Latest blog posts

በእስልምና ሀይማኖት ስም የሽብር ድርጊት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉ አራት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ12 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጡ።

ተከሳሾቹ በደቡብ ትግራይ ዞን፥ ራያ አላማጣ ወረዳ የዋጃ ጥሙጋ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ፥ ሀቢብ ደረሰ ጓንጉል፣ ኢድሪስ ለጋስ መሀመድ፣ መምህር ከድር አደም እድሪስና አብዱልለጢስ ሀሸም ጉባለ የተባሉ ናቸው።

ተከሳሾቹ የእስልምና ሀይማኖትን ሽፋን በማድረግ በአካባቢው የሚገኙ የመንግስት ተሿሚዎች ከስልጣን ይውረዱ፣ የእስልምና ምክር ቤት አባላትን የመንግስት ጉዳይ አስፈፃሚዎች ናቸው እኛን የሚወክሉ አይደሉም፣ በእስልምና ሀይማኖት  ስም የታሰሩ ዜጎች ይፈቱ የሚሉ ጥያቄዎችን በመያዝ 60 የሚሆኑ ሰዎች አካባቢውን ሲረብሹ ነበር ብሏል አቃቤ ህግ።

በዚህም መሰረት የትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ አቃቢቤ ህግ፥ በተከሳሾቹ ላይ በህዝብ የተመረጡ የመንግስት አካላትን በሀይል ለማውረድና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለማፍረስ ሞክረዋል በማለት ክስ መስርቶባቸዋል።

ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ክስ ቢክዱም ማስተባበል ባለመቻላቸው፥ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ብሏቸዋል።

በዚህም መሰረት እያንዳንዳቸው በ12 ዓመት ፅኑ እስራት ሲቀጡ ፥ በዚህ መዝገብ ክስ ውስጥ ሌሎች አመስት ተከሳሾች ከቀረበባቸው ክስ ነፃ በመሆናቸው በነፃ ተሰናብተዋል።


Editors Pick

Criminal Law Blog
በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 145 ላይ አንድ ምስክር በፖሊስ ምርመራ ወቅት የሰጠው ቃል ዓቃቤ ሕግ ወይም ተከሳሹ ባመለከተ ጊዜ የተሰጠውን ምስክርነት ፍርድ ቤቱ ሊመለከተው እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ ይህ መብት የተሰጠው ለዓቃቤ ሕግ እና ለተከሳሽ በእኩል ደረጃ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ በሚባል አኳኋን እየተጠቀመ...
16841 hits
Criminal Law Blog
  ጠቅላላ የዚህ ጽሑፍ ርዕስ ምንም እንኳ የወንጀል ኤኮኖሚክስ ቢልም፤ እንዲሁም ይህ ጽሑፍ የተጠቀመባቸው የጥናትና ምሁራዊ ጽሑፎች የኖቤል ሎሬት ጌሪ ቤከር የጀመረውና በሌሎች ምሁራን የዳበረው የጥናት ክፍል የወንጀል ኤኮኖሚክስ በመባል ቢጠራም፤ በጽሑፉ የሚነሱት ዋና ዋና ነጥቦች በአጠቃላይ በቅጣት ለማስፈጸም የሚሞከ...
13911 hits
International Law Blog
  1.    ስለዓለም አቀፍ ሕግ በአጭሩ ዓለም አቀፍ ሕግ በሉዓላዊ አገሮች መካከል ያለን ግንኙነት ወይም በአገሮችና እንደተባበሩት መንግሥታት ያሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መካከል ያለን ግንኙነት የሚገዛ የሁሉ አቀፍ ደንቦች እና መርሆዎች ሥርዓት ነው። በሌላ አነጋገር «International law is the univer...
15445 hits
Others
Beginning in the early 1990s, Africa in general and the Greater Horn in particular, have been experiencing a major ground swell of social, economic, cultural and political changes. While the movement ...
4359 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...