Abyssinia Law - Made for the People

Log in Register

Log in

Or sign in with your account on:

Not a member yet? Register
You are here: Home Know Ur Legal Rights

Know Your Legal Rights - መብትና ግዴታዎን ይወቁ

Notice: All articles in this section are intended for informational purpose only and should not be used to replace the need to consult official documents and to seek the advice of a qualified Lawyer. If you need a professional advice you may need to navigate to Lawyers Directory!

በዚህ አጭር ጽሑፍ የሕክምና ስህተት ምን ማለት ነው በሀገራችን ሕግስ እንዴት ተካትቷል የሕክምና ስህተት ተፈጽሟል የሚባለው ምን ምን ሲሟላ ነው የሚሉትን ነጥቦች ለመዳሰስና ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንሞክራለን፡፡ የሕክምና ስህተት ሕግ ምን ማለት ነው? የሕክምና ስህተት ሕግ (Medical Malpractice Law) ዶክተሮች ወይም ሌላ የሕክምና አገልግሎት ሰጪ አካላት የሕክምና አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት በታማሚው ላይ በችልተኝነት ለሚያደርሱት ጉዳት ያለባቸውን ተጠያቂነት የሚገዛ ሕግ ነው፡፡ ይህ የሕግ ዘርፍ ከሀገር ሀገር የተለያየ ይዘት ቢኖረውም በአብዛኛው ሀገር ግን በሕክምና ስህተት ግለሰቦች ለሚደርስባቸው ጉዳት ጉዳቱን ያደረሰው አካል ተጠያቂ የሚሆንበት የአሠራር ሥነ ሥርዓት አላቸው፡፡ አንድ…
ተሸከርካሪዎችን ወደ ሀገር ማስገባት የሚችሉት እነማን ናቸው? · በተሸከርካሪ አስመጪነት የንግድ ፍቃድ ያላቸው በዘርፉ የተሰማሩ አስመጪዎች፤ · በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሽከርካሪ ማበረታቻ የተፈቀደላቸው ኢንቨስተሮች፤ · በውጭ ሀገር ከ5 ዓመት በላይ ኖረው ጠቅልለው ወደ ሀገር ተመላሽ የሚሆኑ ዲያስፖራዎች ወይም ወደ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመኖር የሚመጡ የውጭ አገር ዜጎች /እነዚህ ማስገባት (ማስመጣት የሚችሉት አንድ የግል መገልገያ አውቶሞቢል ብቻ ነው፡፡) የአንድ ተሸከርካሪ ቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ እንዴት ይተመናል? የመኪና ቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ የሚተመነው በመኪናው የሲ.ሲ መጠን፣ መኪናው በተመረተበት ጊዜ እና መኪናው በተገዛበት ዋጋ ነው፡፡ እነዚህን ሦስት መተመኛዎች ከዚህ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡…
በአለማችን በየዓመቱ አምስት ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ሲጋራ በማጨስ ምክንያት በሚከሰቱ የጤና ችግሮች እንደሚሞቱም በዘርፉ የተደረጉ የተለያዩ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ በታዳጊ አገሮች ውስጥ ያለዕድሜ የሚከሰተውን ከፍተኛ የሞት መጠንና ህመምተኛነት በማባባስ ረገድ ትምባሆ ወይንም ሲጋራ ማጨስ ቁልፍ ሚና እንዳለው የሚያመላክቱት እነዚህ ጥናቶች፤ የሲጋራ አጫሾች ቁጥር በአደጉት አገራት እየቀነሰ መምጣቱንና በአንፃሩ ደግሞ በታዳጊ አገራት በከፍተኛ መጠን በመጨመር ላይ መሆኑን ይጠቁሟሉ፡፡ በህዝባዊ ሥፍራዎች ሲጋራ ማጨስ በሕግ መከልከሉ፤ ከፍተኛ ታክስ በሲጋራ ምርቶች ላይ መጣሉ፣ የሲጋራ ማስታወቂያዎች እንዳይሠራ መከልከሉና የሲጋራን የጤና ጠንቅነት ለዜጐች በስፋት ማስተማር ባደጉ አገራት ላይ የሚገኙ የሲጋራ አጫሾች ቁጥር…
ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የአቢሲኒያሎው ድኅረገጽ ተከታታዮች! ዛሬ ስለሰላማዊ ሰልፍ እና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ የማድረግ መብትዎ አንዳንድ የሕግ ድንጋጌዎችን ልንነግራችሁ ወደድን፡፡ መሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን አስመልክቶ በሀገራችን የሚጠቀሱ የሕግ መሠረቶች የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 30 ድንጋጌዎች እና የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 3/1983) ናቸው፡፡ ከቤት ውጪ የሚደረግን ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍን በሚመለከት “አግባብ ያላቸው ሥርዓቶች ሊደነገጉ ይችላሉ” ተብሎ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 30 ንዑስ አንቀጽ 1 ቢደነገግም ሰላማዊ ሰልፍን በሚመለከት የወጣውና ሥራ ላይ ያለው ሕግ በሽግግር መንግሥት በ1983 ዓ.ም የታወጀው “የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ …
ሰላም እንዴት ናችሁ! ዛሬ የሰበር ቅሬታ ወይም አቤቱታ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ለማቅረብ መሟላት ስላለባቸው ጉዳዮች አጭር ነገር ልናስታውሳችሁ ወደድን፡፡ በዚህ መሠረት አንድ ጉዳይ በስር ፍርድ ቤት መሠረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በመሆኑም በሰበር ሊታረምልኝ ወይም ሊታይልኝ ይገባል የሚል አንድ አቤቱታ አቅራቢ ማሟላት የሚገባቸው ወይም ጥንቃቄ ሊደረግባቸው የሚገቡ ሁኔታዎችን እንደሚከተለው አቅረበናል፡፡ ሰበር ሰሚ ችሎት አንድን ጉዳይ ለማቅረብ መረጋገጥ ከሚገባቸው ነገሮች መካከል አንድ የስር ፍርድ ቤት ሰነዶች ይገኝበታል፡፡ በዚህም መሠረት ጉዳዩ ከወረዳ፤ ከማህበራዊ ፍርድ ቤትወይም ከመጀመሪያ ፍ/ቤት ወይም ከከፍተኛ ፍ/ቤት ወይም ከክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት …
አይዞት አይደንግጡ! የገዙት ሞባይል ርካሽ በመሆኑ ብቻ ወንጀለኛ ይሆናሉ ማለታችን አይደለም፡፡ ነገር ግን ከመደበኛ የግብይት ሥርዓት ውጭ በተለያዩ አጋጣሚዎች ከግለሰቦች በርካሽ ዋጋ የምንሸምታቸው የሞባይል ስልኮች ፍርድ ቤት አስቀርበው በእሥራት ሊያስቀጡን የሚችሉበት አጋጣሚ ጥቂት አይደለም፡፡ የመሸሸግ ወንጀልን የሚደነግገው የተሻሻለው የኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 682 የወንጀል ፍሬ ወይም ውጤት የሆኑ ንብረቶችን መያዝ፣ መደበቅ፣ ማስቀመጥ ሊያስከትል የሚችለውን ኃላፊነት ይዘረዝራል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሠረት ወንጀለኞችን ለመረዳት ወይም ከወንጀል ድርጊቶች ጥቅም ለማግኘት ታስቦ/ታውቆ ከሚደረግ የመሸሸግ ድርጊት በተጨማሪ ግለሰቦች በቸልተኝነት ማለትም የተጠቀሰው ንብረት የወንጀል ፍሬ መሆኑን ማወቅ እየተገባቸው በግድ የለሽነት ወይም በሌላ…
‹‹መሽናት ክልክል ነው›› ‹‹መሽናት በሕግ ያስቀጣል›› ‹‹አጥር ሥር የሚሸና ውሻ ብቻ ነው›› …ወዘተ በሀገራችን ልዩ ልዩ ቦታዎች የሚገኙ የክልከላ ጥቅሶች ናቸው፡፡ በአብዛኛው የሀገራችን ከተሞች በመንገድ ዳር ሲሸኑ ማየት የተለመደ ድርጊት ከመሆኑ ባሻገር ነውርነቱ ቀርቷል፡፡ በውነቱ ለከተማችን ሽንት ሽንት ማለት ወንዶች ተጠያቂዎች ነን፡፡ ለምንድነው ግን በየመንገዱ፣ በየአጥሩ፣ በየሥርቻውና በየጉራንጉሩ ሽንት መሽናት ልምድ ሆኖ የቀረው? ምናልባት የከተማ አስተዳደሮች በቂ የሆነ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች በየቦታው ስላላኖሩልን ይሆናል፡፡ መንገድ ላይ ሽንት መሽናት ነውር መሆኑስ ለምን ቀረ? መንገድ ላይ ቆሞ መሽናት ወይስ መንገድ ላይ እየበሉ መሔድ? የቱ ነው ነውር? ይህ…
