Abyssinia Law Abyssinia Law
  • Home
  • Laws
    • Federal Laws Database
    • Regional Laws
    • Constitutions
    • Audio Legal Resources
  • Decisions
    • Cassation Decisions by Volume
    • Cassation Decisions Database
    • FFI Court Commercial Bench Decisions
  • Blog
  • Resources
    • Researches Papers
    • Policies and Strategies
    • Codes, Commentaries and Explanatory notes
    • Legal Forms
    • Bench Books
    • Human Right Documents
    • Modules and Materials
    • About Our Laws
  • Study On-line
  • know your rights
  • Lawyers
  • Discussions
  • About Us
    • Who Are We
    • Our Partners
    • Advertise with Us
    • Privacy Policy
    • Professional Advice?
    • Contact us
    • How to submit a blog post
  • login
Michael Teshome

የግልግል ስምምነት /Arbitration Agreement/ እና የፍርድ ቤቶች ሥልጣን

በውሳኔው ሐተታ ላይ ‹‹…ይህ መርህ የግልግል ዳኛው የግልግል ዳኝነት ስምምነቱ ዋጋ ያለው መሆን አለመሆኑን በተመለከተ የሚነሳ ክርክር ጭምር ሰምቶ መወሰን እንዲችል ሥልጣን የሚሰጠው ቢሆንም ይህ መርህ… በአገራችን በከፊል ተቀባይነት ባለማግኘቱ በዚህ ድንጋጌ መሠረት በአገራችን የግልግል ዳኛ የግልግል ዳኝነት ስምምነቱ

Michael Teshome
Arbitration Blog
22 February 2023
Continue reading
Fesseha Negash Fantaye

ARTICLE REVIEW - Seyoum Yohannes, the Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration: the Extent of Party Autonomy

Including the abstract, introduction, and concluding remarks, the author’s work is structured into eight sections. The author used abstract and introduction to introduce readers to his work's content,

Fesseha Negash Fantaye
Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
22 April 2023
Continue reading
Nigussie Redae

የዋስትና መብት መከበር ላይ በፖሊስ የሚቀርብ የይግባኝ ጥያቄ ህጋዊ አንድምታው ሲገመገም

እንዳለመታደል ሆኖ የሀገራችን ተቋማት በእጅጉ በግልሰቦች እና በተለያዩ ፖለቲካዊ ተፅዕኖዎች ውስጥ የወደቁ በመሆናቸው የሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች አፈፃፀም ላይ ብዙ ጥሰቶች ሲፈፀሙ መቆየታቸው ማስረጃ የማይጠየቅበት እውነት ነው። ከእነዚህ የሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ውስጥ በኢፌዲሪ ህገመንግስት አንቀፅ 1

Nigussie Redae
Criminal Law Blog
03 May 2023
Continue reading
muluken seid hassen

ስለባልና ሚስት የጋራ እና የግል ንብረቶች በተመለከተ የፌዴራሉን የቤተሰብ ሕግና የተመረጡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎችን መሰረት በማድረግ የቀረበ

በዚህ ጽሑፍ ጋብቻ በተጋቢዎቹ የግልና የጋራ ንብረት ላይ ስለሚኖረው ውጤት እንዲሁም በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረት የግል ወይም የጋራ ሊባል ሲለሚችልበት የሕግ አግባብ፤ በተጋቢዎቹ መካከል የሚደረግ የስጦታ ውል ህጋዊ ውጤቱና የአደራረግ ስነ ስርዓቱ፣በትዳር ውስጥ የወጣ ወጪ ለትዳር ጥቅም ዋለ ሊባል ስለሚችልባቸውና የማ

muluken seid hassen
Family Law Blog
30 December 2022
Continue reading
Sesay Goa

ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ ዕይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ

