Latest blog posts

“የፍትሕ ማሻሻያ ፕሮግራም መሳካቱን ወይም አለመሳካቱን ለማወቅ መለካት አለበት” ዶ/ር መንበረ ፀሐይ ታደሰ፣ የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር 

በመንግሥታዊ ተቋማት ተግባራዊ የሚደረጉ የማሻሻያ ፕሮግራሞች ተግባራዊ መሆን አለመሆናቸውንና በተቋማቱ ውስጥ መኖር አለመኖራቸውን እንዴት ማወቅ እንደሚቻል፣

የልምድ ልውውጥ የሚደረግበትና ለአምስት ቀናት የሚቆይ የአገር ውስጥና የውጭ ኤክስፐርቶች የሚወያዩበት  ዓውደ ጥናት ከግንቦት 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ ነው፡፡ 

በአሜሪካው ሀርቫርድ ኬኔዲ ስኩል፣ በእንግሊዙ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዲኤፍአይዲ) እና በኢትዮጵያ የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት ከግንቦት 11 እስከ 15 ቀን 2006 ዓ.ም. በሀርመኒ ሆቴል በመካሄድ ላይ በሚገኘው፣ ‹‹የፍትሕ አስተዳደርና ደኅንነት አመላካቾች›› በሚለው የዓውደ ጥናት ውይይት ላይ ከእስያ፣ ከአፍሪካ፣ ከእንግሊዝ፣ ከአሜሪካና ከሌሎች አገሮች የተውጣጡ ሰፊ ልምድና ዕውቀት ያላቸው ኤክስፐርቶች እየተወያዩ ነው፡፡ 

ዓውደ ጥናቱን አስመልክቶ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መንበረ ፀሐይ ታደሰ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች አገሮች የማሻሻያ ፕሮግራሞች አሉ፡፡ ለምሳሌ የፍትሕ ማሻሻያ ፕሮግራም አንዱ ነው፡፡ በመሆኑም ይኼ ማሻሻያ ፕሮግራም የታለመለትን ዓላማ እያሳካ መሆን አለመሆኑን መለካት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በምሳሌነት የጠቀሱት የፍትሕ ሥርዓቱን በሚመለከት ስለኢትዮጵያ የተናገሩት ዶ/ር መንበረ ፀሐይ ፍትሕን ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግና የዳኞችን ነፃነት ለማምጣት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው፣ ‹‹መሻሻል መኖር አለመኖሩ እንዴት ነው የምናውቀው? ቀርፀንስ ወደ ሥራ ለመለወጥ ምን ምን መሠረታዊ መረጃዎችን መጠቀም አለብን? መረጃ የምንሰበስበው እንዴት ነው?›› በሚሉ ነጥቦችና ሌሎች ጉዳዮችም ላይ ሰፋ ያለ ውይይት እንደሚደረግ፣ ጠቃሚ የሆነ የልምድ ልውውጥና ግብዓት ሊገኝ እንደሚችል ያላቸውን እምነት ተናግረዋል፡፡ 

በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ላይ ኢትዮጵያ በርካታ ዕቅዶችን ማስቀመጧን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የተቀመጡት ዕቅዶች በአግባቡ እየተተገበሩ መሆኑን ለማወቅ መለካት መቻል እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ላስቀመጣቸው ዕቅዶች መለኪያ ቢኖረውም፣ የሌሎች አገሮች ልምድንና የኢትዮጵያን ልምድ አንስቶ በመወያየት መድረኩ ጥሩ ግንዛቤ የሚጨበጥበት እንደሚሆን ዶ/ር መንበረ ፀሐይ ተስፋ አድርገዋል፡፡  

ብዙዎቹ ባለሙያዎች ከሀርቫርድ ኬኔዲ ስኩል የመጡ ቢሆንም፣ ከተለያዩ ስምንት አገሮች ወደ ኢትዮጵያ የመጡትና ከኢትዮጵያም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር፣ ከፍርድ ቤቶች፣ ከፓርላማ፣ ከፖሊስ፣ ከማረሚያ ቤቶችና ከተለያዩ ተቋማት የተሰባሰቡ ባለሙያዎች ጋር በሚደረገው ውይይት ጥሩ ግብዓት እንደሚገኝ ዶ/ር መንበረ ፀሐይ አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ማሻሻያዎችን ቀርጾ እየመራና ወደ ተግባር በመለወጥ ብዙ ርቀት መጓዙን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ዓውደ ጥናቱ በየዓመቱ በእንግሊዝ አገር የሚካሄድ ቢሆንም፣ ዘንድሮ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲደረግ የሆነበት ምክንያት መንግሥት ብዙ የተጓዘባቸው የለውጥ እንቅስቃሴዎች መኖራቸው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡


Editors Pick

Taxation Blog
  መግቢያ አዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 እየተሰራበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስቴር ስለኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 67/2013 ጸድቆ ከጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የዚህ ጽሁፍ ዓላማ በመመሪያው ...
2802 hits
About the Law Blog
In 2002, when I was doing my undergraduate degree, our contract law teacher started talking about period of limitation and its effect. I neither had a concept nor an argument about period of limitatio...
7939 hits
Property Law Blog
  Introduction Before the enactment of movable property security right proclamation, Ethiopian movable security right law is ultimately unsatisfactory because it is fragmented, and contained in four d...
3993 hits
Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
    ስለ ዜግነት አዎጁ በፃፍኩት ጽሑፍ ላይ አቶ ግዛዉ ለገሰ የተባሉ የሕግ ባለሙያ የፃፉት ምላሽ ደርሶኝ ተመለከትኩት፡፡ (የአቶ ግዛው ለገሰ ጽሑፍን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ፡፡ ) በመጀመሪያ ጸሐፊው የሕግ ባለሙያ እንደመሆናቸውም ብሎም ጽሑፉን ያወጡት እሳቸው ስላልተስማሙበት የሕግ ጽሑፍ ምላሽ ለመስጠት እንደ መሆኑ...
6455 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...