Latest blog posts

Not published yet

የሕክምና ዕርዳታ በመፈለግ ወደ አንድ የሕክምና ተቋም የሄዱ የሁለት ወር ነፍሰ ጡር ወይዘሮን በቸልተኝነት በአካላቸው ላይ ጉዳት ያደረሱ የሕክምና ባለሙያ ታሰሩ፡፡

ክሱ የቀረበባቸው ተጠርጣሪው ዶ/ር በላቸው ቶሌራ ያደታ ሲባሉ፣ የግል ተበዳይ በሆኑት ወ/ሮ በላይነሽ ይመር ላይ ባደረሱት ጉዳት በዓቃቤ ሕግ ክስ ተመሥርቶባቸው ነበር፡፡ ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራል የመጀመርያ ፍርድ ቤት የመናገሻ ምድብ ወንጀል ችሎት ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ጥፋተኛ ብሏቸዋል፡፡

ተከሳሽ የሌላ ሰውን አካል ወይም ጤንነት የመጠበቅ ሙያዊ ግዴታ እያለባቸው ተገቢውን ጥንቃቄ ባለማድረግ ኅዳር 1 2006 ዓ.ም. በግምት ከቀኑ አምስት ሰዓት ገደማ፣ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 09/15 በሚገኝ የግል ክሊኒክ ውስጥ የሕክምና ስህተቱን በቸልተኝነት እንደፈጸሙ የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ተበዳይ ወ/ሮ በላይነሽ ይመር የሁለት ወር ፅንስ ማህፀናቸው ውስጥ እንደነበርና የደም መፍሰስ ምልክት በማየታቸው ደሙ እንዲቆምላቸው የሕክምና ዕርዳታ ለማግኘት ወደ ክሊኒኩ መሄዳቸውን የመዝገቡ ለመረዳት ተችሏል፡፡

‹‹በክሊኒኩም 987 ብር በመክፈል ፅንሱ ችግር ስላለበት መቋረጥ አለበት በማለት ያለጥንቃቄ በማህፀናቸው ብረት በማስገባት የማህፀናቸው ግድግዳ 3.2 ሴንቲ ሜትር እንዲሸነቆር፣ 70 ሴንቲ ሜትር ትንሹ አንጀት እንዲበላሽ ወይም እንዲሞትና ተቆርጦ እንዲወጣ የሕክምና ባለሙያው በማድረጋቸው፣ 300 ሲሲ ደም ወደ ሆዳቸው እንዲፈስ በማድረግ በፈጸሙት በቸልተኝነት አካል ላይ ከባድ ጉዳት የማድረስ ወንጀል ተከሰዋል፤›› ይላል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተው የክስ መዝገብ፡፡

በጉዳዩ ላይ ላለፉት ወራት ሁለቱን ወገኖች ሲያከራክር የነበረው ፍርድ ቤቱ ባለፈው ግንቦት 26 ቀን 2006 ዓ.ም የሕክምና ባለሙያውን ጥፋተኛ በማለት በእስር እንዲቆዩ ወስኗል፡፡ በጉዳዩ ላይም ፍርድ ለመስጠት ለዛሬ ሰኔ 4 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል፡፡


Editors Pick

Contract Laws Blog
  {autotoc}     Abstract Government contract placing is not left to the whim of the individual power holders at the various hierarchies of the government structure. What officials of the government do...
6894 hits
Taxation Blog
  በዚህ ጽሑፍ ስለ ግብር ስወራ ምንነት፣ በተለያዩ የግብር ዓይነቶች ሥር የግብር ስወራ ስለሚያቋቋሙ ድርጊቶች፣ ለግብር ስወራ መነሻ ሊሆኑ ስለሚችሉ ምክንያቶች እንዲሁም የመከላከያ መንገዶቹ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡ ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ መነሻ የሆነኝ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጉምሩክና ታክስ ወንጀል ችሎት...
12500 hits
Constitutional Law Blog
{autotoc}     1. የመዘዋወር ነፃነት አለም አቀፋዊ አንድምታው የሰው ልጅ ሰው ሆኖ በመፈጠሩ ከሚያገኛቸው አያሌ የተፈጥሮ መብቶች ውስጥ ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነፃነት በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ የሰው ልጆችን ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነፃነት ከሐይማኖት፤ ከባህል እና ከሌሎች የተፈጥሮ ህግጋት ጀምርን ስንመለከተው ፅኑ...
8244 hits
Constitutional Law Blog
{autotoc} መግቢያ የፌዴራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 53 መሠረት በተቋቋመ ወዲህ ላለፉት 24 ዓመታት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከ1100 በላይ አዋጆችን ያወጣ ሲሆን ከእነዚህም አዋጆች ውስጥ በምክር ቤቱ በሚገኙ የገዢው ፓርቲ አባላት መካከል ሞቅ ያሉ ክርክሮችና የልዩነት ሃሳ...
10946 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...