Latest blog posts

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከወንድሞቻቸው ጋር በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የአገር ውስጥ ድኅንነት ኃላፊ አቶ ወልደ ሥላሴ ወልደ ሚካኤል እህት፣ ወ/ሪት ትርሐስ ወልደ ሚካኤል የፌደራል ማረሚያ ቤት ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን እንደነፈጋቸው የካቲት 13 ቀን 2006 ዓ.ም. ለፍርድ ቤት ተናገሩ፡፡

ወ/ሪት ትርሐስ በጠበቆቻቸው አማካይነት ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት እንዳስረዱት፣ ባለቤታቸው የውጭ አገር ዜጋ መሆናቸውን በማስረዳት በስልክ እንዲያገናኟቸው የማረሚያ ቤቱን ኃላፊዎች ሲጠይቁ መከልከላቸውን፣ ነገር ግን ለሌሎች እንደሚፈቀድ አመልክተዋል፡፡

ባቢ አንጄሎ የተባሉ የውጭ አገር ዜጋ የሆኑት ባለቤታቸው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ፈቃድ ጠይቀውና አስፈቅደው፣ እንዲሁም የፈቃድ ወረቀት ይዘው ማረሚያ ቤት ቢሄዱ እንደተከለከሉ የገለጹት የወ/ሪት ትርሐስ ጠበቆች፣ እንዲያውም በወ/ሪት ትርሐስ ምክንያት ለሌሎችም ክልከላ መደረጉን ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡

ባለቤታቸው በችሎት ተገኝተው ወደመጡበት ጣሊያን የሚመለሱት የካቲት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. መሆኑን በማስረዳት፣ ፍርድ ቤቱ በችሎት ስለወለዱት ልጅ እንዲነጋገሩ አንዲፈቅድላቸው ጠይቀዋል፡፡

በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳዳር፣ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የሴቶች ማረሚያ፣ ማረፊያና ጥበቃ ደኅንነት ዘርፍ አስተባባሪ ሱፐር ኢቴንዴንት ለተእግዚአብሔር ገብረመድኅን በችሎት ቀርበው እንዳስረዱት፣ ወ/ሪት ትርሐስ ‹‹ተከልክያለሁ›› የሚሉት ከእውነት የራቀ መሆኑን ነው፡፡ ማንም ቢሆን ከውጭ አገር በሕጋዊ መንገድ መግባቱን የሚገልጽ ደብዳቤ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይዞ ወደ ማረሚያ ቤቱ ከቀረበ፣ እንደማንኛውም ዜጋ እንደሚስተናገድ አስረድተዋል፡፡

የውጭ ዜጋ በስልክ እንዳይገናኝ ለምን አንደተከለከለ ጠይቋቸው በሰጡት ምላሽ፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባፀደቀው ደንብ ቁጥር 138/99 አንቀጽ 13 (1እና2) መሠረት ማንኛውንም ዜጋ እንደማያስተናግዱ፣ ስልክን በሚመለከት ደንቡ ስለማያካትት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካልታከለበት በስተቀር እንደማያገናኙ አስተባባሪዋ ገልጸዋል፡፡

የወ/ሮ ትርሐስ ባለቤት በሕጋዊ መንገድ መግባታቸው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል መረጋገጡ ተገቢ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በመግለጽ፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጻፈላቸውን ደብዳቤ እንዲያቀርቡ ጠይቋል፡፡

ያልተሟሉም ቢሆን በቀረቡት ማስረጃዎች ወ/ሪት ትርሐስና ባለቤታቸው ልጅ መውለዳቸውን የሚያረጋጥ ሰነድ  መኖሩን፣ ባልና ሚስትም ናቸው ማለትም እንደሚቻል በመግለጽ፣ ለአሥር ደቂቃ ያህል እንዲነጋገሩ ችሎቱ በመፍቀዱ ሊገናኙና ሊነጋገሩ ችለዋል፡፡

የእነ አቶ ወልደ ሥላሴ የክስ መዝገብ ለየካቲት 13 ቀን 2006 ዓ.ም. ተቀጥሮ የነበረው፣ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ በመዝገቡ 11ኛ ክስ ላይ የነበረውን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ የነበረ ቢሆንም፣ ዓቃቤ ሕግ ‹‹ቢሮ ውስጥ ጠረጴዛ ላይ ረስቼው ስለመጣሁ ከሰዓት በኋላ ከመዝገቡ ጋር አያይዛለሁ›› በማለቱ ፍርድ ቤቱ፣ ‹‹ይህም ነገር በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ነው ጥንቃቄ አድርጉ፤›› በማለት አስጠንቅቆ፣ ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝና የተጠርጣሪ ጠበቆችም ከጽሕፈት ቤት እንዲወስዱ በመንገር ለየካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡


Editors Pick

About the Law Blog
  Introduction The federal court proclamation no 25/96 its amendment, which has been in force for many years, is repealed and replaced by the federal courts' proclamation number 1234/2021.  When we se...
5409 hits
About the Law Blog
ያው ጉባኤው የሚለውን ርእስ መኮረጄ ነው እየመረጥክ ከዘገብክ የገለልተኝነት እና የእኩልነትን መርህ ጥሰሃል፡፡ /በበውቀቱ እስታይል/ ተከታዮ የመጀመሪያ አንቀፅ ለአገላለፅ ውበት እንጅ በጉዳዩ ላይ ያለኝ መቆጨት እንዳገላለፁ አለመሆኑ ይታወቅልኝ፡፡ የኢትዮጵያ ፕሮድካስቲንግ ባለስልጣል ለኢ ኤን ኤን የቴሌቪዚን ጣቢያ የ...
7112 hits
Human Rights, Public Policy and Law Blog
1. Introduction The purpose of this piece is to highlight the link between good governance and democracy. Through an examination of the key components of both, it argues that the two concepts are inde...
14277 hits
Others
ሰላም እንዴት ናችሁ፡፡ በባለፈው ጽሁፌ የሳይበር ክልልና የሀገሮች የለአላዊነት ስልጣን እስከ ምን ድረስ? በሚል ርእስ አንድ ጽሁፍ አስፍሬ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ለዛሬ ደግሞ የሳይበር ክልል ለመቆጣጠር ሀገሮች በመከተል ላይ ያሉት መርህዎች ምን ይመስላል? የሚለውን ለማየት እሞክራለሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሀለፎም ሃይሉ ...
7771 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...