ዳግም ኢጣሊያ ወረራ ፈፅሞ ለአምስት አመት ግዛቱን ባስተዳደረበት ጊዜና ኢጣሊያን በእንግሊዝ አጋዥነትና በሀገር ውስጥ በነበሩ አርበኞች ያላቋረጠ ትግል ከሀገር ሲባረር ስልጣን በቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ቁጥጥር ስር ቢገኝም የእንግሊዝ መንግስት አስተዳደር በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ፣ ፓሊቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ጣልቃ ገ

Sesay Goa
Criminal Law Blog
17 March 2023
Continue reading
Fasika Abera

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን - የሴቶች ጥቃት ችግር - ሴቶች

በእርግጥ ሁሉም ችግሮች እንደየደረጃቸው እና ጥልቀታቸው በጥናት የሚለዩ መሆኑን አምናለሁ። ይሁን እና ጥናትም ለማድረግ ችግሩ ባለቤት ሊኖረው የሚገባ ስለመሆኑ ደግሞ የምንግባባበት ነው ብየ አስባለሁ። ይህ እንዳለ ሆኖ ጥናትም ለማድረግ ቢሆን መጀመርያ ላይ መነሻ ሊኖረን የሚገባ ነው። ለዚህም ነው ከዚህ ጉዳይ ጋር በተ

Fasika Abera
Human Rights, Public Policy and Law Blog
17 March 2023
Continue reading

Latest Blog posts

Nigussie Redae
Nigussie Redae
03 May 2023
የዋስትና መብት መከበር ላይ በፖሊስ የሚቀርብ የይግባኝ ጥያቄ ህጋዊ አንድምታው ሲገመገም
Criminal Law Blog
መግቢያ በኢፌዲሪ ህገመንግስትም ይሁን ኢትዮጵያ በአፀደቀቻቸው አለማቀፋዊ የሰበዓዊ መብት ስምምነቶች እንዲሁም በሌሎች አዋጆች ላይ የተቀመጡ አያሌ የሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተፈፃሚነት እንዲኖራቸው በህግ እና በስርዓት የሚመሩ፤ ዋና ግባቸው እና የሥራ መለኪያቸው ህግ እና ሥርዓትን ማስከበር የሆኑ ተቋማት መኖራቸው ጥያቄ ውስጥ የማይገባ ቅድመ ሁኔታ ነው። እነዚህ ተቋማት እርስ በራሳቸው በ...
2097 Hits
Read More
Fesseha Negash Fantaye
Fesseha Negash Fantaye
22 April 2023
ARTICLE REVIEW - Seyoum Yohannes, the Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration: the Extent of Party Autonomy
Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
Seyoum Yohannes, the Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration: the Extent of Party Autonomy, Mizan Law Review, Vol. 10, No.2, December 2016, p. 341 - 365 (You may download this article from Here) The arbitration agreement ...
1703 Hits
Read More
Sesay Goa
Sesay Goa
17 March 2023
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ ዕይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ
Criminal Law Blog
መግቢያ ፡- ተበዳዮች በወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ የነበራቸው የተሳትፎ ሚና፡ ጥቅል ምልከታ በኢትዮጵያ የወንጀል ተጎጂዎች በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ውስጥ ያላቸው ሚና ከነበረበት የማማ ደረጃ በጊዜ ሂደት ‹‹ከማማ የመውረድ›› ያህል ዝቅ እያለ መጥቷል። ሀገሪቱ በዳግም የኢጣሊያ ወረራ ተፈፅሞባት ከመያዝዋ እ.እ.አ ከ 1935 ዓ.ም በፊት በወንጀል ጉዳት ደርሶባቸው በቀጥታ ተበዳይ የሆኑ ሰዎች ወይም ...
1871 Hits
Read More
Fasika Abera
Fasika Abera
17 March 2023
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን - የሴቶች ጥቃት ችግር - ሴቶች
Human Rights, Public Policy and Law Blog
እንኳን ለአለማቀፍ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ። ዛሬ የመጣሁበት ዋነኛ ምክንያት ከዚህ ቀን ማለትም ከአለማቀፍ ሴቶች ቀን እና አለማቀፍ ነጭ ሪቫን ቀን አከባበር ጋር በተያያዘ ሁል ግዜም በአይምሮዬ የሚመላለሱ ጥያቄዎች ስላሉኝ እነሱን ለማንሳት እና ከጉዳዩም ጋር ተያይዞ ከስራ እና በሕይወት የተረዳኋቸውን አንዳንድ ነጥቦች ለማካፈል ነው።...
1619 Hits
Read More

