Latest blog posts

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ለሚገኙ አስሩም ክፍለ ከተሞች ለኔትወርክ ማስፋፊያ እንዲውል የተረከባቸውን የተለያዩ እቃዎች የመዘበረው የአስተዳድሩ የንግድ ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ ባልደረባ ዛሬ በሰባት አመት ፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ።

ወንጀለኛው በቢሮው የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደር ክፍል ውስጥ ይሰራ የነበረ ሲሆን፥ አያሌው በቀለ ይባላል።

የ42 አመቱ ጎልማሳ ሰኔ 2003 ዓ.ም ለአስሩም ክፍለ ከተሞች ኔትወርክ ማስፋፊያ ከተረከባቸው እቃዎች 282 ሺህ ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ እቃዎችን ለግል ጥቅም አውሏል።

በዚህ ጥፋቱ የፌደራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ በከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል ክስ መስርቶበት ጉዳዩ ሲታይ ቆይቶ ነው ዛሬ እልባት ያገኘው።

ተከሳሹ ከአቃቤ ህግ ማስረጃ በኋላ ባቀረበው የመከላከያ ማስረጃ የስራ መደቤ ገንዘብ ያዥ አይደለም፤ ያለአግባብ ነው ያስረከቡት፤ እንደዚያም ሆኖ ለአንድ አመት ያህል እቃው ጥቅም ሳይሰጥ መሰንበቱ ጥፋተኛ አስብሎኛል የሚሉና ሌሎች ምክንያቶችን አቅርቧል።

ግለሰቡ የንብረት ክፍል ሰራተኛ ሳይሆን እንዲረከብ ያደረገው የቅርብ ሀላፊው አቶ ሚልኪያስ መንገሻ የተባለው ግለሰብም ከዚህ በፊት ቅጣት ተላልፎበታል።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1 ወንጀል ችሎት ምንም እንኳን ያለ መደብህ ንብረት ብትረከብም፤ የተጣለብህን አደራ ወደ ጎን በመተው ለክፍለ ከተሞቹ ኔትወርክ ማስፋፊያ ይውል የነበረውን እቃ መመዝበርህ የወንጀሉን ደረጃ አነስተኛ አያሰኘውም ብሏል።

በዚህም የአቃቤ ህግ የቅጣት ማክበጃ ባያቀርብም፥ ግለሰቡ የቀደመ የወንጀል ሪከርድ የሌለበትና ቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት በሁለት የቅጣት ማቅለያዎች በሰባት አመት ፅኑ እስራትና በአራት ሺህ ብር ቀጥቶታል።


Editors Pick

Family Law Blog
  መግቢያ የሰው ልጆች በዚህ ምድር ላይ መኖር የጀመሩትና ማህበራዊ መስተጋብር እንድ ህብረተሰብ ክፍል ብሎም እንደ ሀገር መኖር የጀመሩበት ጊዜ እና ቦታ ላይ የታሪክ ሊቃውንት በእርግጥ ይሄ ጊዜና ቦታ ባይሉንም ረጅም ዘመናትን እንዳስቆጠሩ ይገልፃሉ፡፡ የአንድ ሀገር ወይም ማህበረሰብ መሠረት የሆነው ቤተሰብ እንደሆነ ...
52140 hits
Banking & Negotiable Instrument Law Blog
  Unlike the mainstreaming financial institutions, microfinance institutions play an important role in providing access to finance for rural farmers, small businesses, and other people who are engaged...
3248 hits
Labor and Employment Blog
  ከዚህ ቀደም በሀገራችን ኢትዮጵያ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይን የሚገዙ ሕጎች እንደነበሩ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ በ1955 ዓ.ም የወጣው የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 210/1955፣ በ1968 ዓ.ም የወጣው የሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 64/1968፣ የሠራተኛ ጉዳይ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 85/...
68467 hits
Criminal Law Blog
  መግቢያ የሥነ-ሥርዓት ሕግ ሰዎች መሠረታዊ የሆኑ የፍትሕ አቤቱታዎች ሲቀርቡ የሚመሩበትን እና መብቶች ጥቅሞችና ግዴታዎች በሚመለከታቸው የፍትሕ አካላት የሚወስኑበትንና ተፈፃሚ ሊሆኑ የሚችሉበትን ሥርዓት የሚያሳይ ጽንሰ ሀሳብ ነው። የሥነ-ሥርዓት ሕግ መብቶች ጥቅሞችና ግዴታዎች በምንና እንዴት ባለ አኳኋን ወደ ተግባ...
15768 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...