Latest Blog posts
Editors Pick
Latest documents
Education and Training Policy of Ethiopia - Amharic version - 2023 7120 Downloads - policies and strategies | 7.6 MB | |
The Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration - the Extent of Party Autonomy 163 Downloads - Arbitration Law | 635.59 KB | |
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25 8046 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 10.72 MB | |
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ እይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ FEATURED 350 Downloads - Criminal Law | 317.19 KB | |
Federal Supreme Court Cassation Decisions - Table of content Volume 1-25 9940 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 6.57 MB |
- Details
- Category: Legal News - የሕግ ዜናዎች
በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በጨረታ 39 ሚሊዮን ብር የተሸጠው የአክሰስ ይዞታ ታገደ
ስድስት የሚሆኑት በመሠረቱት ክስ አሸናፊ ሆነው በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለጨረታ ቀርቦ 39 ሚሊዮን ብር የተሸጠው የአክሰስ ሪል ስቴት ይዞታ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መታገዱ ተሰማ፡፡
ከ72 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንደደረሰበት በመግለጽ ክስ መሥርቶ የሚገኝውን ጋቢ ኢንቨስትመንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያን ጨምሮ አምስት ግለሰቦች፣ አክሰስ ሪል ስቴት ያደረሰባቸውን በደል በመግለጽ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 6ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ክስ መሥርተው ነበር፡፡ ሪል ስቴቱ በቦሌ ክፍለ ከተማ መድኃኒ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የሚገኝውን 4,133 ካሬ ሜትር ቦታ በጨረታ ሸጠው ገንዘባቸውን እንዲወስዱ ፍርድ ቤቱ ወስኖላቸው እንደነበር ሰነዶች ያረጋግጣሉ፡፡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ያሳለፈበትን ቦታ ፍትሕ ሚኒስቴር እንዳይሸጥ፣ እንዳይለወጥና ጥንቃቄ እንዲደረግበት በሚል ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ለንግድ ሚኒስቴርና ሌሎች የመንግሥት ተቋማት ትዕዛዝ በማስተላለፉ ምክንያት ለተወሰኑ ቀናት የተፈረደላቸውን ሰዎች ግራ ያጋባ ሁኔታ ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም፣ ቆይቶ ግን ዕግዱን በማንሳቱ ቦታው ለጨረታ ቀርቧል፡፡
በመሆኑም በቀረበው 4,133 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ በተደረገው የጨረታ ውድድር፣ ቦታው በ39 ሚሊዮን ብር ለአንድ ባለሀብት ተሽጧል፡ ቦታውን የገዙት ባለሀብት ለመረከብ በመንቀሳቀሱ ላይ እያሉ፣ ‹‹አክሰስ ሪል ስቴት ቦታውን ወስዶ ግንባታ ሳይገነባ ከ18 ወራት በላይ አጥሮ በማስቀመጡ ካርታው መክኗል፡፡ ግንባታ ያላረፈበት ባዶ ቦታ በመሆኑም ባለቤቱ እኔ ነኝ፤›› በማለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት አስተዳደርና ግንባታ ባለሥልጣን ክስ መመሥረቱ ታውቋል፡፡
በሪል ስቴቱ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሚናገሩት በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ግን የአስተዳደሩን ክስ አጥብቀው ይቃወማሉ፡፡ ምክንያቱም እነሱ በደረሰባቸው ጉዳት አክሰስ ላይ ክስ መሥርተው ፍርድ ቤቱ ፍትሕ ከሰጣቸው በኋላ ምንም ሳይል ለዓመታት ቁጭ ብሎ የከረመው አስተዳደሩ አሁን እንቅስቃሴ በመጀመሩ ነው፡፡ መከሰስ ካለበትም አክሰስ ሪል ስቴት መሆን እንዳለበት የሚናገሩት ኢትዮጵያውያኑ፣ ሪል ስቴቱ መሠረት አውጥቶ ግማሽ ግንባታ ያካሄደበትን ቦታ ምንም እንዳልተገነባበትና ጊዜው እንዳለፈበት አስመስሎ ማቅረብ ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ የሚመለከተው የመንግሥት አካልና የፍትሕ ተቋሙም ይህንን ተገቢ ያልሆነ እንቅስቃሴ ሊያስቆምላቸው እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ አስተዳደሩ ያቀረበውን ክስ ተቀብሎ ለሚያዝያ 20 ቀን 2006 ዓ.ም. መቅጠሩንም ጠቁመዋል፡፡
በአቶ ኤርሚያስ አመልጋ የተመሠረተውና ይመራ የነበረው አክሰስ ሪል ስቴት በደል እንዳደረሰባቸው ሲናገሩ የነበሩት ከ2,000 በላይ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
በወቅቱ ሁሉም ተበዳዮች የሕግ ባለሙያዎችን ካነጋገሩ በኋላ የተወሰኑት ወደ ፍርድ ቤት ሲሄዱ፣ የተወሰኑት ደግሞ መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀው ነበር፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የቤቶች፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ባለሥልጣናት የተካተቱበት ኮሜቴ እንደተቋቋመና በቅርቡ መፍትሔ እንደሚያገኙ የተነገራቸው ቢሆንም፣ በጊዜ ብዛት ግን የሚያናግራቸው በማጣታቸው ግራ መጋባታቸውንና ወዴት ሄደው አቤት እንደሚሉ መላው ጠፍቷቸው በመንገላታት ላይ መሆናቸውን እየተናገሩ ናቸው፡፡