Goa
Criminal Law Blog
17 March 2023
Continue reading
muluken seid hassen

ስለባልና ሚስት የጋራ እና የግል ንብረቶች በተመለከተ የፌዴራሉን የቤተሰብ ሕግና የተመረጡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎችን መሰረት በማድረግ የቀረበ

በዚህ ጽሑፍ ጋብቻ በተጋቢዎቹ የግልና የጋራ ንብረት ላይ ስለሚኖረው ውጤት እንዲሁም በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረት የግል ወይም የጋራ ሊባል ሲለሚችልበት የሕግ አግባብ፤ በተጋቢዎቹ መካከል የሚደረግ የስጦታ ውል ህጋዊ ውጤቱና የአደራረግ ስነ ስርዓቱ፣በትዳር ውስጥ የወጣ ወጪ ለትዳር ጥቅም ዋለ ሊባል ስለሚችልባቸውና የማ

muluken seid hassen
Family Law Blog
30 December 2022
Continue reading

Latest Blog posts

Nigussie Redae
Nigussie Redae
03 May 2023
የዋስትና መብት መከበር ላይ በፖሊስ የሚቀርብ የይግባኝ ጥያቄ ህጋዊ አንድምታው ሲገመገም
Criminal Law Blog
መግቢያ በኢፌዲሪ ህገመንግስትም ይሁን ኢትዮጵያ በአፀደቀቻቸው አለማቀፋዊ የሰበዓዊ መብት ስምምነቶች እንዲሁም በሌሎች አዋጆች ላይ የተቀመጡ አያሌ የሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተፈፃሚነት እንዲኖራቸው በህግ እና በስርዓት የሚመሩ፤ ዋና ግባቸው እና የሥራ መለኪያቸው ህግ እና ሥርዓትን ማስከበር የሆኑ ተቋማት መኖራቸው ጥያቄ ውስጥ የማይገባ ቅድመ ሁኔታ ነው። እነዚህ ተቋማት እርስ በራሳቸው በ...
2049 Hits
Read More
Fesseha Negash Fantaye
Fesseha Negash Fantaye
22 April 2023
ARTICLE REVIEW - Seyoum Yohannes, the Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration: the Extent of Party Autonomy
Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
Seyoum Yohannes, the Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration: the Extent of Party Autonomy, Mizan Law Review, Vol. 10, No.2, December 2016, p. 341 - 365 (You may download this article from Here) The arbitration agreement ...
1658 Hits
Read More
Sesay Goa
Sesay Goa
17 March 2023
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ ዕይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ
Criminal Law Blog
መግቢያ ፡- ተበዳዮች በወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ የነበራቸው የተሳትፎ ሚና፡ ጥቅል ምልከታ በኢትዮጵያ የወንጀል ተጎጂዎች በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ውስጥ ያላቸው ሚና ከነበረበት የማማ ደረጃ በጊዜ ሂደት ‹‹ከማማ የመውረድ›› ያህል ዝቅ እያለ መጥቷል። ሀገሪቱ በዳግም የኢጣሊያ ወረራ ተፈፅሞባት ከመያዝዋ እ.እ.አ ከ 1935 ዓ.ም በፊት በወንጀል ጉዳት ደርሶባቸው በቀጥታ ተበዳይ የሆኑ ሰዎች ወይም ...
1834 Hits
Read More
Fasika Abera
Fasika Abera
17 March 2023
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን - የሴቶች ጥቃት ችግር - ሴቶች
Human Rights, Public Policy and Law Blog
እንኳን ለአለማቀፍ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ። ዛሬ የመጣሁበት ዋነኛ ምክንያት ከዚህ ቀን ማለትም ከአለማቀፍ ሴቶች ቀን እና አለማቀፍ ነጭ ሪቫን ቀን አከባበር ጋር በተያያዘ ሁል ግዜም በአይምሮዬ የሚመላለሱ ጥያቄዎች ስላሉኝ እነሱን ለማንሳት እና ከጉዳዩም ጋር ተያይዞ ከስራ እና በሕይወት የተረዳኋቸውን አንዳንድ ነጥቦች ለማካፈል ነው።...
1585 Hits
Read More

