Latest Blog posts
Editors Pick
Latest documents
Education and Training Policy of Ethiopia - Amharic version - 2023 7126 Downloads - policies and strategies | 7.6 MB | |
The Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration - the Extent of Party Autonomy 164 Downloads - Arbitration Law | 635.59 KB | |
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25 8110 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 10.72 MB | |
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ እይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ FEATURED 350 Downloads - Criminal Law | 317.19 KB | |
Federal Supreme Court Cassation Decisions - Table of content Volume 1-25 9980 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 6.57 MB |
- Details
- Category: Legal News - የሕግ ዜናዎች
ሐሰተኛ ሰነዶችን እያዘጋጀ ሲሸጥ የተደረሰበት ግለሰብ በ10 ዓመት ፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ
የጨርቆስ ክፍለከተማ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ሐሰተኛ ሰነዶችን እያዘጋጀ ሲሸጥ ተደርሶበታል ባለው ግለሰብ ላይ የ10 ዓመት ፅኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት አስተላለፈ።
በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ደንበል ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነዋሪ የሆነው ወንጀለኛ ጀማል አወል የሚባል ሲሆን ፥ ግለሰቡ ሐሰተኛ ሰነዶችን እያዘጋጀ እንደሚሸጥ ከህብረተሰቡ ህዳር 16 ቀን 2006 ዓም ለጨርቆስ ክፍለከተማ ፖሊስ መምሪያ ጥቆማ ይደርሳል።
ጥቆማውን ተከትሎም ፖሊስ መምሪያው አስፈላጊውን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማውጣት በግለሰቡ ቤት ባደረገው ፍተሻ ፤ ተጠርጣሪው በመኖሪያ ቤቱ ሐሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት ላይ እንዳለ እጅ ከፍንጅ ይያዛል በፖሊስ አባላቱ።
በ50 የተለያዩ ግለሰቦች ስም የተዘጋጁና ከመንግስት መስሪያ ቤቶችና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እንደተሰጡ የሚያረጋግጥ ማህተም የተመታባቸው ሐሰተኛ ሰነዶችም ይገኛሉ በግለሰቡ መኖሪያ ቤት።
የንግድ ስራ ፈቃድ ሰርተፍኬት ፣ የዩኒቨርስቲ መግቢያ የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የትምህርት ማስረጃ ፣ ከተለያዩ ቀበሌዎች የተሰጡ የልደትና የጋብቻ ማስረጃዎች ፣ የተለያዩ ደረጃ ያላቸው መንጃ ፈቃዶች ፣ የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የምዝገባ የምስክር ወረቀትና ሌሎችም ከተገኙት የሃሰት ማስረጃዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።
ከዚህም አልፎ የመከላከያ ሚኒስቴር ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ የንግድ ሚኒስቴር ፣ የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ፣ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ፣ ተመሳስለው የተዘጋጁ ክብ ማህተሞች በግለሰቡ ቤት ተገኝተዋል።
ኮምፒውተር ካሜራና ሌሎች የሐሰተኛ ሰነዶቹን የሚያዘጋጅባቸው ግብዓቶችም በግለሰቡ ቤት መገኘቱንም ነው ፥ የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ወንጀል መርማሪ ሳጅን የኔነህ ለማ የገለፁት።
በግለሰቡ ላይ የተመሰረተውን ክስ የተመለከተውና በመኖሪያ ቤቱ የተገኙትን የሰነድ ማስረጃዎች፣ ግብዓቶችና የሰው ምስክሮችን ያደመጠው የጨርቆስ ክፍለከተማ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤትም ፥ የመንግስትን ሰነዶችን በሃሰተኛ መንገድ በማዘጋጀትና በመሸጥ ወንጀል ግለሰቡን ጥፋተኛ በማለትበ10 ዓመት ፅኑ እስራትና በ4 ሺህ ብር እንዲቀጣ ወስኖበታል።