Latest Blog posts
Editors Pick
Latest documents
Education and Training Policy of Ethiopia - Amharic version - 2023 7258 Downloads - policies and strategies | 7.6 MB | |
The Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration - the Extent of Party Autonomy 200 Downloads - Arbitration Law | 635.59 KB | |
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25 8869 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 10.72 MB | |
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ እይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ FEATURED 402 Downloads - Criminal Law | 317.19 KB | |
Federal Supreme Court Cassation Decisions - Table of content Volume 1-25 10453 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 6.57 MB |
- Details
- Category: Legal News - የሕግ ዜናዎች
የሁለት ልጀቹን እናት በአስር ጥይቶች ተኩሶ በግፍ የገደለው ግለሰብ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈበት
ወንጀለኛው ወንደሰን ይልማ ጥፋቱን የፈፀመው ባለፈው ዓመት ጥቅምት አስር ከማለዳው ሁለት ሰዓት ላይ ነው ። በወቅቱ የሁለት ልጆቹ እናት የነበረችውን ሟች ወይዘሮ ፍሬህይወት ታደሰ የግል መኪናዋን ይዛ ወደ ባምቢስ መስመር ትጓዛለች።
ተከሳሽ ህጋዊ ፈቃድ የሌለው ክላሽ ጠመንጃ በግል መኪናው ውስጥ አስቀምጦ ይከታተላታል፤ ከዚያም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ኦሎምፒያ ካርቱም ሬስቶራንት በሚባል ስፍራ ይደርስባትና በመኪናው ቀድሞ በማለፍ መንገድ ይዘጋባታል።
መሳሪያውን በማውጣትም በማድረግ አስር ጥይቶችን ወደ ቀድሞ የትዳር አጋሩ በማርከፍከፍ፥ በአምስት የሰውነቷ የተለያዩ ክፍሎች ላይ ያረፉ ጥይቶች ሀይወት እንዲያልፍ አድርገዋል።
በመኪና ውስጥ የነበሩት ወላጅ እናቷ እና ጓደኛዋ ወይዘሮ ተናኘ ሀይለማርያም በዚህ ሌላ ተጨማሪ ጥይት ቢተኮስባቸውም ጉዳት ሳይደርስባቸው በስፍራው የነበሩ ሶስት ግለሰቦችን ግን ለሞት የማያደረስ አደጋ ደርሶባቸዋል።
አቃቢ ህግ ከነዚህ ጥፋቶች በመነሳት ፥ የግፍ ግድያን ጨምሮ ሰባት የተለያዩ ክሶችን በተከሳሹ ላይ መሰርቶበታል። የአቃቢ ህግ ማስረጃዎችም ክሱን በሚያረጋግጥ መልኩ ምስክርነት ስጠተዋል።
የዳግማዊ ሚኒሊክና ሌሎች የግል ሆስፒታሎችም ወይዘሮ ፍሬህይወት በርካታ ጥይቶች ተተኩሰውባት ህይወቷ ማለፉንና ሌሎችም የተተኮሰባቸው ጥይት ጉዳት እንዳደረሰባቸው የላኩት ማስረጃ በሰነድ ማስረጃነት ተቀባይነትን አግኝቷል።
ተከሳሹ በበኩሉ ከናፍቆት የተነሳ ልጆቼን እንድታሳየኝ በዕለቱ ተከታትዬ ሄጄ ብጠይቃት ያልተገባ መልስ ስለሰጠችኝ እርምጃውን ወስጄባታለሁ፤ ነገር ግን በልጆቼ ናፍቆት የተነሳ አዕምሮዬ በመነካቱ ለህክምና ሁሉ ደርሼ ነበር ብሎ አስረድቷል።
የህክምና እርዳታ አደረጉለት የተባሉት አንድ ሀኪም በችሎቱ ተገኝተው ለተከሳሹ የህክምና እርዳታ እንዳደረጉለትና በሰዓቱ የመጨናነቅ ስሜት እንደሚታይበት በመግለፅ በሁለተኛ ቀጠሮ እንዲገኝ ነግረውት እንደነበር ገልፀዋል።
ሆኖም በዚያው ሳይመጣ ቀርቷል ብለዋል ለችሎቱ። የአዕምሮ ህመም በአንድ ቀን ህክምና እንደማይታወቅ እና እርዳታውን ያደረጉለት ወንጀሉ ከመፈፀሙ አንድ ዓመት አስቀድሞ መሆኑን ነው ያስረዱት።
የአዕምሮ ህመምተኛ ነኝ በሚል ሽፋን ከተጠያቂነት ወንጀሉን በክሱ መሰረት አልፈፀምኩም ለማለት የተደረገ ጥረት ነው በማለት ጉዳዩን ሲመለከት የነበረው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ የወንጀል ውድቅ በማድረግ በሰባቱም ክሶች ሙሉ በሙሉ ጥፋተኛ ነህ ብሎታል። ጥፋተኛ ካሰኙት ክሶች መካከል በሌሎች ግለሰቦች ላይ ተራ የመግደል ሙከራ ወንጀል ከአምስት እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣው ሲሆን፥ በልጆቹ እናት ላይ የፈፀመው የግፍ ግድያ ከእድሜ ልክ እስከ ሞት ቅጣት ሊያስፈርድበት እንደሚችል በአገሪቱ የወንጀል ህግ ላይ ሰፍሯል።
ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገኖች የቅጣት አስተያየት ተቀብሎ ውሳኔ ለመስጠት ለመጋቢት 25 2006 ዓመተ ምህረት ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል። ተከሳሽና ሟች ወይዘሮ ፍሬህይወት ታደሰ ሁለት ልጆች በጋራ የወለዱ ሲሆን፥ በወቅቱ ተፋተው ይኖሩ ነበር።