Latest blog posts

በህገ ወጥ የመኖርያ ቤት ማህበር ስም 460 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ተሳትፎ አድርገዋል የተባሉ አንድ የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አባል በሶስት ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጡ።

ለቅጣት ያበቃቸው ወንጀል በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ትዕግስት ለፍሬ በተባለ ህገወጥ የመኖሪያ ቤት ማህበር ስም 460 ካሬ ሜትር ቦታ በመመዝበራቸው ነው።

የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቢ ህግ ስልጣንን ያለ አግባብ መጠቀምና መንግስታዊ ሰነዶችን በሀሰት ማዘጋጀት በሚሉ የሙስና ወንጀሎች በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ማህበራት ማደራጃ ኦፊሰር የነበሩት አቶ አሊ መሀመድን ፣ አቶ ሙባረክ አብደላን እና ዛሬ ጥፋተኛ ተብለው የተፈረደባቸውን ሻለቃ አብረሃ ግደይን ከሷቸው ነበር።

ተከሳሾቹ ማንነታቸው ካልታወቁ የክፍለ ከተማው ማህበራት ማደራጃ ጋር በመመሳጠር የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ያልሆኑ 12 ግለሰቦች ሀሰተኛ መታወቂያ በማውጣት ማህደራቸው በህገወጥ መንገድ ህጋዊ ሰነድ እንዲሆን በማድረግ 460 ካሬ ሜትር ቦታ ለራሳቸውና ለተለያዩ ግለሰቦች እንዲያውሉ አድርገዋል የሚለው በክሱ ተጠቅሷል።

እኝህ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ከአባልነት እስከ አመራርነት ተሳትፈው በጡረታ ላይ ይገኙ የነበሩት ሻለቃ አብርሃ ግደይ በምዝበራው ውስጥ ከነበራቸው ተሳትፎ ባሻገር የህገወጥ ማህበሩ አባላት ውክልና አለኝ በማለት ከ10 ሰዎች ከእያንዳንዳቸው 75 ሺህ ብር መቀበላቸውም ተረጋግጧል።

ከእሳቸው ውጭ የነበሩት ሁለት ተከሳሾች ቀደም ብሎ በነፃ የተሰናበቱ ሲሆን ግለሰቡ ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ጥፋተኛ መባላቸውን ተከትሎ ያቀረቡትን አራት የጥፋት ማቅለያዎችን የተቀበለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ በሶስት አመት ፅኑ እስራት ቀጥቷቸዋል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በህገወጥ መንገድ የተያዘው 460 ካሬ ሜትር ቦታ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ታዟል።


Editors Pick

Family Law Blog
{autotoc}   1. መግቢያ ቤተሰብ የአንድ ማኅበረሰብ በጣም ጠቃሚ እና መሠረት የሆነ አካል ነው፡፡ ቤተሰብ አንድ ግለሰብን ከአጠቃላይ ማኅበረሰብ ጋር የሚያገናኝ ታላቅ ድልድይ ነው፡፡ እንዲሁም ተፈጥሮዊ ኢኮነሚያዊ እና ማኅበረሰባዊ ጥቅም አለው፡፡ በእርግጥ ቤተሰብ በቁጥር ትንሽ ሊሆን ይችላል ነገረግን የአንድ ቤ...
17459 hits
Human Rights, Public Policy and Law Blog
The best interest principle is one of the umbrella principles embodied under the CRC which assures the overall development of children to their fullest potential in order to maximize their capacity an...
8635 hits
Others
መቸም አሁን ለእናንተ ላወጋችሁ ያሰብኩትን ነገር በድሮ በዚያ በጥንት ጊዚያት ለነበሩ ሰዎች ብተርክላቸው ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ይሉኝ እንደነበረ አምናለሁ፡፡ ይህንን ጽሁፍ በተለያየ መልኩ አግኝታችሁ ወይም ያነበቡት አጋርተዋችሁ ስለዚህ ጉዳይ በደንብ የምታውቁ መኖራችሁ እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ አንዶቻችሁ ግን ...
8750 hits
About the Law Blog
ስለሪጉላቶሪ መሳሪያዎች መግቢያ ዛሬ የብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለሁለት ብሮድካስተሮች ጽፈውታል የተባለ ደብዳቤ በፌስቡክ መለጠፉን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተስተናገዱ ነው። በደብዳቤው ብሮድካስተሮቹ ለምን የቅዳሜውን የድጋፍ ሰልፍ እንዳላስተላለፉ መረጃ በተጠቀሰው ቀን ይዘው በመምጣት ከባለሥልጣ...
7763 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...