Latest blog posts

ፖሊስ ሌሎች ያልተያዙ አሉ ብሏል

ተጠርጥረው በተያዙት ሦስት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ላይ የፌዴራሉ ፍርድ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ተጨማሪ የአሥር ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቀደ፡፡

ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ካዋለችው የ‹‹ዞን ናይን›› ጦማሪያንና ጋዜጠኞች መካከል ስድስቱን በሁለት መዝገብ ከፍሎ ዛሬ ሚያዚያ 29 ቀን 2006 ዓ.ም. ለፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት አቅርቧል፡፡

በመጀመሪያው መዝገብ የቀረቡት የዞን ናይን አባላት የሆኑት ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃነና ኤዶም ካሣዬ ናቸው፡፡ በሁለተኛው መዝገብ የቀረቡት ደግሞ ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ፣ ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስና ጦማሪ ዘለዓለም ክብረት ናቸው፡፡ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የተመለከተው በዝግ ቢሆንም ከተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ለመረዳት እንደተቻለው፣ ጋዜጠኞቹና ጦማሪያኑ በሽብርተኝነት ከተፈረጀ ድርጅት ጋር በመገናኘት፣ ሥልጠና በመውሰድና ገንዘብ በመቀበል አገርና ሕዝብን ለማሸበር ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውን ፖሊስ ገልጿል፡፡ በተቀበሉት ገንዘብም ላፕቶፕና ሌሎች የጽሕፈት መሣሪያዎችን ገዝተዋል ብሏል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሌሎች ያልተያዙ በመኖራቸው፣ ያልተተረጐሙ መረጃዎች እስኪተረጐሙና በሌሎች ምክንያቶች ተጨማሪ የ15 ቀናት ጊዜ ፖሊስ መጠየቁንና ፍርድ ቤቱ የአሥር ቀናት ተጨማሪ ጊዜ በሁለቱም መዝገቦች መፍቀዱን ከጠበቆች ለመረዳት ተችሏል፡፡


Editors Pick

Contract Laws Blog
በዚህ በኩል ግቡ ብድር የሰው ልጅ እና ጎደሎው ከተገናኙበት ሩቅ ዘመን ጀምሮ የነበረ ሰዋዊ ድርጊት ነው፡፡ የብድር መሰረቶቹ መቀራረብ፣ እዝነት እና መተማመን ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን እነዚህ መሰረቶቹ እየተናጉ የብድርን ህልውና ሲፈታተኑት ይስተዋላል፡፡ በርካታ ሰዎችም ብድርን መሰረት ላደረጉ ክርክሮች ሲዳረጉ ይታ...
3450 hits
Human Rights, Public Policy and Law Blog
This is a brief article I wrote for the internal newsletter of the EHRC; it never got published due to delays in the coming out of the newsletter. I have planned to update it with additional informati...
17870 hits
About the Law Blog
{autotoc}   ሰሞኑን የአቶ ጀዋር መሐመድን ኢትዮጵያዊ ዜግነት መልሶ የማግኘት ጉዳይ በኦፌኮ እና በምርጫ ቦርድ መካከል ክርክሮችን ማስነሳቱን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየሰማን እንገኛለን፡፡ በመሆኑም የዜግነት ሕጉ ኢትዮጵያዊ ዜግነት መልሶ ስለማግኘት ስላሰቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች እና ዜግነት መልሶ ማግኘት ...
8605 hits
Construction Law Blog
    1. Introduction Risk is part of every human endeavor. From the moment we get up in the morning, drive or take public transportation to get to school or to work until we get back into our beds (and...
5205 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...