Editors Pick

Abyssinia Law | Making Law Accessible!
በኮሮና ወረርሽኝ ፍርድ ቤቶችን እንዴት ማስቀጠል ይቻላል?
Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
  እርግጥ ነው አሁን ያለንበት የኮሮና ቫይርስ ወረርሽኝ ወቅት እጅግ ፈታኝ፣ ፈጣን አስተዳደራዊ ውሳኔ ለመስጠት የሚከብድበት የቱ ትክክልየቱ ስህተት እንደሆነ ለማመዛዘን የሚቸግር ጊዜ ነው፡፡ በተለይም በወረርሽኙ ምክንያት የሰዎች ህይወት አደጋ ላይ መውደቁ ሲታይ አሳሳቢና አስጨናቂ ነው፡፡ በዛው መጠን ደግሞ በማዕበሉ...
4665 hits
Read More
Hawi Asfaw
Birth registration and rights of the child
About the Law Blog
{autotoc}   1 Introduction Birth registration is defined as the ‘official recording of a child’s birth by the State’. It is also a lasting and official record of a child’s existence, which usually inc...
7629 hits
Read More
Abyssinia Law | Making Law Accessible!
The Curious Case of Construction & Business Bank
Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
Businesses want to become big. They want their presence to be felt in every corner of the world. Investors explore different avenues to do this by injecting capital, selling equities, reinvesting thei...
8954 hits
Read More
Fantahun Mengiste
የኢትዮጵያ የብር ኖቶችና የባንኮች አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓተ-ልማድ ከአካል-ጉዳተኞች መብት አንጻር  
Banking & Negotiable Instrument Law Blog
  መግቢያ   በሀገራችን ከ20 ሚሊዮን  በላይ የአካል ጉዳት ያለባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደማንኛውም ሰው የተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት አገልግሎቶችን ለመጠቀም የተለያዩ መሰናክሎች ይገጥሟቸዋል፡፡ በዚህ ጽሑፍ አካል-ጉዳተኞች በኢትዮጵያ የብር ኖቶች አጠቃቀም እና በባ...
5356 hits
Read More

Latest documents

Education and Training Policy of Ethiopia - Amharic version - 2023
7262 Downloads  - policies and strategies
7.6 MB
The Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration - the Extent of Party Autonomy
218 Downloads  - Arbitration Law
635.59 KB
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25
8982 Downloads  - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions
10.72 MB
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ እይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ FEATURED
408 Downloads  - Criminal Law
317.19 KB
Federal Supreme Court Cassation Decisions - Table of content Volume 1-25
10517 Downloads  - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions
6.57 MB
Print Email
Details
Category: Legal News - የሕግ ዜናዎች

በውጭ ዜጋ ላይ ዝርፊያ በመፈጸም ወንጀል ተጠርጥረው በተከሰሱ የደኅንነት ሠራተኞች ላይ ምስክሮች መደመጥ ጀመሩ

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአገር ውስጥ ደኅንነት ሠራተኛ በሆኑት አቶ ዮሐንስ ኪሮስ አብዩና በአቶ በኩረ ጽዮን አብረሃ ዜና፣ እንዲሁም ሾፌር መሆኑ በተገለጸውና ተባባሪ ነው በተባለው የኑስ አብዱልቃድር መሐመድ ላይ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ያቀረባቸውን ምስክሮች መስማት የጀመረው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት መጋቢት 18 ቀን 2006 ዓ.ም. ነው፡፡

