Latest blog posts

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በግለሰቦች መኖሪያ ቤት ገብተው የጦር መሳሪያ በመያዝ የዝርፊያና የግድያ ወንጀል የፈፀሙ ሶስት ግለሰቦች ከ9 እስከ 30 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ።

አቃቢ ህግ በእነአንዳረጌ ጥላሁን የክስ መዝገብ አምስት ግለሰቦችን ነው  በከባድ የውንብድና ወንጀል ክስ መስርቶባቸው የነበረው።

ተከሳሸቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ህይወቱ ያለፈው አንደኛ ተከሳሽ የሰሜን ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ነዋሪ የነበረው አንዳረጌ ጥላሁን ፣ የቦሌው ፍስሃ ሻረው ፣ የሰሜን ወሎ ዞን ሳይንት ከተማ ኗሪው ይመኑ አዳነ ፣ የአቃቂ ቃሊቲው መለሰ ሞገስ እና የቦሌው መርጊያ ሽመልስ ናቸው።

በ2003 ዓ.ም ሽጉጥ እና ሌሎች የጦር መሳያዎች ይዘው ቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 10 አብሽሮ ህንፃ በሟች ዶክተር  መሀሙድ መሀመድ ቤት ነው የውንብድና ተግባራቸውነ አንድ ብለው የጀመሩት።

በዚሁ ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበሩትን ሰባት ሰዎች እንገላችኋለን በማለት አስፈራርተው እንዳይጮሁ በማስጠንቀቅ የተለያዩ ሞባይሎችን ጨምሮ የአንገትና የጆሮ ወርቆችን የወሰዱ ሲሆን ፥ የቤቱ ባለቤት ዶላር አምጣ ብለውት የለኝም ሲላቸው ከምሽቱ 5 ስዓት ተኩል በሽጉጥ ገድለውት ተሰውረዋል።

በዚሁ ዓመት ከወራት በኋላ ሌላኛው የጥቃት ኢላማቸውን ወ/ሪት ወርቅአበባ በሚባሉ ግለሰብ ቤት አድርገገው ፤ ምሽት ሁለት ስዓት ሲሆን በዚሁ ቤት ኡዚ ጠመንጃና ስታርተር ሽጉጥ ይዘው በመግባት በቤት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ግለሰቦችን በሰደፍና በዱላ በመደብደብ ጥሬ ብር ፣ የተለያዩ ወርቆችንና የሞባይል ስልኮችን ወስደዋል።

ይህ አልበቃ ብሏቸው ወይዘሮዋን  ከደበደቡ በኋላ የሚተኙበትን ፍራሽ ገልብጠው ሽጉጥ እስከነ 12 ጥይቶቹ ወስደዋል።

በዚያው ዓመት ሰኔ ወር ላይ ቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተሰብ ባርና ሬስቶራንት ውስጥ እየተዝናኑ በማምሸት ከሌሊቱ 6 ሰዓት ሲሆን ከሌሎች ደንበኞች ጋር ግጭት በመፍጠራቸው ሬስቶራንቱ  ይዘጋል ፤ ነገር ግን ተመልሰው በር ሰብረው በመግባት ከ24 ሺህ ብር በላይ ዘርፈው የሬስቶራንቱን ስራ አስኪያጅና ባልደረቦቹን ደብድበዋል ።

በዚህ ክፉ ተግባራቸው ተሰውረው የነበሩ እነዚህ ወንጀለኞችን  ፖሊስ ከተሸሸጉበት ይዟቸው በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።

አቃቢ ህግ ከዚህ በመነሳት በከባድ የውንብድና ወንጀል ክስ በመመስረት ፥ መዝገቡን ሲመረምር የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ የወንጀል ችሎት ክሳቸው ከተቋረጠባቸው አንዳረጌ ጥላሁንና 5ኛ ተከሳሽ መርጊያ ሽመልስ ውጪ ሌሎቹን በእስራት ቀጥቷቸዋል።

በዚህ መሰረት በተደራራቢ ክሶች የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎበት የነበረው 2ኛው ተከሳሽ ፍስሃ ሻረው ተደማምሮበት በ30 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥቷል።

ይህ ተከሳሽ ምንም እንኳን ከፍተኛ የወንጀል ተሳትፎ ቢኖረውም በአካል ተገኝቶ ክርክር አድርጎ የቅጣት ማቅለያ ባለማቅረቡ ነው የ30 ዓመት ፅኑ እስራት የተላለፈበት።

ፍርድ ቤቱ በግብር አባሮቹ ኢመኑ አዳነና መለሰ ሞገስ ላይም በእያንዳንዳቸው ላይ የ9 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ ፥ በሌለበት ውሳኔ በተሰጠው 2ኛ ተከሳሽ ፍስሃ ሻረውም የፌደራል ፖሊስ አፈላልጎ የእስራት ቅጣቱን እንዲፈፀም አዟል።


Editors Pick

Family Law Blog
  1. መግቢያ ግዴታ ህጋዊ ግንኙነት ሲሆን መሰረታዊ መርሁም የሚያካተው አንድ ዕዳ ያለበት ሰው ወይም ባለዕዳ ለአበዳሪው ዕዳውን የሚፈጽምበት ሂደት ነው፡፡ በዚህ ግንኙነት ውስጥ ባለዕዳው ለአበዳሪው አንድን ነገር ለማድረግ ፣ ለመስጠት ወይም ላለማድረግና ላለመስጠት የሚያደርገው ህጋዊ ግዴታ ነው፤ በተቃራኒው ደግሞ አ...
12141 hits
Criminal Law Blog
ፍርድ ቤት ቅጣት ማቅለያን ወይም ማክበጃን በሌላ ማቅለያ ወይም ማክበጃ ቀይሮ ማቅለል ወይም ማክበድ ይችላል? የቅርብ ጓደኛው ጋር ተጠግቶ ይኖር የነበረ ግለሰብ፣ ጓደኛው በሌለበት አሳቻ ሰዓት 10000 ብር የሚገመት ቶሺባ ላፕቶፕ ወስዶ ለግል ጥቅሙ አውሏል በሚል የወንጀል ሕግ አንቀጽ 665(1)በመተላለፍ በስረቆት ወ...
10080 hits
Criminal Law Blog
 ወስላትነት በኢትዮጵያ ሕግ ምን ማለት ነው   በአንድ ወቅት በፌደራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በታየ የስርቆት ወንጀል ጉዳይ ተከሳሹ ድርጊቱን መፈፀሙ ተረጋግጦ ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ፣ የቅጣት አስተያየቱን እንዲሰጥ የተጠየቀው ዐቃቤ ሕግ ‹‹…ተከሳሽ ድርጊቱን የፈፀመው መጥፎ አመልን በሚያሳይ ሁኔታ በወስላታነት…››...
11111 hits
About the Law Blog
በኅብረተሰብ ጤና ዘርፍ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሚባል ለውጥ ካስመዘገቡ አገሮች ተርታ ትመደባለች፡፡ የጤና አገልግሎትን በቀበሌ ደረጃ ለማስፋፋት፣ በተለይም በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የኅብረተሰብ ክፍል ማዕከል ያደረገና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና የተቸረውን የጤና ኤክስቴንሽን መርሐ ግብር ተግባራዊ በማድረግ...
8209 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...