Latest Blog posts
Editors Pick
Latest documents
Education and Training Policy of Ethiopia - Amharic version - 2023 7210 Downloads - policies and strategies | 7.6 MB | |
The Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration - the Extent of Party Autonomy 187 Downloads - Arbitration Law | 635.59 KB | |
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25 8541 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 10.72 MB | |
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ እይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ FEATURED 370 Downloads - Criminal Law | 317.19 KB | |
Federal Supreme Court Cassation Decisions - Table of content Volume 1-25 10261 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 6.57 MB |
- Details
- Category: Legal News - የሕግ ዜናዎች
አብዛኞቹ ዳኞች ከጠበቆች ጋር እየተመሳጠሩ ይሠራሉ የሚል እምነት የለኝም አቶ ተገኔ ጌታነህ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን የአገሪቱን የሕግ ተርጓሚ አካል የሚመሩት የተከበሩ አቶ ተገኔ ጌታነህ፣ በዳኞች ላይ የሚቀርብ ትችት ቢኖርም አብዛኞቹን ዳኞች የሚመለከት አለመሆኑን ለፓርላማ ገለጹ፡፡
አቶ ተገኔ የፌዴራል ፍርድ ቤቶችና የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የአሥር ወራት የሥራ አፈጻጸምን ባቀረቡበት ወቅት፣ ከብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ለቀረበላቸው ከዲሲፕሊን ጋር የተየያዘ ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
‹‹በአሁኑ ወቅት ኅብረተሰቡ ጠበቆችን የሚመርጠው ምን ያህል ከዳኞች ጋር ትውውቅ አለው? ወይም ባለሥልጣን ያውቃል? በሚል መለኪያ መሆኑን የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባካሄደው ጥናት ገልጿል፡፡ እርስዎ የሚመሩት አካል እንዲህ በመሆኑ ምን ይሰማዎታል?›› ሲሉ አቶ ግርማ ጠይቀዋል፡፡ የጥናቱ ውጤት በጠበቆች ላይ ያነጣጠረ ቢመስልም፣ የተተኮረው ዳኞች ላይ ነው ብለዋል አቶ ግርማ፡፡
አቶ ተገኔ ለጥያቄው በሰጡት ምላሽ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ያጠናው ጥናት ተገቢነት እንደሌለው ራሱ ማመኑን በመጀመሪያ ከገለጹ በኋላ፣ በዳኞችና በጠበቆች መካከል መመሳጠር ሊኖር ቢችልም፣ ይህ ሁኔታ አብዛኞቹ ዳኞችን አይወክልም ብለዋል፡፡
‹‹አብዛኛዎቹ ዳኞች ከጠበቆች ጋር እየተመሳጠሩ ይሠራል ብዬ አላምንም፡፡ ጥቂት ዳኞች ይህንን ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ችግሩ ግን ከዳኞች ጋ ብቻ የሚመነጭ አይደለም፤›› ያሉት አቶ ተገኔ፣ ችግሩን ለመቅረፍ ከሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ጠበቆችንም ጨምሮ እየሠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የዳኝነት ዘርፍ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ በዚህ ዓመት ውስጥ ጥናት መደረጉን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፣ ‹‹በውጤቱም በርካታ ችግሮች ተገኝተዋል፡፡ የሥነ ምግባር፣ የኪራይ ሰብሳቢነት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ከአመራሩ ጀምሮ የክህሎት ችግሮች፤›› ዋነኞቹ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በተጠቀሰው የአሥር ወራት ጊዜ ውስጥም አንድ ዳኛ ከተገልጋይ በቀረበባባቸው ክስ በዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የቃል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው፣ ሁለት ዳኞች ደግሞ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው መደረጉን በሪፖርታቸው አስረድተዋል፡፡
በ50 መዝገቦች የቀረቡ አቤቱታዎች በዲሲፕሊን የማያስጠይቁ በመሆናቸው እንዲዘጉና በሌሎች 17 መዝገቦች የቀረቡ አቤቱታዎች በድጋሚ እንዲጣሩ መወሰኑን በሪፖርታቸው አሳውቀዋል፡፡ በችግርነት ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል ለዳኞች የመኖሪያ ቤት ለመገንባትና ትራንስፖርት ለማቅረብ የተወሰነውን በማስፈጸም ረገድ በመንግሥት በኩል ዘግይቷል ብለዋል፡፡