ክሱ እንደሚለው፣ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ከአሥር ወራት በፊት ግንቦት 14 ቀን 2005 ዓ.ም. ከምሽቱ 12፡30 ሰዓት ሲሆን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 19 ልዩ ቦታው ደንበል ሲቲ ሴንተር ሕንፃ አካባቢ፣ ሚስተር ካሊድ አዋድ የተባሉ የሳዑዲ ዓረቢያ ዜግነት ያላቸውን ግለሰብ ያገኟቸዋል፡፡ 

ግለሰቡን ሲፈትሿቸው 1,200 ዶላርና 1,600 የሳዑዲ ሪያል አግኝተው ከወሰዱ በኋላ፣ ወደ ካራማራ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው እንዳሳደሯቸው ክሱ ያስረዳል፡፡ በማግሥቱ ግንቦት 15 ቀን 2005 ዓ.ም. የግል ተበዳይን ቤታቸው በመውሰድ ቤታቸውን በመበርበርና የተቆለፈ ሳምሶናይት በመስበር 8,000 የሳዑዲ ሪያልና 2,000 ዶላር፣ በድምሩ ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲቀየር 106,880 ብር ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውንም በክሱ ተጠቁሟል፡፡

ሾፌር መሆኑ የተገለጸው የኑስ አብዱልቃድር የተባለው ተርጣሪ ደግሞ ከሁለቱ ተጠርጣሪዎች ጋር በመመሳጠር፣ የግል ተበዳይ የሆኑትን የሚስተር ካሊድ አዋድን ቦታና እንቅስቃሴ በመጠቆም፣ እንዲሁም የተሽከርካሪ አገልግሎት በመስጠትና በወንጀሉ ተሳትፎ በማድረግ 13,000 ብር ለግል ጥቅሙ ማዋሉን ክሱ ያብራራል፡፡

የደኅንነት ሠራተኞቹ የግል ተበዳይን በቁጥጥር ሥር ባዋሉበት ዕለት በግምት ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ሲሆን፣ የተበዳዩ ሠራተኛ መሆናቸው ለተገለጸ ግለሰብ ስልክ ደውለው 100 ሺሕ ብር ካልሰጧቸው ተበዳዩ እንደማይፈቱ መግለጻቸውን የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

በአጠቃላይ ተጠርጣሪዎቹ በዋና ወንጀል አድራጊነት ፈጸሙት በተባለው ገንዘብ ወስዶ መሰወርና ጉቦ መጠየቅ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው፣ ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ የሚያስረዱለትን ሦስት ምስክሮች ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡  

የዓቃቤ ሕግ የመጀመሪያ ምስክር ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዱት፣ ሾፌሩ ስልክ ደውሎላቸው 100 ሺሕ ብር ካልሰጧቸው ተበዳዩን እንደማይለቋቸው እንደገለጹላቸውና በድጋሚ ከደኅንነት ሠራተኛው በኩረ ጽዮን ጋር በመሆን የተጠየቀውን 100 ሺሕ ብር ወደ 80 ሺሕ እና 50 ሺሕ ብር ዝቅ በማድረግ እንደተደራደሯቸው መስክረዋል፡፡

ሁለተኛው ምስክር የግል ተበዳዩ ሲሆኑ፣ በክሱ ላይ የሰፈረውን ቃል በቃል አስረድተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ቀሪ ምስክር ለመስማት ለሚያዝያ 9 ቀን 2006 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ 

Ethiopian Reporter By Ethiopian Reporter
Ethiopian Reporter
Last Updated: 11 October 2022
Hits: 34887
Abyssinia Law | Making Law Accessible!
Abyssinia Law | Making Law Accessible!
  • Prev
  • Next
Copyright © 2023 Abyssinia Law | Making Law Accessible! . All Rights Reserved.
Maintained by Liku Worku Law Office