Latest Blog posts
Editors Pick
Latest documents
Education and Training Policy of Ethiopia - Amharic version - 2023 7210 Downloads - policies and strategies | 7.6 MB | |
The Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration - the Extent of Party Autonomy 187 Downloads - Arbitration Law | 635.59 KB | |
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25 8538 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 10.72 MB | |
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ እይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ FEATURED 367 Downloads - Criminal Law | 317.19 KB | |
Federal Supreme Court Cassation Decisions - Table of content Volume 1-25 10258 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 6.57 MB |
- Details
- Category: Legal News - የሕግ ዜናዎች
ኢትዮጵያውያን መሃን ሴቶች በሰው ሰራሽ መንገድ እንዲወልዱ የሚፈቅድ ደንብ ፀደቀ
በተለያዩ ምክንያቶች ለመካንነት የተዳረጉ ሴቶች በሰው ሰራሽ መንገድ መውለድ እንዲችሉ የሚፈቅድ ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸደቀ።
አገሪቱ በሰው ሰራሽ መንገድ መሃን የሆኑ ሴቶች ልጅ እንዲያገኙ ስራው በህግ የተደገፈ እንዲሆን የተለያዩ አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመዳሰሰ ደንብ ስታዘጋጅ ቆይታለች።
ደንቡም ከሳምንታት በፊት በሚኒስተሮች ምክር ቤት ጸድቋል።
ይህን ደንበ ማጽደቀ ያስፈለገው ልጅ ማግኘት ተፈጥሮአዊ መብት በመሆኑና ልጅ የሌላቸው ዜጎች የሚደርስባቸው የማህበራዊ ችግሮች ከፍተኛ በመሆኑ ነው ብለዋል በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህግ ጉዳዮች ዳይሮክቶሬት ረዳት ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ደስታ።
ይህን አገልግሎት አቅሙ ያለው የመንግስትም ይሁን የግል የጤና ተቋም መስጠት እንደሚችል ደንቡ ይፈቅዳል።
ከዚሀ በፊት ሀገሪቱ በግልጽ የከለከለችውን የማህጸን ኪራይ ይህ ደንብም በግልጽ ይከለክላል ብሏል ሚኒስቴሩ።
እናም ለህክምና አገልግሎት ከተሰጠው ፈቃድ ባሻገር ይህ አገልግሎት አለም አቀፍ ደረጃን የሚጠይቅ በመሆኑ ማንኛውም የጤና ተቋም ከተሰጠው ፈቃድ ባሻገር ልዩ ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል።
ለዚህም በመሳሪያም ይሁን በባለሙያ ዝግጁ መሆን የሚገባው ሲሆን፥ ባለሙያውም ይህን አገልገሎት ለመስጠት ልዩ ፈቃድ ያስፈልገዋል።
በአሁኑ ጊዜ ደንቡን ማስፈጸም የሚያስችል መመሪያ እየወጣ መሆኑን ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የገለፀው።
የቤተል ቲቺንግ ጄኔራል ሆስፒታል ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የማህፀን ደዌና የፅንሰ ስፔሻሊስት ዶክተር ይገረሙ አስፋው በማንኛውም መንገድ መውለድ የማይችሉ ኢትዮጵያውያን በህንድና ታይላንድ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት አገልግሎቱን ሲያገኙ መቆየታቸውን ያነሳሉ።
ኢትዮጵያውያኑ ልጅ ለማግኘትም ከ200 ሺህ ብር እስከ 300 ሺህ ብር ያወጡ ነበር ነው የሚሉት።
በሀገራችን በብቸኝነት አገልግሎቱን ጀምሮ ስራው በህግ የተደገፈ ባለመሆኑ አገልግሎቱን ያቋረጠው ቤተል ሆስፒታል ለሰባት አመታት ከጣልያንና ከእስራኤል ሀኪሞች ጋር በመተባበር አገልግሎቱን ሲሰጥ ቆይቷል ።
በዚህ መንገድም ለ700 ሰዎች አገልግሎቱን መስጠት ተችሏል ነው ያሉት።
አገልግሎቱ ከፍተኛ መድሀኒቶችን ከውጭ በማምጣትና ከውጭ የህክምና ባለሙያዎች ጋር የሚከናወን በመሆኑ ሆስፒታሉ ከ60 እስከ 90 ሺ ብር ነው አገልግሎቱን ሲሰጥ ቆይቷል።
አሁን ደንቡ መውጣቱም ኢትዮጵያውያን አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ውጭ የሚያደርጉትን ጉዞ የሚያስቀር ይሆናል።