Latest blog posts

በኢትዮጵያ ካኦርጃ የተባለ ፅንፈኛ የእስልምና አክራሪ አመለካከትን በሀይልና በሽብር ለማስፋፋት በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት የአሸባሪ ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሄራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎትና የፌደራል ፖሊስ የጋራ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል አስታወቀ።

ግብረ ሀይሉ በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ያላቸውን ተጠርጣሪዎች የሽብር መረብ ለመበጣጠስ እርምጃ መወሰዱን ገልጿል።

በቁጥር 25 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋቸውን የገለፀው ግብረ ሀይሉ፥ በሁለት የህቡዕ ቡድኖች የተደራጁት እነዚህ ተጠርጣሪዎች አልሸባብ ከተባለውና ከዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድኑ አልቃይዳ ጋር ቁርኝት ባለው አሸባሪ ቡድን በጎረቤት አገር ሶማሊያ ግዛት ውስጥ የሽብር ስልጠና የወሰዱ ናቸው ብሏል።

አንደኛው ቡድን ቀጥተኛ አመራር የሚያገኘው ደቡብ አፍሪካ ከሚገኝ እንድ አክራሪ ቡድን እንደነበርና የሽብር ቡድኑ በሶማሊያ በአልሸባብ ስልጠና ካገኘ በኋላ በኬኒያ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጓዝ አደረጃጀቱን አጠናክሮ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት በመግባት በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን እንቅስቃሴውን ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንዳለ በተደረገ ክትትል አባላቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

መግለጫው አያይዞም ሁለተኛው የሽብር ቡድን በሱዳን፣ በየመንና በኢንግሊዝ በሚገኙ ዓለም አቀፍ የካኦርጃ ጂሃዲስቶች እንቅስቃሴዎች ጋር ግኑኝነት በመመስረት ቀትተኛ አመራርና ልዩ ልዩ ድጋፍ ሲያገኝ ቆይቷል ነው ያለው።

የፀረ ሽብር ግብረ ሀይሉ በክትትል የተገኘው ይህ የሽብር ቡድን 30 የሚሆኑ አባላቱን ወደ ሶማሊያ በመላክ በአልሸባብ አማካኝነት ወታደራዊ ስልጠና እንዲያገኙ ማድረጉን ለማወቅ እንደተቻለ አስታውቋል።

የፅንፈኛው የካኦጃ እንቅስቃሴ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በሀይማኖት ስም በሚፈፀሙ የሽብር ድርጊቶች ውስጥ የተጋ ተሳትፎ እንዳለው ያሳወቀው ግብረ ሀይሉ፥ እንቅስቃሴው የሚከተላቸው የእምነት መርሆዎች ከናይጄሪያው እስላማዊ አሸባሪ ቡድን ከቦኮ ሃራም እምነቶች ጋር ተመሳሳይ መሆናቸውን አትቷል።

ፅንፈኛ አሸባሪ ቡድኑ ጠባብ አስተምህሮውን የማይጋሩ ሌሎች ሙስሊሞችን በሙሉ በከሃዲነትና በመናፍቅነት የሚፈርጅና በከሃዲነት የፈረጃቸውን ለመግደል በፈጣሪ የተሰጠ መለኮታዊ ፈቃድ አለ የሚል አደገኛ አስተምህሮ እንደሚያራምድ መግለጫው አሳውቋል።

ንቅናቄው ለምድራዊ መንግስት ግብር መክፈልን እንደ ከፍተኛ ሀጢያትና የእምነት ጥሰት የሚመለከትና የሞባይል ካርድ የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚቀረጥበት በመሆኑ በሞባይል ስልክ መገልገል በእስልምና እምነት የተከለከለ ሃጢያት /ሃራም/ ነው ብሎ የሚያራምድ ነው ብሏል መግለጫው።

የትራፊክ ህግጋትን ማክበርን ጨምሮ ዘመናዊ ትምህርትን መሻት ወይም መከታተል ለእርግማን የሚዳርግ ከፍተኛ ሀጢያት አድርጎ በማቅረብ ይህን አመለካከቱን በሌሎች ላይ በሀይልና በተፅዕኖ በመጫን የሚንቀሳቀስ አክራሪ አመለካከትን የሚከተል አደገኛ እንቅስቃሴ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል።

ከዚህ ቀደም በ1994 ዓመተ ምህረት የካኦርጃ ታጣቂዎች በምእራብ ኢትዮጵያ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች በተወሰደባቸው እርምጃ ጉዳትና ኪሳራ ደርሶባቸው እንደነበር መግለጫው አስታውሷል።

ሆኖም በቅርቡ በአክራሪ ሙስሊሞች የተሞከሩ የአመፅና የነውጥ ክስተቶች ለቡድኑ እንቅስቃሴ የሚመቹ መልካም አጋጣሚዎች ተደርገው በካኦርጃ እንቅስቃሴ አመራሮች መወሰዳቸውን ከምርመራው ለመረዳት መቻሉንም ነው ግብረ ሀይሉ የገለፀው።

መግለጫው እንቅስቃሴው ከአገር ውጪ ከሚያገኘው የገንዘብ እርዳታ በተጨማሪ በጅማ ዞን በሚገኙ የገጠር መንገዶችና በዋና ዋና መንገዶች ላይ በሚንቀሳቀሱ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቢሶች ላይ ጥቃት በማድረስ ገንዘብና ሞባይል ሲዘርፍ መቆየቱንና በነዚህ ጥቃቶችም ሁለት ሰላማዊ ዜጎችን መግደሉን አስታውሷል።

የአሸባሪ ቡድን አባላቱ ለሽብር ድርጊቱ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችንና የጦር መሳሪያዎችን ሲያከማቹ መቆየታቸውን የገለፀው የፀረ ሽብር ግብረ ሀይሉ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የተጀመረው ምርመራ እንደተጠናቀቀም ክስ እንደሚቀርብባቸውና ዝርዝር ጉዳዩን የሚመለከት መረጃ ለህዝብ ይፋ እንደሚደርግ ገልጿል።


Editors Pick

Criminal Law Blog
“Violations of human rights are both a cause and a consequence of trafficking in persons.”                                       UN human rights office of the High Commissioner, fact sheet 36  Introdu...
10890 hits
Commercial Law Blog
  Traditionally, corporations were responsible only to their owners; and their primary and only objective was profit maximization. Corporations’ responsibility towards the community and the environmen...
8780 hits
Taxation Blog
  በዚህ ጽሑፍ ስለ ግብር ስወራ ምንነት፣ በተለያዩ የግብር ዓይነቶች ሥር የግብር ስወራ ስለሚያቋቋሙ ድርጊቶች፣ ለግብር ስወራ መነሻ ሊሆኑ ስለሚችሉ ምክንያቶች እንዲሁም የመከላከያ መንገዶቹ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡ ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ መነሻ የሆነኝ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጉምሩክና ታክስ ወንጀል ችሎት...
12482 hits
About the Law Blog
  መግቢያ "ችሎት መድፈር" ወይም Contempt of Court በአብዛኛው ሃገራት የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ግልጋሎት ላይ እየዋሉ ካሉ የሕግ ፅንሰ ሃሳቦች አንዱ ነው። ይህ የሕግ ፅንሰ ሃሳብ በእኛ ሃገር በሰፊው ሥራ ላይ እየዋለ ቢሆንም ከሕጉ መንፈስ ውጭ አተገባበሩ ላይ የሚታየው የሕግ አተረጓጎም ክፍተትና ልዩነት የተለ...
7681 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...