Latest blog posts

-ከዘውዲቱ ሆስፒታል ጋር በተገናኘ በ14.9 ሚሊዮን ብር ተጠርጥረዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊን ጨምሮ፣ አምስት በተለያዩ ከፍተኛ ኃላፊነቶች ላይ የነበሩና ሁለት ግለሰቦች ከዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል እድሳት ጋር በተገናኘ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ከሆስፒታሉ ዕድሳት ጋር በተገናኘ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘትና ለማስገኘት ወይም በሌላ መብትና ጥቅም ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ፣ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ጠርጥሮ ክስ የመሠረተባቸው፣ አቶ ዮሴፍ ኃይለ ማርያም አርጋኖ የአስተዳደሩ የዲዛይንና ግንባታ አስተዳደር ልማት ቢሮ የግንባታ ንዑስ የሥራ ሒደት ባለቤት፣ አቶ ዮናስ አያሌው የዲዛይንና ግንባታ አስተዳደር ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ፣ ሂሩት አያሌው የመሠረተ ልማት ግንባታ ባለሥልጣን የውል አስተዳደር ቲም ሠራተኛ፣ ገነት ጌታቸው የሆስፒታሉ ሕንፃ ዕድሳት ኮሚቴ አባል፣ አምባዬ አክሊሉ የኮንስትራክሽንና መሠረተ ልማት ቢሮ ሥራ አስኪያጅ፣ አቶ ግርማ በነበሩ የዲዛይንና ግንባታ አስተዳደር ልማት ቢሮ ተቆጣጣሪ መሀንዲስና የሆስፒታሉን ሕንፃ ለማደስ የተስማማው ተክለ ሃይማኖት አስገዶም ሕንፃ ተቋራጭ ባለቤት አቶ ተክለ ሃይማኖት አስገዶም ተድላ ናቸው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የተመሠረተባቸውን የሙስና ወንጀል ክስ እንዲመረምር ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የቀረበለት ክስ እንደሚያስረዳው፣ ተጠርጣሪዎቹ የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ሕንፃ ዕድሳት የዋና ጨረታ ኮሚቴ አባል፣ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት፣ ሥራ አስኪያጅና ተቋራጭ ነበሩ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከ2000 ዓ.ም. ጀምሮ በእድሳት ላይ የነበረውን የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ሕንፃን በተሰጣቸው የማጫረት ኃላፊነት፣ በመንግሥት ግዥ ሕግና ሥርዓት መሠረት የቴክኒክና የፋይናንስ ግምገማ ሳያደርጉ፣ የፋይናንስ ግምገማ ብቻ በማድረግ፣ ጉዳዩ በበላይ ኃላፊ ወይም በመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ ተመርምሮ ውሳኔ መሰጠት ሲገባው፣ የቴክኒክ ግምገማ አለመደረጉ እየታወቀ ያላግባብ የተላለፈውን የጨረታ ኮሚቴ የውሳኔ ሐሳብ በማፅደቅ ኮንትራክተሩ እንዲያሸንፍ ማድረጋቸውን ያብራራል፡፡ 

በሆስፒታሉ ሕንፃ ላይ ከፍተኛ የሆኑ የዕድሳት ችግሮች እንዲከሰቱና ጥራታቸው ዝቅተኛ የሆኑ ዕቃዎችን ኮንትራክተሩ እንዲጠቀም በማድረጋቸው፣ በፈጸሙት በዋና ወንጀል አድራጊነትና በልዩ ወንጀል ተካፋይነት ሥልጣንን ያላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል መከሰሳቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ 

ኮንትራክተሩ ተገቢ የሆኑና ጥራታቸውን የጠበቁ ዕቃዎች እንዲገጠሙና ትክክለኛውን አሠራር የተከተለ ዕድሳት እንዲደረግ ተገቢ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ሲገባቸው፣  የሕንፃው ዕድሳት በአግባቡ ሳይከናወን የክፍያ ምስክር ወረቀት በመስጠት፣ ሌሎች ያልተሠሩ የሲቪል፣ የኤሌክትሪክና የሳኒተሪ ሥራዎች እያሉና በውሉ መሠረት ተገቢውን የአሠራር ሥርዓት የተከተለ አሠራር ሳያከናውኑ 14,955,05 ብር ክፍያ እንደተፈጸመላቸው በማብራራት፣ ተጠርጣሪዎቹ በሙስና ወንጀል መከሰሳቸውን የክስ ቻርጁ ያብራራል፡፡ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ዘጠኝ የሰውና ዘጠኝ የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦባቸዋል፡፡ 


Editors Pick

Commercial Law Blog
  መግቢያ    ቼክ በተግባር በሰፊው ከሚሰራባቸውና በሕግ ከተቀመጡት ንግድ ሰነዶች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡  በቼክ ላይ እምነት የሚታጣበት ከሆነ የንግድ ዝውውር ደህንነት (security of transaction) ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ የንግድ ሥራው እያደገ በመጣ ቁጥር በቼክ የሚደረጉ ...
20187 hits
Human Rights, Public Policy and Law Blog
One of the many things globalization is credited for is that it has “considerably weakened traditional governance processes,” according to Professor Charnovitz Steve, a well-known writer on non-state ...
10702 hits
Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
በተለምዶ የሕግ ባለሙያዎች በንግዱ ዘርፍ ለሚንቀሳቀሱት ተወዳዳሪ ኃይሎች የተጋለጡ አልነበሩም፡፡ ይህ በሲቪል ሎው የሕግ ሥርዓት ተከታይ ሃገራት በአድቮኬቶችና ላቲን ኖታሪዎች እንዲሁም በኮመን ሎው የሕግ ሥርዓት ተከታይ ሃገራት በባሪስተሮች፣ ሎሊሳይቶሮች እና ኮንቬሮች መካከል ተመሳሳይ እውነታ ነበር፡፡ በእነዚህ በሁለ...
13062 hits
Labor and Employment Blog
  ዓለማችን ላይ የፈረንጆቹ 2020 የተወሳሰቡ ችግሮችን ይዞባት መጥቷል፡፡ ከቻይና ውሃን በትንሹ ተነስቶ በወራት ውስጥ ዓለምን ካዳረሰው የኮሮና ቫይረስ የሚስተካከል ችግር ግን ይመጣል ብሎ የገመተ አልነበረም፡፡ ይህ ቫይረስ በቀጥታ በሰው ልጆች ጤና እና ህይዎት ላይ እያሰከተለ ከሚገኘው ኪሳራ እና ውድመት በሚስተካከ...
6917 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...