Latest Blog posts
Editors Pick
Latest documents
Education and Training Policy of Ethiopia - Amharic version - 2023 7263 Downloads - policies and strategies | 7.6 MB | |
The Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration - the Extent of Party Autonomy 218 Downloads - Arbitration Law | 635.59 KB | |
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25 9026 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 10.72 MB | |
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ እይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ FEATURED 408 Downloads - Criminal Law | 317.19 KB | |
Federal Supreme Court Cassation Decisions - Table of content Volume 1-25 10533 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 6.57 MB |
- Details
- Category: Legal News - የሕግ ዜናዎች
ቀደም ሲል የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ኖሯቸው በህገ ወጥ መንገድ ተጨማሪ ቦታ ለያዙ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጀ
በአዲስ ከተማ አስተዳደር ህገወጥ ተብለው የተለዩ እስከ 60 ሺህ የሚደርሱ የመሬት ይዞታዎች ሲኖሩ ፥ እነዚህን የመሬት ይዞታዎች መልክ ለማስያዝ ነው የአሁኑ የህግ ማእቀፍ የተዘጋጀው።
በከተማ አስተዳደሩ የይዞታ አስተዳደርና የሽግግር ጊዜ ፅህፈት ቤት ምክትል ሰራ አስክያጅ አቶ ደረጀ ላቀው እንዳሉት ፥ የመሬት ይዞታዎቹን መልክ የማስያዝ ስራ በሁለት መንገድ የሚከናወን ነው ፤ አንደኛው የሊዝ ስርዓቱን በመከተል ህጋዊ ማድረግ ሲሆን ፥ ሌላኛው ደግሞ ማንሳት ነው።
በከተማ አስተዳደሩ ህገ ወጥ እየተባሉ ያሉት የመሬት ይዞታዎች በግለሰቦች ቢያዙም የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የሌላቸው ናቸው።
አቶ ደረጀ በበኩላቸው በሊዝ አዋጁ መሰረት በህገ ወጥ መንገድ የተስፋፉ የመሬት ይዞታዎች እንደ አሰፈላጊነቱ የሚስተናገዱት በሊዝ ክፍያ ፈፅመው መሆኑን በመጥቀስ ፥ የህግ ማእቀፉ ፀድቆ ተግባራዊ ሲደረግ ፤ ለግለሰቦቹ የባለቤትነት መብት የሚሰጥና ይዞታዎቹን በተሻለ ሁኔታ ለማልማት ያስችላል ይላሉ።
የህግ ማእቀፉ ህገወጥ የመሬት ወረራን የሚያስቀር እንደሆነና በተሳሳተ ግንዛቤ አሁንም በህገ ወጥ መንገድ የመሬት ይዞታቸውን የሚያስፋፉ አካላት ላይ ግን ተገቢው እርምጃ እንደሚወሰድ ነው የገለፁት።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የይዞታ አስተዳደርና የሽግግር ጊዜ ፅህፈት ቤት ምክትል ስራ አስክያጅ አቶ ደረጀ ላቀውም ቅጣቱ በገንዘብና በእስራት የሚተገበር መሆኑን ገልፀዋል።
አብዛኛው ከህግ ማእቀፉ ዝግጅት ጋር የተያያዙ ስራዎች በመጠናቀቃቸው የህግ ማእቀፉ ለካቢኔ ቀርቦ በቅርቡ እንዲፀድቅ የሚደረግ ሲሆን ፤ ይህም በተያዘው ዓመት ተፈፅሞ ተግባራዊ ስራዎች ይጀመራል ተብሏል።