Editors Pick

Saleamlak Yemane Birhan
የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ትኩረት ያልሰጠበት የገበያዉ ሁኔታ እና አተገባበሩ
Commercial Law Blog
  መግቢያ የኮሮና ወረርሽኝን ተከትሎ በሽታዉን ከመቋቋም ጎን ለጎን ኢተዮጵያ ካጋጠማት ችግሮች መካካል አንዱ የገበያ በተለመደዉ የፍላጎትና አቅርቦት መርህ (Demand and supply) አለመሄድ ነዉ፡፡ ይህ ችግር በአብዘኃኛዉ ያደጉ ሃገራት ላይ በተለይ በእንደዚህ አስጊ ሰዓት የመፈጠር እድሉ በጣም ዝቅተኛ ነዉ፤ ይ...
5630 hits
Read More
አብዱሰላም ሳዲቅ ሙክታር
አዲሱ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እና አንዳንድ ጉዳዮች
Labor and Employment Blog
  ከዚህ ቀደም በሀገራችን ኢትዮጵያ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይን የሚገዙ ሕጎች እንደነበሩ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ በ1955 ዓ.ም የወጣው የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 210/1955፣ በ1968 ዓ.ም የወጣው የሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 64/1968፣ የሠራተኛ ጉዳይ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 85/...
80055 hits
Read More
Zelalem Kibret
ሳንሱር እና ሕግ፡ ከትናንት እስከዛሬ
About the Law Blog
የሰው ልጅ ሐሳቡን ለሌላው መግለጽ መጀመሩ ሰዎች የጋራ ባሕርያትን ይዘው ወደ አዲስ ስልጣኔ፤ ወደ አዲስ ሕይወት እንዲወጣ አድርጎታል፡፡ ነገር ግን የዚህ ትስስር ድንበር የለሽ መሆን ጉዳት አለው በማለት፤ በተለያዩ ወቅቶች በተለያዩ ምክንያቶች መረጃን የመለዋወጡ ሂደት ገደብ እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ ገደብ እንዲደረግ የ...
7058 hits
Read More
Abyssinia Law | Making Law Accessible!
የዞን ዘጠኝ አምስት ተከሳሾች ክስ መቋረጥ ብዥታ
Criminal Law Blog
መግቢያ   መጠይቅ ደግ ነው፡፡ የአስፈጻሚ አካላት ሥልጣንና ተግባራትን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 691/2003 አንቀጽ 16(6) ፍትሕ ሚኒስቴር በቂ ምክንያት ሲኖር በሕግ መሠረት ሂደት ላይ ያለን ክስ ያነሳል በሚል ይደነግጋል፡፡ ፍትሕ ሚኒስቴር የተሰጠው ክስ የማንሳት ሥልጣን እስከምን ድረስ ነው? ክስ ማንሳት...
9280 hits
Read More

Latest documents

Education and Training Policy of Ethiopia - Amharic version - 2023
7259 Downloads  - policies and strategies
7.6 MB
The Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration - the Extent of Party Autonomy
202 Downloads  - Arbitration Law
635.59 KB
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25
8871 Downloads  - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions
10.72 MB
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ እይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ FEATURED
402 Downloads  - Criminal Law
317.19 KB
Federal Supreme Court Cassation Decisions - Table of content Volume 1-25
10454 Downloads  - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions
6.57 MB
Print Email
Details
Category: Legal News - የሕግ ዜናዎች

የጋዜጠኞችና ጦማሪያን ጊዜ ቀጠሮ በመደበኛ ችሎት እንዲታይ ታዘዘ

-ጉዳዩ በግልጽ ችሎት እየታየ ነው ቢባልም ታዳሚዎች ግን መግባት አልቻሉም 

በተጠረጠሩበት የሽብርተኝነት ወንጀል በቁጥጥር ሥር ውለው ከታሠሩ ሁለት ወራት የሆናቸው የጋዜጠኞችና ጦማሪያን ጊዜ ቀጠሮ ቅዳሜና እሑድ መታየቱ ቀርቶ፣ በመደበኛ የችሎት ጊዜ እንዲታይ ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡

የተጠርጣሪዎቹ የጊዜ ቀጠሮ በመደበኛ ችሎት እንዲታይ የታዘዘው፣ የሦስቱ ጦማሪያን ማኅሌት ፋንታሁን፣ በፍቃዱ ኃይሉና አቤል ዋበላ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. ሲቀርቡ ነው፡፡

ሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. የነበረውን የተጠርጣሪ ጦማሪያን ጉዳይ ለመከታተል በአራዳ ምድብ ችሎት የተገኙ ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ የተለያዩ አገሮች ዲፕሎማቶች፣ የአገር ውስጥና የውጭ ጋዜጠኞች እንደወትሮው ሁሉ በርከት ያሉ ነበሩ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከመምጣታቸው በፊት ዳኛዋ በችሎት የተገኙ ቢሆንም፣ የምርመራ መዝገብ የሚያቀርቡት ሬጅስትራር በሰዓቱ ባለመገኘታቸው ዳኛዋ ያለመዝገብ መሥራት እንደማይችሉ ገልጸው፣ ለሰኔ 23 ቀን 2006 ዓ.ም. ቀጠሮ በመስጠት የተጠርጣሪዎቹን ጠበቃ ማሰናበታቸውን ጠበቃ አመሐ መኮንን ለታዳሚዎች ተናገረዋል፡፡ ተስፋ ያልቆረጡ የችሎቱ ታዳሚዎች ባሉበት ሆነው በመነጋገር ላይ እያሉ ሬጅስትራሯ ከጠዋቱ 4፡05 ሰዓት ላይ ሲደርሱ፣ ‹‹መጡ መጡ›› ተብሎ ጠበቃውም ወደ ችሎት ተመልሰው ገቡ፡፡ 

በዕለቱ የተሰየሙት ዳኛ የተጠርጣሪዎቹ ጉዳይ በመደበኛ ችሎት እንዲታይ ያዘዙት በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡ አንደኛው ለሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. ተቀጥረው የነበሩት ሦስቱ ተጠርጣሪዎች በሰዓቱ ቀርበው ዳኛዋም በሰዓቱ የተሰየሙ ቢሆንም፣ የምርመራ መዝገቡን የሚያቀርቡት የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር በሰዓቱ ባለመድረሳቸው ነው፡፡ ሌላው ምክንያት ደግሞ ተጠርጣሪዎቹ የሚያቀርቡትን አቤቱታ በመደበኛው ችሎት ማስመዝገብ እንዲችሉ መሆኑን ጠበቃ አመሐ መኮንን ተናግረዋል፡፡ 

ሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በቀረቡት ጦማሪያን ማኅሌት፣ በፍቃዱና አቤል ላይ የፌደራል ፖሊስ ለ28 ቀናት የሠራውን የምርመራ ሒደት እንዲያስረዳ ተጠይቋል፡፡ መርማሪ ፖሊስም ያልተያዙ የተጠርጣሪዎቹ ግብረ አበሮች መኖራቸውን፣ ምስክሮችን ሰምቶ አለመጨረሱን፣ ሰነዶችን አስተርጉሞ እንዳልጨረሰና የቴክኒክ ምርመራ እንደሚቀረው አስረድቶ፣ ለተጨማሪ ምርመራ የ28 ቀናት ጊዜ እንዲሰጠው መጠየቁን ጠበቃ አመሐ ገልጸዋል፡፡ 

በዕለቱ የተሰየሙት ዳኛ ግን የተጠርጣሪዎቹን ጠበቃ አስተያየትም መስማት ሳያስፈልጋቸው መዝገቡ ረጅም ጊዜ የቆየ መሆኑን በመግለጽ፣ 28 ቀናት እንደማይፈቅዱ አስታውቀዋል፡፡ በመሆኑም ፖሊስ ቀርቶኛል ለሚለው ተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት ብቻ በመፍቀድ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ ዳኛዋ የፈቀዱት የ14 ቀናት ማብቂያ እሑድ ሐምሌ 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ቢሆንም፣ እሳቸው ግን አንድ ቀን በመጨመር ለሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. እንዲሆን ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ ዳኛዋ አንድ ቀን የጨመሩበትን ምክንያት ሲገልጹ፣ የቅዳሜና የእሑድ ችሎት ለአሠራር አመች ስላልሆነና በጉዳዩም ላይ ዳኞች በመቀያየራቸው ወጥነት የሌለው ነገር እየተከሰተ በመሆኑ፣ አሠራሩን ለማስተካከል መሆኑን ጠበቃ አመሐ መኮንን  አስረድተዋል፡፡ 

