Latest blog posts

-በቀድሞው የደኅንነት ኃላፊና ሌሎች ተከሳሾች ላይ ምስክር መስማት ተጀመረ

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉ አንድ ዓመት ያለፋቸው የእነ አቶ መላኩ ፈንታ ክስ፣ ከሌሎች የክስ መዝገቦች ተለይቶ ሊታይ መሆኑን ፍርድ ቤት ሚያዝያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡

የተጠርጣሪዎቹን ክስ በመመርመር ላይ የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት እንዳስታወቀው፣ ችሎቱ ሥራ ይበዛበታል፡፡ ፍርድ ቤቱ እንደነ አቶ መላኩ ሁሉ ሌሎች በርካታ የክስ መዝገቦች ስለሚያይ፣ ሁሉንም መዝገቦች በተፋጠነ ሁኔታ ማየት አለመቻሉን አስረድቷል፡፡ የችሎቱ ሦስቱም ዳኞች በሥራ ብዛት በመጠመዳቸው፣ ብይን አጠናቀው በሠሩባቸው መዝገቦች ላይ ተገናኝተው ለመወያየት እንኳን አለመቻላቸውን የገለጸው ፍርድ ቤቱ፣ አቶ መላኩ ላይ  በሦስት መዝገቦች ያቀረበውን ክስና መቃወሚያን ብይን ሠርተው ቢጨርሱም፣ ተወያይተው ብይኑን ሚያዝያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ለተጠርጣሪዎቹ ለመንገር አለመቻላቸውን ፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ችግሩ ዳኞች ብቻ የሚናገሩት ሳይሆን የፍርድ ቤቱ አስተዳደርም እንደሚያውቀው የገለጸው ፍርድ ቤቱ፣ በቅርቡ የተሾሙ 27 ዳኞች እየተመደቡ በመሆኑ ችግሩ ሊቀረፍ እንደሚችል ተናግሯል፡፡

በመሆኑም የእነ አቶ መላኩ ፈንታን ክስ እየመረመረው የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት ለሁለት እንደሚከፈል የገለጸው ፍርድ ቤቱ፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ ድልድሉ እንደሚያበቃና ለሁለት በሚከፍለው አንደኛው ችሎት የእነ አቶ መላኩ የክስ ሒደት በተከታታይ መታየት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡ የፍርድ ቤቱ አስተዳደር በቅርብ ቀን አመቻችቶ እንደሚጨርስ እምነቱ መሆኑን የገለጸው ፍርድ ቤቱ፣ በሰጠው ብይን ላይ ዳኞች የቀራቸውን ውይይት አጠናቀው፣ ግንቦት 8 ቀን 2006 ዓ.ም. በክሱ፣ በተጠርጣሪዎች የክስ መቃወሚያና በዓቃቤያኑ የመቃወሚያ መቃወሚያ ላይ ብይን እንደሚሰጥ ተናግሮ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ሌላው ፍርድ ቤቱ በዕለቱ ያየው የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገር ውስጥ ኃላፊ በነበሩት አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፣ በወንድማቸው አቶ ዘርዓይና በእህታቸው ወ/ሪት ትርሃስ ወልደሚካኤል፣ እንዲሁም የቅርብ ጓደኞቻው ናቸው በተባሉት ነጋዴ አቶ ዱሪ ከበደ ላይ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን መስማት ጀምሯል፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ በአራቱ ተከሳሾች ላይ ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ማፍራት፣ ሥልጣንን አላግባብ መጠቀምና በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ሀብት ሕጋዊ አስመስሎ መያዝ (መጠቀም) በሚል 11 ክሶችን የመሠረተ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 35 ምስክሮችን በመቁጠር ከሚያዝያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ማሰማት ጀምሯል፡፡

የመጀመሪያዎቹ የዓቃቢያን ሕግ ምስክሮች ለፍርድ ቤቱ እንደገለጹት፣ ከአቶ ዱሪ ጋር በአፋር ክልል ከ1988 ዓ.ም. ጀምሮ አጋር ሆነው ይሠሩ እንደነበር፣ በኋላ ግን አቶ ወልደ ሥላሴ በ1999 ዓ.ም. ሲመጡ ከአጋርነታቸው እንዳስወጧቸው መስክረዋል፡፡ አቶ ወልደ ሥላሴ እንዳሳሰሯቸውም አስረድተዋል፡፡

ሁለተኛው የዓቃቤ ሕግ ምስክር ደግሞ ከአቶ ዱሪ ጋር አፍዴራ ላይ በጋራ ጨው ማምረት ቢጀምሩም፣ አቶ ዱሪ፣ አቶ ወልደ ሥላሴን ካስተዋወቋቸው በኋላ፣ በእሳቸው ተሽከርካሪ ይጫን የነበረው የጨው ምርት፣ በጌትአስና በነፃ ትሬዲንግ ተሽከርካሪዎች እንዲጫን በማድረግ እሳቸውን ከአጋርነት እንዳስወጡዋቸውና ክትትል ሲበዛባቸው ከአገር ተሰደው እንደነበር አስረድተዋል፡፡ 

አቶ ወልደሥላሴ በመስቀለኛ ጥያቄ እንደገለጹት፣ ምስክሩ ተገደው ሳይሆን ከአጋርነት የወጡት 1.5 ሚሊዮን ብር ድርሻቸውን ይዘው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሌሎች ምስክሮችም የተሰሙ ሲሆን፣ ቀሪ ምስክሮችን ግንቦት 14 እና 15 ቀን 2006 ዓ.ም.  እንደሚደመጡ ፍርድ ቤቱ ተናግሯል፡፡


Editors Pick

Commercial Law Blog
Introduction Staling public money hurts the poor disproportionately by diverting funds intended for development, undermining a Government’s ability to provide basic services, feeding inequality and in...
8430 hits
Taxation Blog
  የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 እራስን በራስ የማስተዳደር መብትን ከአዲስ አበባ እና ከድሬዳዋ ከተሞች ላይ የገፈፈ ስለመሆኑ እና የመፍትሔ አቅጣጫዎቹ፡፡   እራስን በራስ የማስተዳደር መብት የፌዴራል ሥርዓትን በሚከተሉ አገሮች የተለመደ አሰራር ሲሆን በዋናነትም ክልሎች ወይም ራስ ገዝ አስተዳ...
10005 hits
Criminal Law Blog
የተዋጣለት የወንጀል ምርመራ ሥራ ለወንጀል ፍትሕ ሥርዓት መስፈን ቁልፍ የሆነ ሚና እንደሚጫወት በርካታ በወንጀል ምርመራ ሥራ ላይ የታተኮሩ መጽሐፍት የሚገልጹት ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን፡፡ በወንጀል ምርመራ ወቀት የተፈጸመ ወንጀልን ለማግኘት እና ጥፋተኛውን ለይቶ ለማውጣት ከሚጠቅሙ ቀዳሚ ነገሮች መካከል የሚከተሉትን ...
21361 hits
Legislative Drafting Blog
Introduction It has often been considered that every addition of a new law in a statute book is amending a prior existing law. As a result, analyzing legislative proposal both in its relation and in i...
18042 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...