ማንኛውንም ቤት፣ ለንግድ ቢሆን ለመኖሪያ፣ ቦታ፣ ክፍል ወይም ተሽከርካሪ የሚያከራዩ ከሆነ ይህንን የሕጉን አንቀጽ ከግምት ያስገቡ፡፡ በ2001 ዓ.ም የወጣው የጸረ ሽብር አዋጅ አዋጅ ቁጥር 652/2001 በአንቀጽ 15 ማንኛውም ቤት፣ ቦታ፣ ክፍል ወይም ተሽከርካሪ ወይም ተመሳሳይ መገልገያ አከራይ (ልብ ይበሉ አከራይ) የሆነ ሰው የተከራዩን ማንነት በዝርዝርና በጽሑፍ የመያዝ እንዲሁም በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የማሳወቅ ግዴታ አለበት ብሎ ደንግጓል፡፡ በዚህም መሠረት አከራይ ከሆኑ የሚያከራዩትን ሰው ማንነት ማለትም ስም፣ አደራሻ እንዲሁም መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም ማንኛውም ዓይነት ማንነትን የሚገልጽ ማስረጃ ኮፒ በማድረግ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ…
ሰላም የአቢሲኒያ ሎው አንባብያን አንዴት ከርማችኋል፡፡ መብትና ግዴታዎን ይወቁ በሚል ርዕስ ዘርፈ ብዙ ሀሳቦችን እያነሳን መብትና ግዴታችንን የማስተዋወቅ አምድ ከከፈትን ቆየት አልን፡፡ ይህ መብትና ግዴታዎትን ይወቁ በሚል ርዕስ የጀመርነውን ሃሳብ በጣም ጠቃሚ ነው ቀጥሉበት ላላችሁን ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡ ዛሬ የምናነሳው ርዕስ አያድርሰውና ከሥራ ጋር ተያይዞ ስለሚደርስ አደጋ እና ከዚህ ጋር ተያይዘው ማወቅ ስላለብን መብትና ግዴታዎች ለማውሳት ነው፡፡ መቼስ አብዛኞቻችን ይብዛም ይነስም፣ ያስደስት አያስደስትም፣ ያዝናና አያዝናናም ተቀጥረን ሠራተኛ የሚለውን ማዕረግ ይዘን እንቀሳቀሳለን፡፡ ታዲያ ከሥራ ጋር ተያይዘው የሚደርሱ አደጋዎችን የሀገራችን ሕጎች እንዴት አይተውታል እንዴትስ አስተናግደውታል የሚለውን ሀሳብ ይዘን…
ቃብድ የሚለው ቃል በተለምዶ ቀብድ ብለን የመንጠራው ነው፡፡ ሕጋችን ቃብድ ስለሚለው እኛም ቃብድ ብለነዋል፡፡ ያው እናንተ ቀብድ ብላችሁ ተረዱት፡፡ 1. የቃብድ ክፍያ ማለት ምን ማለት ነው? የቃብድ ክፍያ ማለት ተዋዋይ ወገኑ በውሉ ለመገደድ ወይም ውሉን እስከመጨረሻው ተከታትሎ ለመጨረስ ያለውን ፍላጎት ለማሳየት ሲል በመያዣነት ለሌላኛው ወገን የሚሰጠው ክፍያ ነው:: እንዲህ ዓይነቱ ክፍያ የሚፈጸምበት ዓላማም ተደራዳሪው ወገን ውሉን አስመልክቶ ከልቡ መሆኑን ወይም በውሉ ለመገደድ ያለውን ፍላጎት የሚገልጽበት ስልት ነው:: የሚከፈለውም የክፍያ መጠን እንደየ አከባቢው ሁኔታ ወይም እንደስራው ዓይነት እና ስምምነት የሚለያይ ሲሆን በአማራጭም /earnest/ a Good-faith deposit…
ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኛ ከሆኑ መሠረታዊ ሕጋዊ መብትና ግዴታ አለበዎት፡፡ ከአሠሪና ሠራተኛ መብትና ግዴታ ተያይዘው ያሉ መብቶች አጅግ በርካታ ቢሆኑም ዋና ዋና የሚባሉትን ግዴታዎች ቢያወቁ ለርሶ ጠቃሚ ይሆናል በሚል እምነት የአሠሪና ሠራተኛ ግዴታዎች ጠቅለል ባለ መልኩ አቅርበነዋል፡፡ የአሠሪ ግዴታዎች አሠሪ የሚከተሉት ግዴታዎች አሉበት፡፡ ሥራ የመስጠትና ውሉ በሌላ ሁኔታ ካልገለጸ በስተቀር መሣሪያና ጥሬ ዕቃ የማቅረብ ግዴታ ደሞዝና ሌሎች ክፍያዎችን የመፈጸም ግዴታ የሰራተኛውን ሰብአዊ ክብር፣ ከስራ ጋር የተያያዘ ጤንነትና ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ሕጉ በሚያዘው መሰረት የተለያዩ ሁኔታዎችን በመዝገብ የመያዝ እና አግባብ ባለው አካል ሲጠየቅ መዝገብ የማቅረብ ግዴታ የስራ…

Page 1 of 2