ከተጠርጣሪዎቹ ጦማሪያን መካከል በፍቃዱ ኃይሉ ለችሎቱ ባቀረበው አቤቱታ፣ በምርመራ ወቅት እሱ የሰጠውን ቃል ሳይሆን ፖሊስ በራሱ መንገድ እየጻፈው መሆኑን ገልጾ፣ በመዝገቡ ላይ ያለው ቃል የሱ ቃል አለመሆኑ በማስረዳት ድርጊቱን መቃወሙን ጠበቃ አመሐ ተናግረዋል፡፡ ለተጠርጣሪ በፍቃዱ ምላሽ የሰጡት ዳኛዋ፣ አቤቱታውን ማቅረብ ያለበት ክስ የሚመሠረት ከሆነ በመደበኛው ችሎት ላይ መሆኑ አስታውቀው የዕለቱ ችሎት ማብቃቱን ጠበቃው ለታዳሚዎች አስረድተዋል፡፡ 

በዕለቱ በታዳሚዎችና በፖሊስ መካከል አለመግባባትም ተከስቶ ነበር፡፡ በፖሊስ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩት ሦስቱ ተጠርጣሪ ጦማሪያን ወደ ፍርድ ቤቱ ግቢ ሲደርሱ፣ በግቢው ውስጥ የነበሩ የችሎቱ ታዳሚዎች መጠነኛ ጭብጨባ አሰሙ፡፡ ከችሎቱ ግቢ ያስወጡናል የሚል ፍርኃት ያደረባቸው የተወሰነ ታዳሚዎች ‹‹ተው ተው አታጨብጭቡ›› ሲሉ፣ ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት ተንደርድረው በመሄድ አንዲትን ልጅ ጎትተው በማውጣት እያመነጫጨቁ ሲገፏት፣ ሌላኛው ወጣት ደግሞ ‹‹እህቴ ናት ልቀቋት ምን አደረገች?›› በማለት ሲቃወም፣ ‹‹ዝም በል›› በማለት ከፖሊስ ግሰጻ ቢደርስበትም መታገስ ያልቻለው ወጣት ‹‹እኔንም ውሰዱኝ›› ሲል አንድ መገናኛ ሬዲዮ የያዘ የፌደራል ፖሊስ ‹‹አምጣው›› በማለት ወጣቱን በመገፍተር ሁለቱንም ወደ ችሎት ወስዷቸዋል፡፡ በፖሊስ የተወሰዱት ሁለቱ ወጣቶች ዮናታን ተስፋዬና ምኞት መኮንን የሰማያዊ ፓርቲ አባል መሆናቸውም ተነግሯል፡፡ ሌሎች የፖሊስ አባላት ወደ ታዳሚዎች በመመለስ ‹‹በሕግ አምላክ ውጡ›› ሲሉ፣ የተወሰኑ ታዳሚዎች ‹‹ምን አደረግን? ዝም ብለን ቆመናል፤›› በማለት መልሰዋል፡፡ ፖሊሱ ‹‹እንዴት ፎቶ ታነሳላችሁ?፣ ማንም ሳያስፈቅድ ማንንም ማንሳት አይችልም፣ እንኳን ሰው ይችን (በጣቱ እያሳየ) መሬት ሳያስፈቅድ ፎቶ ማንሳት አይችልም›› ሲል ታዳሚዎች ከንዴታቸው በረድ ብለው ፈገግ አሉ፡፡ በመጨረሻም ታዳሚዎች እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡ እያጉረመረሙ ግቢውን የለቀቁት የችሎት ታዳሚዎች አስፓልት ላይ በመቆም ተጠርጣሪዎቹን ሲወጡ ለመሰናበት መጠበቅ ጀመሩ፡፡ ሁኔታ ያላስደሰተው ፌደራል ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠሪያ ኤጀንሲ በኩል አስወጥቶ ወደ ማዕከላዊ መውሰዱ ሲረጋገጥ ታዳሚዎችም ወደየመጡበት ሄዱ፡፡

EthiopianReporter By EthiopianReporter
EthiopianReporter
Last Updated: 11 October 2022
Hits: 33810
Abyssinia Law | Making Law Accessible!
Abyssinia Law | Making Law Accessible!
  • Prev
  • Next
Copyright © 2023 Abyssinia Law | Making Law Accessible! . All Rights Reserved.
Maintained by Liku Worku Law Office